የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 7

7
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተ​ሠራ በኋላ፥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አቆ​ምሁ፤ በረ​ኞ​ቹ​ንና መዘ​ም​ራ​ኑን፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ሾምሁ፤ 2ወን​ድ​ሜን ሃና​ኒ​ንና የግ​ን​ቡን አለቃ ሐና​ን​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ሾም​ኋ​ቸው፤ እር​ሱም እው​ነ​ተኛ ከሌ​ሎ​ቹም ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ነበረ። 3እኔም፥ “ፀሐይ እስ​ኪ​ሞቅ ድረስ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች አይ​ከ​ፈቱ፤ እነ​ር​ሱም ቆመው ሳሉ ደጆ​ቹን ይዝጉ፤ ይቈ​ል​ፉም፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሰዎች አን​ዳ​ን​ዱን በየ​ተ​ራው፥ አን​ዳ​ን​ዱ​ንም በየ​ቤቱ አን​ጻር ጠባ​ቂ​ዎ​ችን አስ​ቀ​ምጡ” አል​ኋ​ቸው። 4ከተ​ማ​ዪ​ቱም ሰፊና ታላቅ ነበ​ረች፤ በው​ስ​ጥዋ የነ​በሩ ሕዝብ ግን ጥቂ​ቶች ነበሩ፤ ቤቶ​ቹም ገና አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር።
ከስ​ደት የተ​መ​ለሱ አይ​ሁድ ስም ዝር​ዝር
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቤ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እቈ​ጥ​ራ​ቸው ዘንድ ልቤን አነ​ሣሣ፤ አስ​ቀ​ድ​መው የመ​ጡ​ት​ንም ሰዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐ​ፋ​ቸ​ውን አገ​ኘሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ደ​ዚህ ተጽፎ አገ​ኘሁ። 6የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። 7ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከአ​ዛ​ር​ያስ፥ ከረ​ዓ​ምያ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዳዕ​ምያ” ይላል። ከሄ​ሜ​ኔስ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ል​ሰማ፥ ከሚ​ስ​ፌ​ሬት፥ ከዕ​ዝራ፥#“ከዕ​ዝራ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ከበ​ጉ​ዋይ፥ ከነ​ሑም፥ ከበ​ዓና፥ ከመ​ስ​ፈር#“ከመ​ስ​ፈር” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ጋር መጡ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ የወ​ን​ዶች ቍጥር ይህ ነው፥
8የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ አንድ መቶ#ግእዝ “ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰባ ሁለት” ይላል። ሰባ ሁለት። 9የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 10የኤራ ልጆች ስድ​ስት መቶ አምሳ ሁለት። 11ከኢ​ያ​ሱና ከኢ​ዮ​አብ ልጆች የሆኑ የፈ​ሐት ሞዓብ ልጆች ሁለት ሺህ ስም​ንት መቶ ዐሥራ ስም​ንት። 12የኤ​ላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 13የዘ​ቱዕ ልጆች ስም​ንት መቶ አርባ አም​ስት። 14የዘ​ካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። 15የበ​ኑይ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ስም​ንት። 16የቤ​ባይ ልጆች ስድ​ስት መቶ ሃያ ስም​ንት። 17የአ​ዝ​ጌድ ልጆች ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ሁለት። 18የአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስድ​ስት መቶ ስድሳ ሰባት። 19የበ​ጉ​ዋይ ልጆች ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት። 20የዓ​ዴን ልጆች ስድ​ስት መቶ አምሳ አም​ስት። 21የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ወገን የአ​ጤር ልጆች ዘጠና ስም​ንት። 22የሐ​ሱም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ ስም​ንት። 23የቤ​ሳይ ልጆች ሦስት መቶ ሃያ አራት። 24የሐ​ሪፍ ልጆች መቶ ዐሥራ ሁለት።#አን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ዘርዕ “የአ​ሴን ልጆች ሁለት መቶ ሃያ ሦስት” የሚል ይጨ​ም​ራል። 25የገ​ባ​ዖን ልጆች ዘጠና አም​ስት። 26የቤተ ልሔ​ምና የነ​ጦ​ፍያ ሰዎች መቶ ሰማ​ንያ ስም​ንት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ሰባ ዘጠኝ” ይላል። 27የዓ​ና​ቶት ሰዎች መቶ ሃያ ስም​ንት። 28የቤ​ት​አ​ዝ​ሞት ሰዎች አርባ ሁለት። 29የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምና የቃ​ፌር፥ የቤ​ሮ​ትም ሰዎች ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 30የሐ​ራ​ማና የገ​ቢኣ ሰዎች ስድ​ስት መቶ ሃያ አንድ። 31የማ​ኬ​ማስ ሰዎች መቶ ሃያ ሁለት። 32የቤ​ቴ​ልና የጋይ ሰዎች መቶ ሃያ ሦስት። 33የና​ብያ ሰዎች መቶ አምሳ ሁለት።#ዕብ. “የሁ​ለ​ተ​ኛው ናብያ ሰዎች አምሳ ሁለት” ይላል። 34የኤ​ላም ሰዎች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሺህ ሁለት መቶ አምሳ ሁለት” ይላል። 35የኤ​ራም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ። 36የኢ​ያ​ሪኮ ልጆች ሦስት መቶ አርባ አም​ስት። 37የሎ​ድና ሐዲድ የሐ​ኖም ልጆች ሰባት መቶ ሃያ አንድ። 38የሴ​ናዓ ልጆች ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።
39ካህ​ናቱ ከኢ​ያሱ ወገን፦ የዮ​ዳሔ ልጆች ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 40የኤ​ሜር ልጆች ሺህ አምሳ ሁለት። 41የፋ​ስ​ኮር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 42የሐ​ራም ልጆች ሺህ ዐሥራ ሰባት።
43ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከሆ​ዳ​ይዋ ወገን የኢ​ያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች ሰባ አራት። 44መዘ​ም​ራኑ የአ​ሳፍ ልጆች መቶ አርባ ስም​ንት። 45በረ​ኞቹ የሴ​ሎ​ምያ ልጆች፥ የአ​ጤር ልጆች፥ የጤ​ል​ማና ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥ የሐ​ጢጣ ልጆች፥ የሶ​ባይ ልጆች መቶ አርባ ስም​ንት።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ሠላሳ ስም​ንት” ይላል።
46ናታ​ኒም የሲአ ልጆች፥ የሐ​ሡፋ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዓት ልጆች፤ 47የቄ​ራስ ልጆች፥ የአ​ሲያ ልጆች፥ የፋ​ዶን ልጆች፤ 48የል​ባና ልጆች፥ የአ​ጋባ ልጆች፥ የሰ​ል​ማይ ልጆች፤ 49የሐ​ናን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፥ የጋ​ኤር ልጆች፤ 50የር​አያ ልጆች፥ የረ​አ​ሶን ልጆች፥ የኔ​ቆዳ ልጆች፤ 51የጋ​ሴም ልጆች፥ የኡዚ ልጆች፥ የፋ​ሴሓ ልጆች፤ 52የቤ​ሳይ ልጆች፥ የም​ዑ​ና​ው​ያን ልጆች፥ የኔ​ፋ​ሴ​ስም ልጆች፤ 53የበ​ቅ​ቡቅ ልጆች፥ የሐ​ቀፋ ልጆች፥ የሐ​ሩር ልጆች፤ 54የበ​ስ​ሎት ልጆች፥ የም​ሒዳ ልጆች፥ የሐ​ርሳ ልጆች፤ 55የበ​ር​ቆስ ልጆች፥ የሲ​ሣራ ልጆች፥ የታ​ማህ ልጆች፥ 56የነ​ስያ ልጆች፥ የሐ​ጤፋ ልጆች።
57የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሦ​ጠይ ልጆች፥ የሰ​ፋ​ሬት ልጆች፥ የፈ​ሪዳ ልጆች፥ 58የየ​ዕላ ልጆች፥ የደ​ር​ቆን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፤ 59የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች፥ የሐ​ጢል ልጆች፥ የፈ​ከ​ራት ልጆች፥ የሰ​ባ​ይም ልጆች፥ የአ​ሞን ልጆች። 60ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
61ከቲ​ል​ሜል፥ ከቲ​ላ​ሬስ፥ ከኪ​ሩብ፥ ከአ​ዶን፥ ከኢ​ሜር የወጡ እነ​ዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶ​ችና ዘራ​ቸ​ውን ወይም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን መሆ​ና​ቸ​ውን ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ 62የዳ​ላያ ልጆች፥ የጦ​ብያ ልጆች፥ የኔ​ቆዳ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ሁለት። 63ከካ​ህ​ና​ቱም የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ሙም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች። 64እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ። 65ሐቴ​ር​ሰ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።
66ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ 67ይኸ​ውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነ​በሩ ከሎ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውና ከገ​ረ​ዶ​ቻ​ቸው ሌላ ሁለት መቶም አርባ አም​ስት ወን​ዶች መዘ​ም​ራ​ንና ሴቶች መዘ​ም​ራት ነበ​ሩ​አ​ቸው። 68ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድ​ስት፥ በቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሁለት መቶ አርባ አም​ስት፤ 69ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አራት መቶ ሠላሳ አም​ስት፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ስድ​ስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ነበሩ።
70ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴ​ር​ሰ​ታም አንድ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪክ፥ አም​ሳም ድስ​ቶች፥ አም​ስት መቶ ሠላ​ሳም የካ​ህ​ናት ልብስ በቤተ መዛ​ግ​ብት ውስጥ ሰጠ። 71ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ዐያ​ሌ​ዎቹ በሥ​ራው ቤተ መዛ​ግ​ብት ውስጥ ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ። 72የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ የሰ​ጡት ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪ​ክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባ​ትም የካ​ህ​ናት ልብስ ነበረ።
73ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም ዐያ​ሌ​ዎቹ፥ ናታ​ኒ​ምም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ