መጽሐፈ ምሳሌ 25
25
1እነኚህም የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ሰዎች የገለበጧቸው የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው።
2የእግዚአብሔር ክብር በምሥጥራዊ መንገድ ነገርን ማከናወን ነው፥
የነገሥታት ክብር ግን ነገርን መመርመር ነው።
3እንደ ሰማይ ከፍታ እንደ ምድርም ጥልቀት
የነገሥታት ልብ አይመረመርም።
4ከብር ዝገትን አስወግድ፥
ፈጽሞም ይጠራል።
5ከንጉሥ ፊት ክፉ ሰዎችን አርቅ፥
ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።
6 #
ሉቃ. 14፥8-10። በንጉሥ ፊት አትመካ፥
በታላላቆችም ስፍራ አትቁም፥
7ዐይኖችህ ባዩት በመኰንን ፊት ከምትዋረድ፦
“ወደዚህ ከፍ በል” ብትባል ይሻልሃልና።
8ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት
ለሙግት ወደ ሽንጎ ፈጥነህ አትውጣ፥
9ሙግትህን ከባልንጀራህ ጋር በቀጥታ ፈጽም፥
የሌላ ሰው ምሥጢር ግን አትግለጥ፥
10የሚሰማ እንዳይነቅፍህ፥
ስምህንም ለሁልጊዜ እንዳያጠፋው፤
11በአግባብ የተነገረ ቃል፥
በብር ፃሕል ላይ እንደተቀመጠ ወርቅ ነው።
12የሚሰማን ጆሮ የሚገሥጽ ጠቢባዊ ምክር፥
እንደ ወርቅ ጉትቻ እንደሚያንጸባርቅም ዕንቁ ነው።
13ለላኩት የታመነ መልእክተኛ፥
በመከር ወራት ደስ እንዲሚያሰኝ የውርጭ ጠል ነው፥
የጌታውን ነፍስ ያሳርፋልና።
14ስለ ስጦታው በሐሰት የሚመካ ሰው
ዝናብ እንደሌለው ደመናና ነፋስ ነው።
15በትዕግሥት አለቃ ይለዝባል፥
ገር ምላስ አጥንትን ይሰብራል።
16በጣም እንዳትጠግብና እንዳትተፋው፥
ማር ባገኘህ ጊዜ የሚበቃህን ብላ።
17እንዳይሰለቸውና እንዳይጠላህ፥
አዘውትረህ ወደ ባልንጀራህ ቤት አትሂድ።
18በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር
እንደ መዶሻና እንደ ሰይፍ እንደ ተሳለም ቀስት ነው።
19ከሃዲን ሰው በመከራ ጊዜ መተማመን
እንደ ተሰበረ ጥርስና እንደ ሰለለ እግር ነው።
20ባዘነ ሰው ላይ የሚዘምር፥
በብርድ ቀን ልብስን እንደሚገፍና
በቁስልም ላይ ሆምጣጤ እንደሚጨምር ሰው ነው።
21 #
ሮሜ 12፥20። ጠላትህ ቢራብ እንጀራ አብላው፥
ቢጠማም ውኃ አጠጣው፥
22በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና፥
ጌታም ይሸልምሃልና።
23የሰሜን ነፋስ ዝናብ ያመጣል፥
ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቈጣል።
24ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ከመቀመጥ
በሰገነት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
25የቀዘቀዘ ውኃ ለደረቀ ጉሮሮ#25፥25 ለተጠማች ነፍስ ማለትም ይቻላል። ደስ እንደሚያሰኝ፥
ከሩቅ አገር የመጣ መልካም ምሥራች እንዲሁ ነው።
26በኀጥእ ፊት የሚወድቅ ጻድቅ
እንደደፈረሰ ምንጭና እንደ ተበከለ ኩሬ ነው።
27ብዙ ማር መብላት መልካም አይደለም፥
ክቡር ነገሮችን መፈለግ ግን የሚያስከብር ነው።
28ራሱን መቆጣጠር የማይችል ሰው፥
ቅጥር እንደሌለው እንደ ፈረሰ ከተማ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 25: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ