የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ነህምያ 7:4-73

መጽሐፈ ነህምያ 7:4-73 አማ05

ኢየሩሳሌም ታላቅና ሰፊ ከተማ ሆና ነበር፤ ነገር ግን የሚኖርባት ሕዝብ ቊጥር አነስተኛ ነበር፤ ገና ብዙ ቤቶችም አልተሠሩባትም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡንና መሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖችን እንድሰበስብና የቤተሰባቸውን የትውልድ ሐረግ አመዘጋገብ እንድቈጣጠር አነሣሣኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ የተመለሱትንም ምርኮኞች የትውልድ ሐረግ ማስረጃ መዝገብ አገኘሁ፤ ያገኘሁትም ማስረጃ ከዚህ የሚከተለው ነበር። ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር። ሲመለሱም መሪዎቻቸው ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ዐዛርያ፥ ረዓምያ፥ ናሐማኒ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፔሬት፥ ቢግዋይ፥ ነሑምና በዓና ናቸው። ከምርኮ ከተመለሱት ከእያንዳንዱ ጐሣ ተወጣጥተው የተመዘገቡት የእስራኤል ጐሣዎችና የትውልዳቸው ብዛት ይህ ነው፦ ከፓርዖሽ ወገን የተመዘገቡ 2172 ከሸፋጥያ ወገን የተመዘገቡ 372 ከአራሕ ወገን የተመዘገቡ 652 የኢያሱና የኢዮአብ ትውልድ ጐሣ ከሆነው ከፓሐትሞአብ ወገን የተመዘገቡ 2818 ከዔላም ወገን የተመዘገቡ 1254 ከዛቱ ወገን የተመዘገቡ 845 ከዛካይ ወገን የተመዘገቡ 760 ከቢኑይ ወገን የተመዘገቡ 648 ከቤባይ ወገን የተመዘገቡ 628 ከዓዝጋድ ወገን የተመዘገቡ 2322 ከአዶኒቃም ወገን የተመዘገቡ 667 ከቢግዋይ ወገን የተመዘገቡ 2067 ከዓዲን ወገን የተመዘገቡ 655 ሕዝቅያስ ተብሎ ከሚጠራው ከአጤር ወገን የተመዘገቡ 98 ከሐሹም ወገን የተመዘገቡ 328 ከቤጻይ ወገን የተመዘገቡ 324 ከሐሪፍ ወገን የተመዘገቡ 112 ከገባዖን ወገን የተመዘገቡ 95 የቀድሞ አባቶቻቸው ከዚህ በሚከተሉት ከተሞች የሚኖሩም ከምርኮ ተመልሰዋል፦ በቤተልሔምና በነጦፋ የሚኖሩ 188 በዐናቶት የሚኖሩ 128 በቤት ዓዝማዌት የሚኖሩ 42 በቂርያትይዓሪም፥ በከፊራና በበኤሮት የሚኖሩ 743 በራማና በጌባዕ የሚኖሩ 621 በሚክማስ የሚኖሩ 122 በቤትኤልና በዐይ የሚኖሩ 123 በሁለተኛይቱ ነቦ የሚኖሩ 52 በሁለተኛይቱ ዔላም የሚኖሩ 1254 በሓሪም የሚኖሩ 320 በኢያሪኮ የሚኖሩ 345 በሎድ፥ በሐዲድና በኦኖ የሚኖሩ 721 በሰናአ የሚኖሩ 3930 ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ጐሣዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፦ የኢያሱ ዘር ከሆነው ከይዳዕያ ወገን 973 ከኢሜር ወገን 1052 ከፓሽሑር ወገን 1247 ከሓሪም ወገን 1017 ከምርኮ የተመለሱ ሌዋውያን ጐሣዎች፦ የሆዳውያ ዘሮች ከነበሩት ከኢያሱና ከቃድሚኤል ወገን 74 የአሳፍ ዘሮች ከሆኑት ከቤተ መቅደስ መዘምራን ወገን 148 የሻሉም፥ የአጤር፥ የጣልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሾባይ ዘሮች ከሆኑት የቤተ መቅደስ ዘበኞች ወገን 138 ከምርኮ የተመለሱ የቤተ መቅደስ ሠራተኞች፥ ዘሮች በየጐሣቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ሻልማይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ መዑኒም፥ ነፉሸሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሊት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲስራ፥ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ። ከምርኮ የተመለሱ የሰሎሞን አገልጋዮች ጐሣዎች፦ ሶጣይ፥ ሶፌሬት፥ ፐሪዳ፥ ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥ ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት ሀጸባይምና አሞን። ከምርኮ የተመለሱት የቤተ መቅደስ ሠራተኞችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ብዛት ጠቅላላ ድምር 392 ነበር። ቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ከሩብ፥ አዶንና ኢሜር ተብለው ከሚጠሩት የገጠር ከተሞች የተመለሱ የደላያ፥ የጦቢያና የነቆዳ ጐሣዎች ወገኖች የሆኑት ዘሮች ድምር 642 ነበር፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ዘሮች መሆናቸውን ለማወቅ የሚያስችል በቂ ማስረጃ አልነበራቸውም። ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች የቀድሞ አባቶቻቸውን የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ አልቻሉም፤ እነርሱም ሖባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ ናቸው፤ የካህን ወገን የሆነው የባርዚላይ የቀድሞ አባት የገለዓድ ተወላጅ ከነበረው ከባርዚላይ ወገን አንዲት ሴት አግብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ የዐማቱን ጐሣ ስም ወርሶ ይኖር ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻቸውንም የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ ካለመቻላቸው የተነሣ፥ በክህነት ለማገልገል አልተፈቀደላቸውም። ስለዚህም የይሁዳ ገዥ በኡሪምና በቱሚም የሚያገለግል ካህን እስከሚነሣበት ጊዜ ድረስ ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ከሚቀርበው ቊርባን መመገብ የማይችሉ መሆናቸውን ነገራቸው። ከምርኮ የተመለሰው ሕዝብ ጠቅላላ ድምር 42360 የወንዶችና የሴቶች አገልጋዮቻቸው ቊጥር 7337 የወንዶችና የሴቶች መዘምራናቸው ቊጥር 245 የፈረሶቻቸው ብዛት 736 የበቅሎዎቻቸው ብዛት 245 የግመሎቻቸው ብዛት 435 የአህዮቻቸው ብዛት 6720 ነበር። አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎችም ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመሥራት የሚረዳ አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ ከእነርሱም መካከል፥ አገረ ገዢው፦ 8 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 50 ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ 530 የካህናት ልብሶችን ሰጠ። የጐሣ አለቆችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1250 ኪሎ የሚመዝን ብር ሰጡ፤ የቀሩት ሰዎችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1100 ኪሎ የሚመዝን ብርና 67 የካህናት ልብሶችን ሰጥተዋል። ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።