የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ነህምያ 7:4-73

ነህምያ 7:4-73 NASV

ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር። ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ። የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከዓዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋራ ነው። የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፦ የፋሮስ ዘሮች 2,172 የሰፋጥያስ ዘሮች 372 የኤራ ዘሮች 652 የኢያሱና የኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,818 የኤላም ዘሮች 1,254 የዛቱዕ ዘሮች 845 የዘካይ ዘሮች 760 የቢንዊ ዘሮች 648 የቤባይ ዘሮች 628 የዓዝጋድ ዘሮች 2,322 የአዶኒቃም ዘሮች 667 የበጉዋይ ዘሮች 2,067 የዓዲን ዘሮች 655 በሕዝቅያስ የትውልድ ሐረግ የአጤር ዘሮች 98 የሐሱም ዘሮች 328 የቤሳይ ዘሮች 324 የሐሪፍ ዘሮች 112 የገባዖን ዘሮች 95 የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች 188 የዓናቶት ሰዎች 128 የቤት አዝሞት ሰዎች 42 የቂርያትይዓይሪም፣ የከፊራና የብኤሮት ሰዎች 743 የራማና የጌባዕ ሰዎች 621 የማክማስ ሰዎች 122 የቤቴልና የጋይ ሰዎች 123 የሌላው ናባው ሰዎች 52 የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254 የካሪም ዘሮች 320 የኢያሪኮ ዘሮች 345 የሎድ፣ የሐዲድና የኦኖም ዘሮች 721 የሴናዓ ዘሮች 3,930 ካህናቱ፦ ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973 የኢሜር ዘሮች 1,052 የፋስኮር ዘሮች 1,247 የካሪም ዘሮች 1,017 ሌዋውያኑ፦ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74 መዘምራኑ፦ የአሳፍ ዘሮች 148 በር ጠባቂዎቹ፦ የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 138 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋ፣ የጠብዖት ዘሮች፣ የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን፣ የልባና፣ የአጋባ፣ የሰምላይ ዘሮች፣ የሐናን፣ የጌዴል፣ የጋሐር ዘሮች፣ የራያ፣ የረአሶን፣ የኔቆዳ ዘሮች፣ የጋሴም፣ የዖዛ፣ የፋሴሐ ዘሮች፣ የቤሳይ፣ የምዑኒም፣ የንፉሰሲም ዘሮች፣ የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፣ የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፣ የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፣ የንስያና፣ የሐጢፋ ዘሮች። የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፣ የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፣ የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈክራት ሐፂቦይምና የአሞን ዘሮች። የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392 ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የመጡ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦ የዳላያ፣ የጦብያና፣ የኔቆዳ ዘሮች 642 ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል። እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ። ስለዚህ አገረ ገዥውም ኡሪምና ቱሚም የሚይዝ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው። የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤ ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው። 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣ 435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው። አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ። ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 ምናን ብር ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 ምናን ብርና 67 ልብሰ ተክህኖ ነበር። ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።