1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 2:12-15

1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 2:12-15 መቅካእኤ

ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም የወለደው የበኩር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሳምዓ፥ አራተኛውንም ናትናኤልን፥ አምስተኛውንም ራዳይን፥ ስድስተኛውንም አሳምን፥ ሰባተኛውንም ዳዊትን ነበረ፤