1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 2
2
የእስራኤል ልጆች እና የይሁዳ ትውልድ
1የእስራኤልም ልጆች፤ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ 2ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር ናቸው።
3የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ሴዋ የተወለዱለት ልጆች ናቸው። የይሁዳም የበኩር ልጅ ዔር በጌታ ፊት ክፉ ነበረ፤ እርሱም ገደለው። 4ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ።
5የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው። 6የዛራም ልጆች፤ ዘምሪ፥ ኤታን፥ ሄማን፥ ከልኮል፥ ዳራ ናቸው፤ አምስት ነበሩ። 7#ኢያ. 7፥1።የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ። 8የኤታንም ልጅ አዛርያ ነበረ።
9ለኤስሮም የተወለዱለት ልጆች፤ ይረሕምኤል፥ አራም፥ ካልብ ነበሩ። 10አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳን ልጆች አለቃ ነአሶንን ወለደ፤ 11ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥ 12ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ 13እሴይም የወለደው የበኩር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሳምዓ፥ 14አራተኛውንም ናትናኤልን፥ አምስተኛውንም ራዳይን፥ 15ስድስተኛውንም አሳምን፥ ሰባተኛውንም ዳዊትን ነበረ፤ 16እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያም ልጆች፤ አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል ናቸው፤ ሦስቱ ነበሩ። 17አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ዬቴር ነበር።
18የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ፤ ልጆቹዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ። 19ዓዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት። 20ሆርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
21ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስልሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኪር ልጅ ገባ፤ ሠጉብንም ወለደችለት። ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ 22ሠጉብም በገለዓድ ምድር ሀያ ሦስት ከተሞች ነበሩትን ጌሹርን ወለደ። 23ጌሹርና አራምም የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስልሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ። 24ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
25የኤስሮምም የበኩር ልጁ የይረሕምኤል ልጆች በኩሩ ራም፥ ቡናህ፥ ኦሬን፥ ኦጼም፥ አኪያ ነበሩ። 26ለይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናም እናት ነበረች። 27የይረሕምኤል የበኩሩ የራም ልጆች መዓስ፥ ያሚን፥ ዔቄር ነበሩ። 28የኦናምም ልጆች ሸማይና ያዳ ነበሩ። የሸማይ ልጆች ናዳብና አቢሱር ነበሩ። 29የአቢሱርም ሚስት አቢካኢል ትባል ነበር፤ አሕባንንና ሞሊድን ወለደችለት። 30የናዳብም ልጆች ሴሊድና አፋይም ነበሩ፤ ሴሌድም ያለ ልጆች ሞተ። 31የአፋይምም ልጅ ይሽዒ፥ የይሽዒም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ። 32የሸማይም ወንድም የያዳ ልጆች ዬቴርና ዮናታን ነበሩ፤ ዬቴርም ያለ ልጆች ሞተ። 33የዮናታንም ልጆች ፌሌትና ዛዛ ነበሩ፤ እነዚህ የይረሕምኤል ልጆች ነበሩ። 34ለሶሳንም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ለሶሳንም ኢዮሄል የተባለ ግብጻዊ አገልጋይ ነበረው። 35ሶሳንም ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ልጁን አጋባት፥ እርሷም ዓታይን ወለደችለት። 36አታይም ናታንን ወለደ፤ ናታንም ዛባድን ወለደ፤ 37ዛባድም ኤፍላልን ወለደ፤ ኤፍላልም ዖቤድን ወለደ፤ 38ዖቤድም ኢዩን ወለደ፤ ኢዩም ዓዛርያስን ወለደ፤ 39ዓዛርያስም ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስም ኤል-ዓሣን ወለደ፤ 40ኤል-ዓሣም ሲስማይን ወለደ፤ ሲስማይም ሰሎምን ወለደ፤ 41ሰሎምም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
42የይረሕምኤልም ወንድም የካሌብ ልጆች በኩሩ የዚፍ አባት ሞሳ፥ የኬብሮንም አባት የመሪሳ ልጆች ነበሩ። 43የኬብሮንም ልጆች ቆሬ፥ ተፉዋ፥ ሬቄም፥ ሽማዕ ነበሩ። 44ሽማዕም የዮርቅዓምን አባት ረሐምን ወለደ፤ ሬቄምም ሸማይን ወለደ። 45የሸማይም ልጅ ማዖን ነበረ፤ ማዖንም የቤት-ጹር አባት ነበረ። 46የካሌብም ቁባት ዔፋ ሐራንን፥ ሞዳን፥ ጋዜዝን ወለደች፤ ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። 47የያህዳይም ልጆች ሬጌም፥ ኢዮታም፥ ጌሻን፥ ፋሌጥ፥ ሔፋ፥ ሸዓፍ ነበሩ። 48የካሌብም ቁባት ማዕካ ሼቤርንና ቲርሐናን ወለደች። 49ደግሞም የመድማናን አባት ሸዓፍንና የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ ዓክሳ ነበረች።
50የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኩሩ የሆር ልጅ የቂርያት-ይዓሪም አባት ሦባል፥ 51የቤተልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት-ጋዴር አባት ሐሬፍ። 52ለቂርያት-ይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኩሌታ። 53የቂርያት-ይዓሪምም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፉታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሽራውያን ነበሩ፤ ከእነዚህም ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ወጡ። 54የሰልሞንም ልጆች ቤተልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዓጣሮት-ቤት-ዮአብ፥ የመናሕታውያን እኩሌታ፥ ጾርዓውያን ነበሩ። 55በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ