መጽሐፈ ነህምያ 7
7
1እንዲህም ሆነ፥ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥ 2ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፥ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። 3እኔም፦ ፀሀይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፥ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፥ ይቈልፉም፥ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቆችን አስቀምጡ አልኋቸው። 4ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፥ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር። 5አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፥ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ። 6የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። 7ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከነሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከሚስጴሬት፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና ጋር መጡ።
8የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቁጥር ይህ ነው፥ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት። 9የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 10የኤራ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት። 11ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት። 12የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 13የዛቱዕ ልጆች፥ ስምንት መቶ አርባ አምስት። 14የዘካይ ልጆች፥ ሰባት መቶ ስድሳ። 15የቢንዊ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት። 16የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት። 17የዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት። 18የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት። 19የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት። 20የዓዲን ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ አምስት። 21የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። 22የሐሱም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት። 23የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ አራት። 24የሐሪፍ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት። 25የገባዖን ልጆች፥ ዘጠና አምስት። 26የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች፥ መቶ ሰማንያ ስምንት። 27የዓናቶች ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። 28የቤትዓዝሞት ሰዎች፥ አርባ ሁለት። 29የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 30የራማና የጌባ ሰዎች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። 31የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። 32የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ መቶ ሃያ ሦስት። 33የሁለተኛው ናባው ሰዎች፥ አምሳ ሁለት። 34የሁለተኛው ኤላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 35የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። 36የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት 37የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አንድ። 38የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።
39ካህናቱ፥ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 40የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት። 41የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 42የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት።
43ሌዋውያኑ፥ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
44መዘምራኑ፥ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ አርባ ስምንት።
45በረኞቹ፥ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ መቶ ሠላሳ ስምንት።
46ናታኒም የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ 47የጣብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥ 48የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥ 49የአጋባ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ 50የራያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ 51የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥ 52የቤሳይ ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ 53የንፉሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ 54የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥ 55የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥ 56የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
57የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች፥ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ 58የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ 59የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈከራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች። 60ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
61ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፥ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፥ 62የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። 63ከካህናቱም የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች። 64እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፥ ከክህነትም ተከለከሉ። 65ሐቴርሰታም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም አላቸው።
66-67ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፥ ሁለቱ መቶም አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። 68ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ 69ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
70ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። 71ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ። 72የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ።
73ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 7: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ