የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 1

1
ከአዳም እስከ አብርሃም
1አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥ 2ቃይናን፥ መላልኤል፥ ያሬድ፥ 3ሄኖክ፥ ማቱሳላ፥ ላሜሕ፥ 4ኖኅ፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት።
5የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። 6የጋሜርም ልጆች፤ አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። 7የያዋንም ልጆች፤ ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው።
8የካምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው። 9የኩሽም ልጆች፤ ሴባ፥ ሐዊላ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰብቃታ ናቸው። የራዕማም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን ናቸው። 10ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ኃያል መሆንን ጀመረ። 11ምጽራይምም የወለደው ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍተሂምን፥ 12ፈትሩሲምን፥ ፍልስጥኤማውያን አባት ከስሉሂምን፥ ከፍቶሪምን ነበር። 13ከነዓንም የወለደው የበኩር ልጁን ሲዶንን፥ ሔትን፥ 14ኢያቡሳዊውን፥ አሞራዊውን፥ ጌርጌሳዊውን፥ 15ኤዊያዊውን፥#1፥15 ሒዋውያን ዐርካዊውን፥ ሲኒያዊውን፥ 16አራዴዎንን፥ ሰማሪዎንን፥ አማቲንን ነበር።
17የሴምም ልጆች፤ ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌቴር፥ ሞሳሕ ናቸው። 18አርፋክስድም ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ። 19ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ይባል ነበር። 20ዮቅጣንም የወለደው አልሞዳድን፥ ሼሌፍን፥ ሐጻርማዌትን፥ ያራሕን፥ 21ሀዶራምን፥ ኡዛልን፥ ዲቅላን፥ 22ዖባልን፥ አቢማኤልን፥ ሳባን፥ 23ኦፊርን፥ ሐዊላን፥ ዮባብን ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ።
24ሴም፥ አርፋክስድ፥ ሼላሕ፥ 25ዔቦር፥ ፋሌቅ፥ ራግው፥ 26ሴሮሕ፥ ናኮር፥ ታራ፥ 27አብርሃም የተባለ አብራም።
ከአብርሃም እስከ ያዕቆብ
28የአብርሃምም ልጆች፤ ይስሐቅና እስማኤል ናቸው። 29ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የእስማኤል በኩር ልጅ ነባዮት፤ ከዚህ በኋላ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ 30ሚሽማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ 31ይጡር፥ ናፊሽ፥ ቄድማ ነበሩ፤ እነዚህ የእስማኤል ልጆች ናቸው።
32የአብርሃምም ቊባት የኬጡራ ልጆች፤ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የሽቦቅ፥ ሹሐን ናቸው። የዮቅሻንም ልጆች፤ ሳባና ድዳን ናቸው። 33የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ።
34አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና እስራኤል ነበሩ።
35የዔሳው ልጆች፤ ኤልፋዝ፥ ራጉኤል፥ የዑስ፥ የዕላም፥ ቆሬ ናቸው። 36የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ ናቸው። 37የራጉኤል ልጆች፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ ናቸው።
38የሴይርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሦባል፥ ጽብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን ናቸው። 39የሎጣንም ልጆች፤ ሖሪ፥ ሔማም ናቸው፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች። 40የሦባል ልጆች፤ ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ አውናም ናቸው። የጽብዖንም ልጆች፤ አያነና ዓና ናቸው። 41የዓና ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶንም ልጆች፤ ሔምዳን፥ ኤስባን፥ ይትራን፥ ክራን ናቸው። 42የኤጽር ልጆች፤ ቢልሐን፥ ዛዕዋን፥ ዓቃን ናቸው። የዲሳን ልጆች፤ ዑፅና አራን ናቸው።
43በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማይቱም ስም ዲንሃባ ነበረ። 44ባላቅም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የባሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ። 45ኢዮባብም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ። 46ሑሳምም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በሞዓብ ሜዳ ምድያምን የመታው የባዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ዓዊት ነበረ። 47ሃዳድም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የመሥሬቃ ሰው ሠምላ ነገሠ። 48ሠምላም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሆቦት ሰው ሳኡል ነገሠ። 49ሳኡልም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ። 50በኣልሐናንም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች፤ ሃዳድም ሞተ።
51የኤዶምያስም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥ 52አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፊኖን አለቃ፥ 53ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ ሚብሳር አለቃ፥ 54መግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ የኤዶምያስ አለቆች ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ