መጽሐፈ ነህምያ 7
7
1እነሆ የቅጽሩ ግንብ ተሠርቶ አለቀ፤ የቅጽር በሮችም ሁሉ በየቦታቸው ተገጣጥመው ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁ ዘበኞች ለመዘምራን ቡድን አባላትና ለሌሎችም ሌዋውያን የሥራ ድርሻቸው ተመድቦላቸው ነበር። 2እኔም የኢየሩሳሌምን ከተማ ያስተዳድሩ ዘንድ ሁለት ሰዎችን ሾምኩ፤ እነርሱም የእኔ ወንድም የሆነው ሐናኒና የምሽግ ኀላፊ የነበረው ሐናንያ ናቸው፤ ሐናንያ እውነተኛና እግዚአብሔርን በመፍራት ረገድ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሰው ነበር። 3ለእነርሱም የሰጠኋቸው መመሪያ የኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ እንዳይከፈቱ፥ ደግሞ ማታ ፀሐይ ስትጠልቅ የዘብ ጠባቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት የቅጽር በሮቹ በቊልፍና በመወርወሪያ አጥብቀው እንዲዘጉአቸው ነበር። እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል ሰዎችን ቀጥረው ከፊሎቹ በሥራቸው ላይ ሆነው ሌሎቹ ደግሞ በየቤታቸው ፊት ለፊት ሆነው እንዲጠብቁ አዘዝኳቸው።
ከምርኮ የተመለሱ ሰዎች ስም ዝርዝር
4ኢየሩሳሌም ታላቅና ሰፊ ከተማ ሆና ነበር፤ ነገር ግን የሚኖርባት ሕዝብ ቊጥር አነስተኛ ነበር፤ ገና ብዙ ቤቶችም አልተሠሩባትም፤ 5እግዚአብሔርም ሕዝቡንና መሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖችን እንድሰበስብና የቤተሰባቸውን የትውልድ ሐረግ አመዘጋገብ እንድቈጣጠር አነሣሣኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ የተመለሱትንም ምርኮኞች የትውልድ ሐረግ ማስረጃ መዝገብ አገኘሁ፤ ያገኘሁትም ማስረጃ ከዚህ የሚከተለው ነበር።
6ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር። 7ሲመለሱም መሪዎቻቸው ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ዐዛርያ፥ ረዓምያ፥ ናሐማኒ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፔሬት፥ ቢግዋይ፥ ነሑምና በዓና ናቸው።
8-25ከምርኮ ከተመለሱት ከእያንዳንዱ ጐሣ ተወጣጥተው የተመዘገቡት የእስራኤል ጐሣዎችና የትውልዳቸው ብዛት ይህ ነው፦
ከፓርዖሽ ወገን የተመዘገቡ 2172
ከሸፋጥያ ወገን የተመዘገቡ 372
ከአራሕ ወገን የተመዘገቡ 652
የኢያሱና የኢዮአብ ትውልድ ጐሣ ከሆነው ከፓሐትሞአብ ወገን የተመዘገቡ 2818
ከዔላም ወገን የተመዘገቡ 1254
ከዛቱ ወገን የተመዘገቡ 845
ከዛካይ ወገን የተመዘገቡ 760
ከቢኑይ ወገን የተመዘገቡ 648
ከቤባይ ወገን የተመዘገቡ 628
ከዓዝጋድ ወገን የተመዘገቡ 2322
ከአዶኒቃም ወገን የተመዘገቡ 667
ከቢግዋይ ወገን የተመዘገቡ 2067
ከዓዲን ወገን የተመዘገቡ 655
ሕዝቅያስ ተብሎ ከሚጠራው ከአጤር ወገን የተመዘገቡ 98
ከሐሹም ወገን የተመዘገቡ 328
ከቤጻይ ወገን የተመዘገቡ 324
ከሐሪፍ ወገን የተመዘገቡ 112
ከገባዖን ወገን የተመዘገቡ 95
26-38የቀድሞ አባቶቻቸው ከዚህ በሚከተሉት ከተሞች የሚኖሩም ከምርኮ ተመልሰዋል፦
በቤተልሔምና በነጦፋ የሚኖሩ 188
በዐናቶት የሚኖሩ 128
በቤት ዓዝማዌት የሚኖሩ 42
በቂርያትይዓሪም፥ በከፊራና በበኤሮት የሚኖሩ 743
በራማና በጌባዕ የሚኖሩ 621
በሚክማስ የሚኖሩ 122
በቤትኤልና በዐይ የሚኖሩ 123
በሁለተኛይቱ ነቦ የሚኖሩ 52
በሁለተኛይቱ ዔላም የሚኖሩ 1254
በሓሪም የሚኖሩ 320
በኢያሪኮ የሚኖሩ 345
በሎድ፥ በሐዲድና በኦኖ የሚኖሩ 721
በሰናአ የሚኖሩ 3930
39-42ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ጐሣዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፦
የኢያሱ ዘር ከሆነው ከይዳዕያ ወገን 973
ከኢሜር ወገን 1052
ከፓሽሑር ወገን 1247
ከሓሪም ወገን 1017
43-45ከምርኮ የተመለሱ ሌዋውያን ጐሣዎች፦
የሆዳውያ ዘሮች ከነበሩት ከኢያሱና ከቃድሚኤል ወገን 74
የአሳፍ ዘሮች ከሆኑት ከቤተ መቅደስ መዘምራን ወገን 148
የሻሉም፥ የአጤር፥ የጣልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሾባይ ዘሮች ከሆኑት የቤተ መቅደስ ዘበኞች ወገን 138
46-56ከምርኮ የተመለሱ የቤተ መቅደስ ሠራተኞች፥ ዘሮች በየጐሣቸው፦
ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥
ቄሮስ፥ ሲዓ፥ ፋዶን፥
ለባና፥ ሐጋባ፥ ሻልማይ፥
ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥
ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥
ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥
ቤሳይ፥ መዑኒም፥ ነፉሸሲም፥
ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥
ባጽሊት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥
ባርቆስ፥ ሲስራ፥ ቴማሕ፥
ነጺሐና ሐጢፋ።
57-59ከምርኮ የተመለሱ የሰሎሞን አገልጋዮች ጐሣዎች፦
ሶጣይ፥ ሶፌሬት፥ ፐሪዳ፥
ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥
ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት
ሀጸባይምና አሞን።
60ከምርኮ የተመለሱት የቤተ መቅደስ ሠራተኞችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ብዛት ጠቅላላ ድምር 392 ነበር።
61-62ቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ከሩብ፥ አዶንና ኢሜር ተብለው ከሚጠሩት የገጠር ከተሞች የተመለሱ የደላያ፥ የጦቢያና የነቆዳ ጐሣዎች ወገኖች የሆኑት ዘሮች ድምር 642 ነበር፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ዘሮች መሆናቸውን ለማወቅ የሚያስችል በቂ ማስረጃ አልነበራቸውም።
63-64ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች የቀድሞ አባቶቻቸውን የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ አልቻሉም፤ እነርሱም ሖባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ ናቸው፤ የካህን ወገን የሆነው የባርዚላይ የቀድሞ አባት የገለዓድ ተወላጅ ከነበረው ከባርዚላይ ወገን አንዲት ሴት አግብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ የዐማቱን ጐሣ ስም ወርሶ ይኖር ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻቸውንም የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ ካለመቻላቸው የተነሣ፥ በክህነት ለማገልገል አልተፈቀደላቸውም። 65ስለዚህም የይሁዳ ገዥ በኡሪምና በቱሚም የሚያገለግል ካህን እስከሚነሣበት ጊዜ ድረስ ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ከሚቀርበው ቊርባን መመገብ የማይችሉ መሆናቸውን ነገራቸው። #ዘፀ. 28፥30፤ ዘዳ. 33፥8።
66-69ከምርኮ የተመለሰው ሕዝብ ጠቅላላ ድምር 42360
የወንዶችና የሴቶች አገልጋዮቻቸው ቊጥር 7337
የወንዶችና የሴቶች መዘምራናቸው ቊጥር 245
የፈረሶቻቸው ብዛት 736
የበቅሎዎቻቸው ብዛት 245
የግመሎቻቸው ብዛት 435
የአህዮቻቸው ብዛት 6720 ነበር።
70-72አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎችም ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመሥራት የሚረዳ አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ ከእነርሱም መካከል፥
አገረ ገዢው፦ 8 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 50 ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ 530 የካህናት ልብሶችን ሰጠ።
የጐሣ አለቆችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1250 ኪሎ የሚመዝን ብር ሰጡ፤
የቀሩት ሰዎችም፦ 168 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 1100 ኪሎ የሚመዝን ብርና 67 የካህናት ልብሶችን ሰጥተዋል።
73ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ። #1ዜ.መ. 9፥2፤ ነህ. 11፥3።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 7: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997