ነህምያ 7:4-73 - Compare All Versions

ነህምያ 7:4-73 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ከተ​ማ​ዪ​ቱም ሰፊና ታላቅ ነበ​ረች፤ በው​ስ​ጥዋ የነ​በሩ ሕዝብ ግን ጥቂ​ቶች ነበሩ፤ ቤቶ​ቹም ገና አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቤ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እቈ​ጥ​ራ​ቸው ዘንድ ልቤን አነ​ሣሣ፤ አስ​ቀ​ድ​መው የመ​ጡ​ት​ንም ሰዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐ​ፋ​ቸ​ውን አገ​ኘሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ደ​ዚህ ተጽፎ አገ​ኘሁ። የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከአ​ዛ​ር​ያስ፥ ከረ​ዓ​ምያ፥ ከሄ​ሜ​ኔስ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ል​ሰማ፥ ከሚ​ስ​ፌ​ሬት፥ ከዕ​ዝራ፥ ከበ​ጉ​ዋይ፥ ከነ​ሑም፥ ከበ​ዓና፥ ከመ​ስ​ፈር ጋር መጡ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ የወ​ን​ዶች ቍጥር ይህ ነው፥ የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት። የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። የኤራ ልጆች ስድ​ስት መቶ አምሳ ሁለት። ከኢ​ያ​ሱና ከኢ​ዮ​አብ ልጆች የሆኑ የፈ​ሐት ሞዓብ ልጆች ሁለት ሺህ ስም​ንት መቶ ዐሥራ ስም​ንት። የኤ​ላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። የዘ​ቱዕ ልጆች ስም​ንት መቶ አርባ አም​ስት። የዘ​ካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። የበ​ኑይ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ስም​ንት። የቤ​ባይ ልጆች ስድ​ስት መቶ ሃያ ስም​ንት። የአ​ዝ​ጌድ ልጆች ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ሁለት። የአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስድ​ስት መቶ ስድሳ ሰባት። የበ​ጉ​ዋይ ልጆች ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት። የዓ​ዴን ልጆች ስድ​ስት መቶ አምሳ አም​ስት። የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ወገን የአ​ጤር ልጆች ዘጠና ስም​ንት። የሐ​ሱም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ ስም​ንት። የቤ​ሳይ ልጆች ሦስት መቶ ሃያ አራት። የሐ​ሪፍ ልጆች መቶ ዐሥራ ሁለት። የገ​ባ​ዖን ልጆች ዘጠና አም​ስት። የቤተ ልሔ​ምና የነ​ጦ​ፍያ ሰዎች መቶ ሰማ​ንያ ስም​ንት። የዓ​ና​ቶት ሰዎች መቶ ሃያ ስም​ንት። የቤ​ት​አ​ዝ​ሞት ሰዎች አርባ ሁለት። የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምና የቃ​ፌር፥ የቤ​ሮ​ትም ሰዎች ሰባት መቶ አርባ ሦስት። የሐ​ራ​ማና የገ​ቢኣ ሰዎች ስድ​ስት መቶ ሃያ አንድ። የማ​ኬ​ማስ ሰዎች መቶ ሃያ ሁለት። የቤ​ቴ​ልና የጋይ ሰዎች መቶ ሃያ ሦስት። የና​ብያ ሰዎች መቶ አምሳ ሁለት። የኤ​ላም ሰዎች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። የኤ​ራም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ። የኢ​ያ​ሪኮ ልጆች ሦስት መቶ አርባ አም​ስት። የሎ​ድና ሐዲድ የሐ​ኖም ልጆች ሰባት መቶ ሃያ አንድ። የሴ​ናዓ ልጆች ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ። ካህ​ናቱ ከኢ​ያሱ ወገን፦ የዮ​ዳሔ ልጆች ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። የኤ​ሜር ልጆች ሺህ አምሳ ሁለት። የፋ​ስ​ኮር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። የሐ​ራም ልጆች ሺህ ዐሥራ ሰባት። ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከሆ​ዳ​ይዋ ወገን የኢ​ያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች ሰባ አራት። መዘ​ም​ራኑ የአ​ሳፍ ልጆች መቶ አርባ ስም​ንት። በረ​ኞቹ የሴ​ሎ​ምያ ልጆች፥ የአ​ጤር ልጆች፥ የጤ​ል​ማና ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥ የሐ​ጢጣ ልጆች፥ የሶ​ባይ ልጆች መቶ አርባ ስም​ንት። ናታ​ኒም የሲአ ልጆች፥ የሐ​ሡፋ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዓት ልጆች፤ የቄ​ራስ ልጆች፥ የአ​ሲያ ልጆች፥ የፋ​ዶን ልጆች፤ የል​ባና ልጆች፥ የአ​ጋባ ልጆች፥ የሰ​ል​ማይ ልጆች፤ የሐ​ናን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፥ የጋ​ኤር ልጆች፤ የር​አያ ልጆች፥ የረ​አ​ሶን ልጆች፥ የኔ​ቆዳ ልጆች፤ የጋ​ሴም ልጆች፥ የኡዚ ልጆች፥ የፋ​ሴሓ ልጆች፤ የቤ​ሳይ ልጆች፥ የም​ዑ​ና​ው​ያን ልጆች፥ የኔ​ፋ​ሴ​ስም ልጆች፤ የበ​ቅ​ቡቅ ልጆች፥ የሐ​ቀፋ ልጆች፥ የሐ​ሩር ልጆች፤ የበ​ስ​ሎት ልጆች፥ የም​ሒዳ ልጆች፥ የሐ​ርሳ ልጆች፤ የበ​ር​ቆስ ልጆች፥ የሲ​ሣራ ልጆች፥ የታ​ማህ ልጆች፥ የነ​ስያ ልጆች፥ የሐ​ጤፋ ልጆች። የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሦ​ጠይ ልጆች፥ የሰ​ፋ​ሬት ልጆች፥ የፈ​ሪዳ ልጆች፥ የየ​ዕላ ልጆች፥ የደ​ር​ቆን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፤ የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች፥ የሐ​ጢል ልጆች፥ የፈ​ከ​ራት ልጆች፥ የሰ​ባ​ይም ልጆች፥ የአ​ሞን ልጆች። ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። ከቲ​ል​ሜል፥ ከቲ​ላ​ሬስ፥ ከኪ​ሩብ፥ ከአ​ዶን፥ ከኢ​ሜር የወጡ እነ​ዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶ​ችና ዘራ​ቸ​ውን ወይም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን መሆ​ና​ቸ​ውን ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ የዳ​ላያ ልጆች፥ የጦ​ብያ ልጆች፥ የኔ​ቆዳ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ሁለት። ከካ​ህ​ና​ቱም የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ሙም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች። እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ። ሐቴ​ር​ሰ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር አት​በ​ሉም” አላ​ቸው። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ይኸ​ውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነ​በሩ ከሎ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውና ከገ​ረ​ዶ​ቻ​ቸው ሌላ ሁለት መቶም አርባ አም​ስት ወን​ዶች መዘ​ም​ራ​ንና ሴቶች መዘ​ም​ራት ነበ​ሩ​አ​ቸው። ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድ​ስት፥ በቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሁለት መቶ አርባ አም​ስት፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አራት መቶ ሠላሳ አም​ስት፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ስድ​ስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ነበሩ። ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴ​ር​ሰ​ታም አንድ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪክ፥ አም​ሳም ድስ​ቶች፥ አም​ስት መቶ ሠላ​ሳም የካ​ህ​ናት ልብስ በቤተ መዛ​ግ​ብት ውስጥ ሰጠ። ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ዐያ​ሌ​ዎቹ በሥ​ራው ቤተ መዛ​ግ​ብት ውስጥ ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ። የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ የሰ​ጡት ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪ​ክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባ​ትም የካ​ህ​ናት ልብስ ነበረ። ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም ዐያ​ሌ​ዎቹ፥ ናታ​ኒ​ምም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።

ነህምያ 7:4-73 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር። ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ። የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከዓዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋራ ነው። የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፦ የፋሮስ ዘሮች 2,172 የሰፋጥያስ ዘሮች 372 የኤራ ዘሮች 652 የኢያሱና የኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,818 የኤላም ዘሮች 1,254 የዛቱዕ ዘሮች 845 የዘካይ ዘሮች 760 የቢንዊ ዘሮች 648 የቤባይ ዘሮች 628 የዓዝጋድ ዘሮች 2,322 የአዶኒቃም ዘሮች 667 የበጉዋይ ዘሮች 2,067 የዓዲን ዘሮች 655 በሕዝቅያስ የትውልድ ሐረግ የአጤር ዘሮች 98 የሐሱም ዘሮች 328 የቤሳይ ዘሮች 324 የሐሪፍ ዘሮች 112 የገባዖን ዘሮች 95 የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች 188 የዓናቶት ሰዎች 128 የቤት አዝሞት ሰዎች 42 የቂርያትይዓይሪም፣ የከፊራና የብኤሮት ሰዎች 743 የራማና የጌባዕ ሰዎች 621 የማክማስ ሰዎች 122 የቤቴልና የጋይ ሰዎች 123 የሌላው ናባው ሰዎች 52 የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254 የካሪም ዘሮች 320 የኢያሪኮ ዘሮች 345 የሎድ፣ የሐዲድና የኦኖም ዘሮች 721 የሴናዓ ዘሮች 3,930 ካህናቱ፦ ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973 የኢሜር ዘሮች 1,052 የፋስኮር ዘሮች 1,247 የካሪም ዘሮች 1,017 ሌዋውያኑ፦ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74 መዘምራኑ፦ የአሳፍ ዘሮች 148 በር ጠባቂዎቹ፦ የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 138 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋ፣ የጠብዖት ዘሮች፣ የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን፣ የልባና፣ የአጋባ፣ የሰምላይ ዘሮች፣ የሐናን፣ የጌዴል፣ የጋሐር ዘሮች፣ የራያ፣ የረአሶን፣ የኔቆዳ ዘሮች፣ የጋሴም፣ የዖዛ፣ የፋሴሐ ዘሮች፣ የቤሳይ፣ የምዑኒም፣ የንፉሰሲም ዘሮች፣ የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፣ የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፣ የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፣ የንስያና፣ የሐጢፋ ዘሮች። የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፣ የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፣ የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈክራት ሐፂቦይምና የአሞን ዘሮች። የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392 ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የመጡ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦ የዳላያ፣ የጦብያና፣ የኔቆዳ ዘሮች 642 ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል። እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ። ስለዚህ አገረ ገዥውም ኡሪምና ቱሚም የሚይዝ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው። የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤ ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው። 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣ 435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው። አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ። ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 ምናን ብር ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 ምናን ብርና 67 ልብሰ ተክህኖ ነበር። ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።

ነህምያ 7:4-73 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፥ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር። አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፥ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከነሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከሚስጴሬት፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቁጥር ይህ ነው፥ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት። የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። የኤራ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት። ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት። የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። የዛቱዕ ልጆች፥ ስምንት መቶ አርባ አምስት። የዘካይ ልጆች፥ ሰባት መቶ ስድሳ። የቢንዊ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት። የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት። የዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት። የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት። የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት። የዓዲን ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ አምስት። የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። የሐሱም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት። የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ አራት። የሐሪፍ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት። የገባዖን ልጆች፥ ዘጠና አምስት። የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች፥ መቶ ሰማንያ ስምንት። የዓናቶች ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። የቤትዓዝሞት ሰዎች፥ አርባ ሁለት። የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። የራማና የጌባ ሰዎች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ መቶ ሃያ ሦስት። የሁለተኛው ናባው ሰዎች፥ አምሳ ሁለት። የሁለተኛው ኤላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አንድ። የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ። ካህናቱ፥ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት። የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት። ሌዋውያኑ፥ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት። መዘምራኑ፥ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ አርባ ስምንት። በረኞቹ፥ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ መቶ ሠላሳ ስምንት። ናታኒም የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጣብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥ የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥ የአጋባ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥ የቤሳይ ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የንፉሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥ የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች። የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች፥ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈከራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች። ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፥ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፥ የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። ከካህናቱም የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች። እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፥ ከክህነትም ተከለከሉ። ሐቴርሰታም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም አላቸው። ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፥ ሁለቱ መቶም አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ። ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ። የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ። ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

ነህምያ 7:4-73 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ኢየሩሳሌም ታላቅና ሰፊ ከተማ ሆና ነበር፤ ነገር ግን የሚኖርባት ሕዝብ ቊጥር አነስተኛ ነበር፤ ገና ብዙ ቤቶችም አልተሠሩባትም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡንና መሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖችን እንድሰበስብና የቤተሰባቸውን የትውልድ ሐረግ አመዘጋገብ እንድቈጣጠር አነሣሣኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ የተመለሱትንም ምርኮኞች የትውልድ ሐረግ ማስረጃ መዝገብ አገኘሁ፤ ያገኘሁትም ማስረጃ ከዚህ የሚከተለው ነበር። ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር። ሲመለሱም መሪዎቻቸው ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ዐዛርያ፥ ረዓምያ፥ ናሐማኒ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፔሬት፥ ቢግዋይ፥ ነሑምና በዓና ናቸው። ከምርኮ ከተመለሱት ከእያንዳንዱ ጐሣ ተወጣጥተው የተመዘገቡት የእስራኤል ጐሣዎችና የትውልዳቸው ብዛት ይህ ነው፦ ከፓርዖሽ ወገን የተመዘገቡ 2172 ከሸፋጥያ ወገን የተመዘገቡ 372 ከአራሕ ወገን የተመዘገቡ 652 የኢያሱና የኢዮአብ ትውልድ ጐሣ ከሆነው ከፓሐትሞአብ ወገን የተመዘገቡ 2818 ከዔላም ወገን የተመዘገቡ 1254 ከዛቱ ወገን የተመዘገቡ 845 ከዛካይ ወገን የተመዘገቡ 760 ከቢኑይ ወገን የተመዘገቡ 648 ከቤባይ ወገን የተመዘገቡ 628 ከዓዝጋድ ወገን የተመዘገቡ 2322 ከአዶኒቃም ወገን የተመዘገቡ 667 ከቢግዋይ ወገን የተመዘገቡ 2067 ከዓዲን ወገን የተመዘገቡ 655 ሕዝቅያስ ተብሎ ከሚጠራው ከአጤር ወገን የተመዘገቡ 98 ከሐሹም ወገን የተመዘገቡ 328 ከቤጻይ ወገን የተመዘገቡ 324 ከሐሪፍ ወገን የተመዘገቡ 112 ከገባዖን ወገን የተመዘገቡ 95 የቀድሞ አባቶቻቸው ከዚህ በሚከተሉት ከተሞች የሚኖሩም ከምርኮ ተመልሰዋል፦ በቤተልሔምና በነጦፋ የሚኖሩ 188 በዐናቶት የሚኖሩ 128 በቤት ዓዝማዌት የሚኖሩ 42 በቂርያትይዓሪም፥ በከፊራና በበኤሮት የሚኖሩ 743 በራማና በጌባዕ የሚኖሩ 621 በሚክማስ የሚኖሩ 122 በቤትኤልና በዐይ የሚኖሩ 123 በሁለተኛይቱ ነቦ የሚኖሩ 52 በሁለተኛይቱ ዔላም የሚኖሩ 1254 በሓሪም የሚኖሩ 320 በኢያሪኮ የሚኖሩ 345 በሎድ፥ በሐዲድና በኦኖ የሚኖሩ 721 በሰናአ የሚኖሩ 3930 ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ጐሣዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፦ የኢያሱ ዘር ከሆነው ከይዳዕያ ወገን 973 ከኢሜር ወገን 1052 ከፓሽሑር ወገን 1247 ከሓሪም ወገን 1017 ከምርኮ የተመለሱ ሌዋውያን ጐሣዎች፦ የሆዳውያ ዘሮች ከነበሩት ከኢያሱና ከቃድሚኤል ወገን 74 የአሳፍ ዘሮች ከሆኑት ከቤተ መቅደስ መዘምራን ወገን 148 የሻሉም፥ የአጤር፥ የጣልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሾባይ ዘሮች ከሆኑት የቤተ መቅደስ ዘበኞች ወገን 138 ከምርኮ የተመለሱ የቤተ መቅደስ ሠራተኞች፥ ዘሮች በየጐሣቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ሻልማይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ መዑኒም፥ ነፉሸሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሊት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲስራ፥ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ። ከምርኮ የተመለሱ የሰሎሞን አገልጋዮች ጐሣዎች፦ ሶጣይ፥ ሶፌሬት፥ ፐሪዳ፥ ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥ ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት ሀጸባይምና አሞን። ከምርኮ የተመለሱት የቤተ መቅደስ ሠራተኞችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ብዛት ጠቅላላ ድምር 392 ነበር። ቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ከሩብ፥ አዶንና ኢሜር ተብለው ከሚጠሩት የገጠር ከተሞች የተመለሱ የደላያ፥ የጦቢያና የነቆዳ ጐሣዎች ወገኖች የሆኑት ዘሮች ድምር 642 ነበር፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ዘሮች መሆናቸውን ለማወቅ የሚያስችል በቂ ማስረጃ አልነበራቸውም። ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች የቀድሞ አባቶቻቸውን የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ አልቻሉም፤ እነርሱም ሖባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ ናቸው፤ የካህን ወገን የሆነው የባርዚላይ የቀድሞ አባት የገለዓድ ተወላጅ ከነበረው ከባርዚላይ ወገን አንዲት ሴት አግብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ የዐማቱን ጐሣ ስም ወርሶ ይኖር ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻቸውንም የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ ካለመቻላቸው የተነሣ፥ በክህነት ለማገልገል አልተፈቀደላቸውም። ስለዚህም የይሁዳ ገዥ በኡሪምና በቱሚም የሚያገለግል ካህን እስከሚነሣበት ጊዜ ድረስ ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ከሚቀርበው ቊርባን መመገብ የማይችሉ መሆናቸውን ነገራቸው። ከምርኮ የተመለሰው ሕዝብ ጠቅላላ ድምር 42360 የወንዶችና የሴቶች አገልጋዮቻቸው ቊጥር 7337 የወንዶችና የሴቶች መዘምራናቸው ቊጥር 245 የፈረሶቻቸው ብዛት 736 የበቅሎዎቻቸው ብዛት 245 የግመሎቻቸው ብዛት 435 የአህዮቻቸው ብዛት 6720 ነበር። አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎችም ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመሥራት የሚረዳ አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ ከእነርሱም መካከል፥ አገረ ገዢው፦ 8 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 50 ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ 530 የካህናት ልብሶችን ሰጠ። የጐሣ አለቆችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1250 ኪሎ የሚመዝን ብር ሰጡ፤ የቀሩት ሰዎችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1100 ኪሎ የሚመዝን ብርና 67 የካህናት ልብሶችን ሰጥተዋል። ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።