የሉ​ቃስ ወን​ጌል 12

12
ስለ ፈሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ
1 # ማቴ. 16፥6፤ ማር. 8፥15። በዚ​ያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እስ​ኪ​ረ​ጋ​ገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ ተጠ​በቁ፤ ይኸ​ውም ግብ​ዝ​ነት ነው። 2#ማር. 4፥22፤ ሉቃ. 8፥17። የማ​ይ​ገ​ለጥ የተ​ሰ​ወረ፥ የማ​ይ​ታ​ይም የተ​ሸ​ሸገ የለ​ምና። 3በጨ​ለማ የም​ት​ና​ገ​ሩት በብ​ር​ሃን ይሰ​ማል፤ በእ​ል​ፍ​ኝም ውስጥ በጆሮ የም​ት​ን​ሾ​ካ​ሾ​ኩት በሰ​ገ​ነት ይሰ​በ​ካል። 4ለእ​ና​ንተ ለወ​ዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሥጋ​ች​ሁን የሚ​ገ​ድ​ሉ​ትን አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ከዚ​ህም የበ​ለጠ ማድ​ረግ የሚ​ች​ሉት የላ​ቸ​ውም። 5ነገር ግን፤ የም​ት​ፈ​ሩ​ትን አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተስ ከገ​ደለ በኋላ ወደ ገሃ​ነም ሊጥል ሥል​ጣን ያለ​ውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ሱን ፍሩ። 6አም​ስት ወፎች በሁ​ለት ሻሚ መሐ​ለቅ ይሸጡ የለ​ምን? ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ስን​ኳን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አት​ረ​ሳም። 7የእ​ና​ን​ተስ የራስ ጠጕ​ራ​ችሁ ሁሉ የተ​ቈ​ጠረ ነው፤ እን​ግ​ዲህ አት​ፍሩ፤ ከብዙ ወፎች እና​ንተ ትበ​ል​ጣ​ላ​ች​ሁና።
8“እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ በሰው ፊት የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝን ሁሉ እኔም#በግ​ሪኩ “የሰው ልጅም ...” ይላል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት አም​ነ​ዋ​ለሁ። 9በሰው ፊት የሚ​ክ​ደ​ኝን ግን እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት እክ​ደ​ዋ​ለሁ። 10#ማቴ. 12፥32፤ ማር. 3፥29። በሰው ልጅ ላይ የስ​ድብ ቃል የሚ​ና​ገር ሁሉ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ላይ የስ​ድብ ቃል የሚ​ና​ገር ግን በዚህ ዓለ​ምም ሆነ በሚ​መ​ጣው ዓለም#“በዚህ ዓለ​ምም ሆነ በሚ​መ​ጣው ዓለም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አይ​ሰ​ረ​ይ​ለ​ትም። 11ወደ አደ​ባ​ባይ#በግ​ሪኩ ወደ ምኵ​ራብ” ይላል። ወደ ሹሞ​ቹና ወደ ነገ​ሥ​ታቱ፥ ወደ መኳ​ን​ን​ቱም በሚ​ወ​ስ​ዱ​አ​ችሁ ጊዜ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን አታ​ስቡ። 12ያን​ጊዜ በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ና​ገ​ረው መን​ፈስ ቅዱስ ነውና።”
ርስት ሊካ​ፈል ስለ ወደ​ደው ሰው
13ከሕ​ዝ​ቡም አንዱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ርስ​ቴን እን​ዲ​ያ​ካ​ፍ​ለኝ ለወ​ን​ድሜ ንገ​ረው” አለው። 14ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው። 15“ዕወቁ፤ ከቅ​ሚ​ያም ሁሉ ተጠ​በቁ፤ ሰው የሚ​ድን ገን​ዘብ በማ​ብ​ዛት አይ​ደ​ለ​ምና” አላ​ቸው።
እር​ሻው ስለ በጀ​ለት ባለ​ጸጋ
16ምሳ​ሌም መሰ​ለ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፤ “እር​ሻው የበ​ጀ​ለ​ትና ሀገር የተ​መ​ቸው#“ሀገር የተ​መ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ። 17እህ​ሌን የማ​ኖ​ር​በት የለ​ኝ​ምና ምን ላድ​ርግ ብሎ በልቡ ዐሰበ። 18እር​ሱም አለ፦ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጎተ​ራ​ዬን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ጎተ​ራም እሠ​ራ​ለሁ፤ እህ​ሌ​ንና በረ​ከ​ቴ​ንም በዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ። 19ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዲህ እላ​ታ​ለሁ፦ ሰው​ነቴ ሆይ፥ የሰ​በ​ሰ​ብ​ሁ​ልሽ ለብዙ ዓመ​ታት የሚ​በ​ቃሽ የደ​ለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበ​ልሽ። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ከሥ​ጋህ ለይ​ተው ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ ያጠ​ራ​ቀ​ም​ኸው ለማን ይሆ​ናል? አለው። 21ሀብ​ትን ለራሱ የሚ​ሰ​በ​ስብ፤ ሀብ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ሆነ እን​ዲሁ ነው።”
በከ​ንቱ መጨ​ነቅ ስለ​ማ​ይ​ገባ
22ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ። 23ነፍስ ከም​ግብ ትበ​ል​ጣ​ለ​ችና፤ ሰው​ነ​ትም ከል​ብስ ይበ​ል​ጣ​ልና። 24የማ​ይ​ዘ​ሩ​ት​ንና የማ​ያ​ጭ​ዱ​ትን፥ ጎተ​ራና ጕድ​ጓድ የሌ​ላ​ቸ​ውን የቍ​ራ​ዎ​ችን ጫጭ​ቶች#“ጫጭ​ቶች” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም። ተመ​ል​ከቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ይመ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ከወ​ፎች እን​ዴት እጅግ አት​በ​ል​ጡም? 25ከእ​ና​ን​ተስ ዐስቦ በቁ​መቱ ላይ አንድ ክንድ መጨ​መር የሚ​ቻ​ለው ማነው? 26ይህን ቀላ​ሉን የማ​ት​ችሉ ከሆነ በሌ​ላው ለምን ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ? 27#1ነገ. 10፥4-7፤ 2ዜ.መ. 9፥3-6። እነሆ፥ አበ​ባ​ዎ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ድጉ ተመ​ል​ከቱ፤ አይ​ፈ​ት​ሉም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ነገር ግን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሰሎ​ሞን እንኳ በክ​ብሩ ዘመን #“ዘመን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ አል​ለ​በ​ሰም። 28እነሆ፥ ዛሬ ያለ​ውን፥ ነገም ወደ እሳት የሚ​ጣ​ለ​ውን የአ​በባ አገዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ከሆነ፥ እና​ንተ እም​ነት የጐ​ደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተማ እን​ዴት አብ​ልጦ አያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ? 29እና​ን​ተም የም​ት​በ​ሉ​ት​ንና የም​ት​ጠ​ጡ​ትን አት​ፈ​ልጉ፤ ወዲ​ያና ወዲ​ህም አት​በሉ፤ አት​ጨ​ነ​ቁ​ለ​ትም። 30ይህን ሁሉ በውጭ ያሉ የዓ​ለም አሕ​ዛብ ይሹ​ታ​ልና፤ ለእ​ና​ን​ተስ አባ​ታ​ችሁ ይህን ሁሉ እን​ደ​ም​ት​ሹት ያው​ቃል። 31ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥ​ትና ጽድቅ ሹ፤ ይህም ሁሉ ይጨ​መ​ር​ላ​ች​ኋል።
32“አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና። 33ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ። 34መዝ​ገ​ባ​ችሁ ካለ​በት ልባ​ችሁ በዚያ ይኖ​ራ​ልና።
ስለ መት​ጋት
35 # ማቴ. 25፥1-13። “ወገ​ባ​ችሁ የታ​ጠቀ መብ​ራ​ታ​ች​ሁም የበራ ይሁን። 36#ማር. 13፥34-36። እና​ን​ተም፥ በመ​ጣና በር በመታ ጊዜ ወዲ​ያው ይከ​ፍ​ቱ​ለት ዘንድ ከሰ​ርግ እስ​ኪ​መ​ለስ ጌታ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ሰዎች ሁኑ። 37ጌታ​ቸው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ር​ጉና ሲተጉ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው፤ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወገ​ቡን ታጥቆ በማ​ዕድ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤ እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸ​ዋል። 38ከሌ​ሊቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወይም በሦ​ስ​ተ​ኛው ክፍል ቢመ​ጣና እን​ዲሁ ቢያ​ገ​ኛ​ቸው እነ​ዚያ አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው። 39#ማቴ. 24፥43-44። ነገር ግን ይህን ዕወቁ፤ ባለ​ቤት ሌባ የሚ​መ​ጣ​በ​ትን ጊዜ ቢያ​ውቅ ተግቶ በጠ​በቀ፥ ቤቱ​ንም እን​ዲ​ቈ​ፍ​ሩት ባል​ፈ​ቀ​ደም ነበር። 40እና​ን​ተም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ ባል​ጠ​ረ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ሰዓት ይመ​ጣ​ልና።” 41ጴጥ​ሮ​ስም፥ “አቤቱ፥ ይህን ምሳሌ የም​ት​ና​ገ​ረው ለእኛ ነውን? ወይስ ለሁሉ ነው?” አለው። 42ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታው በቤ​ተ​ሰቡ ላይ የሚ​ሾ​መው ደግ#“ደግ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ታማ​ኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን? 43ጌታው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ርግ የሚ​ያ​ገ​ኘው አገ​ል​ጋይ ብፁዕ ነው። 44እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ በሀ​ብቱ ሁሉ ላይ ይሾ​መ​ዋል፤ 45ነገር ግን ያ ክፉ አገ​ል​ጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይ​መ​ጣም ቢል፥ በጌ​ታው ቤት ያሉ​ት​ንም ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮች ሊደ​በ​ድ​ብና ሊያ​ጕ​ላላ ቢጀ​ምር፥ ከሰ​ካ​ራ​ሞ​ችም ጋር ቢበ​ላና ቢጠጣ፥ ቢሰ​ክ​ርም፥ 46የዚያ አገ​ል​ጋይ ጌታ ባል​ጠ​ረ​ጠ​ረው ዕለት፥ ባላ​ወ​ቀ​ውም ሰዓት መጥቶ ከሁ​ለት ይሰ​ነ​ጥ​ቀ​ዋል፤ ዕድ​ሉ​ንም ከማ​ይ​ታ​መኑ ጋር ያደ​ር​ገ​ዋል። 47የጌ​ታ​ውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማ​ይ​ሠ​ራና የማ​ያ​ዘ​ጋጅ የዚያ አገ​ል​ጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው። 48ያላ​ወቀ ግን ባይ​ሠ​ራም ቅጣቱ ጥቂት ነው፤ ብዙ ከሰ​ጡት ብዙ ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና። ጥቂት ከሰ​ጡ​ትም ጥቂት ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና።#በግ​ሪኩ እና አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ብዙ አደራ ከተ​ሰ​ጠው ከእ​ርሱ አብ​ዝ​ተው ይሹ​በ​ታል” ይላል።
ስለ ሰይ​ፍና ስለ መለ​ያ​የት
49“በም​ድር ላይ እሳ​ትን አም​ጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ን​ደድ በቀር ምን እሻ​ለሁ? 50#ማር. 10፥38። ነገር ግን፤ የም​ጠ​መ​ቃት ጥም​ቀት አለ​ችኝ፤ እስ​ክ​ፈ​ጽ​ማ​ትም ድረስ እጅግ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።” 51ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለም​ድር ሰላ​ምን ያመ​ጣሁ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን? እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አይ​ደ​ለም፤ ሰይ​ፍ​ንና#በግ​ሪኩ “ሰይ​ፍን” የሚል የለም። መለ​ያ​የ​ትን ነው እንጂ። 52ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ አም​ስት ሰዎች በአ​ንድ ቤት ቢኖሩ ሦስቱ ከሁ​ለቱ፥ ሁለ​ቱም ከሦ​ስቱ ይለ​ያሉ፤#በግ​ሪኩ እና በብዙ የግ​እዝ ዘርዕ “አን​ዱም ከሌ​ላው ይለ​ያል” የሚል ይጨ​ም​ራል። 53#ሚክ. 7፥6። አባት ከልጁ፥ ልጅም ከአ​ባቱ ይለ​ያል፤ እናት ከል​ጅዋ፥ ልጅም ከእ​ናቷ ትለ​ያ​ለች፤ አማት ከም​ራቷ፥ ምራ​ትም ከአ​ማቷ ትለ​ያ​ለች።”
54ከዚ​ህም በኋላ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ደመና በም​ዕ​ራብ በኩል ደምኖ ባያ​ችሁ ጊዜ ‘ዝናም ይመ​ጣል’ ትላ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ይሆ​ናል። 55የአ​ዜብ ነፋስ በነ​ፈሰ ጊዜም ‘ድርቅ ይሆ​ናል፤’ ትላ​ላ​ችሁ እን​ዲ​ሁም ይሆ​ናል። 56እና​ንት ግብ​ዞች! የሰ​ማ​ዩ​ንና የም​ድ​ሩን ፊት መመ​ር​መር ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን እነ​ዚ​ህን ዘመ​ናት መመ​ር​መ​ርን እን​ዴት አታ​ው​ቁም? 57እና​ንተ ራሳ​ችሁ እው​ነ​ቱን ለምን አት​ፈ​ር​ዱም? 58ከባ​ለ​ጋ​ራህ ጋር ወደ ሹም በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ ወደ ዳኛ እን​ዳ​ይ​ወ​ስ​ድህ በመ​ን​ገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳ​ህ​ንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎ​ሌው አሳ​ልፎ ይሰ​ጥ​ሃ​ልና። ሎሌ​ውም በወ​ኅኒ ቤት ያስ​ር​ሃል። 59ያለ​ብ​ህን የመ​ጨ​ረ​ሻ​ዋን ግማሽ ሣን​ቲም ቢሆን እስ​ክ​ት​ጨ​ርስ ድረስ አት​ወ​ጣም እል​ሃ​ለሁ።”

Kleurmerk

Deel

Kopieer

None

Wil jy jou kleurmerke oor al jou toestelle gestoor hê? Teken in of teken aan