የሉ​ቃስ ወን​ጌል 11

11
ስለ ጸሎት
1ከዚ​ህም በኋላ በአ​ን​ዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎ​ቱን በጨ​ረሰ ጊዜም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐ​ንስ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንደ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ጸሎት አስ​ተ​ም​ረን” አለው። 2እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በም​ት​ጸ​ል​ዩ​በት ጊዜ እን​ዲህ በሉ፦ በሰ​ማ​ያት የም​ት​ኖር አባ​ታ​ችን ሆይ፥ ስምህ ይቀ​ደስ፤ መን​ግ​ሥ​ትህ ትምጣ፤ ፈቃ​ድህ በሰ​ማይ እንደ ሆነ እን​ዲ​ሁም በም​ድር ይሁን። 3የዕ​ለት ምግ​ባ​ች​ንን በየ​ዕ​ለቱ ስጠን። 4እኛም የበ​ደ​ለ​ንን ሁሉ ይቅር እን​ድ​ንል በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታ​ግ​ባን፤ ከክፉ ሁሉ አድ​ነን እንጂ።”
5እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ወዳጅ ያለው ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ወደ እርሱ ሄዶ እን​ዲህ ቢለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ ሦስት እን​ጀራ አበ​ድ​ረኝ። 6ወዳጄ ከመ​ን​ገድ መጥ​ቶ​ብ​ኛ​ልና የማ​ቀ​ር​ብ​ለት የለ​ኝም።’ 7ያ ወዳ​ጁም ከው​ስጥ ሆኖ፦ ‘አት​ዘ​ብ​ዝ​በኝ፤ ደጁን አጥ​ብ​ቀን ዘግ​ተ​ናል፤ ልጆ​ችም ከእኔ ጋር በአ​ልጋ ላይ ተኝ​ተ​ዋል፤ እሰ​ጥህ ዘንድ መነ​ሣት አል​ች​ልም’ ይለ​ዋ​ልን? 8ወዳጁ ስለ​ሆነ ሊሰ​ጠው ባይ​ነሣ እንኳ እን​ዳ​ይ​ዘ​በ​ዝ​በው ተነ​ሥቶ የወ​ደ​ደ​ውን ያህል ይሰ​ጠ​ዋል። 9እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ ፈልጉ፥ ታገ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ደጅ ምቱ፥ ይከ​ፈ​ት​ላ​ች​ኋ​ልም። 10የሚ​ለ​ምን ሁሉ ይሰ​ጠ​ዋ​ልና፤ የሚ​ፈ​ል​ግም ያገ​ኛ​ልና፤ ደጅ ለሚ​መ​ታም ይከ​ፈ​ት​ለ​ታ​ልና። 11ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ልጁ ዳቦ የሚ​ለ​ም​ነው አባት ቢኖር ድን​ጋይ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? ዓሣ ቢለ​ም​ነ​ውስ በዓሣ ፋንታ እባ​ብን ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? 12ወይስ ዕን​ቍ​ላል ቢለ​ም​ነው በዕ​ን​ቍ​ላል ፋንታ ጊንጥ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? 13እና​ንተ ክፉ​ዎች ስት​ሆኑ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ስጦ​ታን መስ​ጠ​ትን የም​ታ​ውቁ ከሆነ፥ የሰ​ማይ አባ​ታ​ች​ሁማ ለሚ​ለ​ም​ኑት መል​ካ​ሙን ሀብተ መን​ፈስ ቅዱስ#በግ​ሪክ “መን​ፈስ ቅዱ​ስን” ይላል። እን​ዴት አብ​ዝቶ ይሰ​ጣ​ቸው ይሆን?”
ደን​ቆሮ ጋኔን ስለ ያዘው ሰው
14ዲዳና ደን​ቆሮ#“ደን​ቆሮ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ጋኔ​ን​ንም ያወጣ ነበር፤ ጋኔ​ኑም በወጣ ጊዜ ዲዳና ደን​ቆሮ የነ​በ​ረው ተና​ገረ፤ ሰዎ​ችም አደ​ነቁ። 15#ማቴ. 9፥34፤ 10፥25። ነገር ግን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው፥ “በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” ያሉ ነበሩ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል?” አላ​ቸው።#“እር​ሱም መልሶ ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 16#ማቴ. 12፥38፤ 16፥1፤ ማር. 8፥11። ሌሎ​ችም ሊፈ​ት​ኑት ከእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትን ይፈ​ልጉ ነበር። 17እርሱ ግን የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ስዋ የም​ት​ለ​ያይ መን​ግ​ሥት ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ቤትም እርስ በርሱ ቢለ​ያይ ያ ቤት ይወ​ድ​ቃል። 18ሰይ​ጣ​ንስ እርስ በርሱ ከተ​ለ​ያየ መን​ግ​ሥቱ እን​ዴት ይጸ​ናል? በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣል ትላ​ላ​ች​ሁና። 19እኔ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ፥ ልጆ​ቻ​ችሁ በምን ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል? ስለ​ዚህ እነ​ርሱ ይፋ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።#በግ​ሪኩ “ይፈ​ር​ዱ​ባ​ች​ኋል” ይላል። 20እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ እን​ግ​ዲህ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ ደር​ሳ​ለች። 21ኀይ​ለኛ ሰው በጦር መሣ​ሪያ ቤቱን የጠ​በቀ እንደ ሆነ ገን​ዘቡ ሁሉ ደኅና ይሆ​ናል። 22ከእ​ርሱ የሚ​በ​ረ​ታው ቢመ​ጣና ቢያ​ሸ​ን​ፈው ግን፥ ይታ​መ​ን​በት የነ​በ​ረ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይገ​ፈ​ዋል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንና የዘ​ረ​ፈ​ውን#“የዘ​ረ​ፈ​ውን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም። ገን​ዘ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል። 23#ማር. 9፥40። ከእኔ ጋር ያል​ሆነ ባለ​ጋ​ራዬ ነው፤ ከእኔ ጋር የማ​ይ​ሰ​በ​ስ​ብም ይበ​ት​ን​ብ​ኛል።
24“ክፉ ጋኔ​ንም ከሰው በወጣ ጊዜ ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ይሄ​ዳል፤ የሚ​ያ​ር​ፍ​በ​ት​ንም መኖ​ሪያ ይሻል፤ ያላ​ገኘ እንደ ሆነም ወደ ወጣ​ሁ​በት ቤቴ እመ​ለ​ሳ​ለሁ ይላል። 25በመ​ጣም ጊዜ ተጠ​ርጎ አጊ​ጦም ያገ​ኘ​ዋል። 26ከዚ​ህም በኋላ ይሄ​ድና ከእ​ርሱ የሚ​ከፉ ሌሎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን#“ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም። ሰባት አጋ​ን​ንት ያመ​ጣል፤ ገብ​ተ​ውም በዚያ ሰው ያድ​ሩ​በ​ታል፤ ለዚያ ሰውም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛው የከፋ ይሆ​ን​በ​ታል።”
በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አሰ​ምታ ስለ ተና​ገ​ረ​ችው ሴት
27ከዚ​ህም በኋላ ይህን ሲና​ገር ከሕ​ዝቡ መካ​ከል አን​ዲት ሴት ድም​ፅ​ዋን አሰ​ምታ፥ “የተ​ሸ​ከ​መ​ችህ ማኅ​ፀን ብፅ​ዕት ናት፤ የጠ​ባ​ሃ​ቸው ጡቶ​ችም ብፁ​ዓት ናቸው” አለ​ችው። 28እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።
ምል​ክ​ትን ስለ​ሚ​ጠ​ይቁ ሰዎች
29 # ማቴ. 16፥4፤ ማር. 8፥12። ብዙ ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ ፥ “ይቺ ትው​ልድ ክፉ ናት፤ ምል​ክ​ትም ትሻ​ለች፤ ነገር ግን ከነ​ቢዩ ከዮ​ናስ ምል​ክት በቀር ምል​ክት አይ​ሰ​ጣ​ትም። 30#ዮና. 3፥4። ዮናስ ለነ​ነዌ ሰዎች ምል​ክት እንደ ሆና​ቸው የሰው ልጅም ለዚች ትው​ልድ እን​ዲሁ ምል​ክት ይሆ​ና​ታል። 31የአ​ዜብ ንግ​ሥት በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥታ ትፋ​ረ​ዳ​ቸ​ዋ​ለች፤ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ልት​ሰማ ከም​ድር ዳርቻ መጥ​ታ​ለ​ችና፤ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ። 32የነ​ነዌ ሰዎች በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥ​ተው ይፋ​ረ​ዱ​አ​ታል፤#በግ​ሪኩ “ይፈ​ር​ዱ​ባ​ታል” ይላል። ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ታ​ልም፤#“ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ታ​ልም” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም። ዮናስ በሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ጊዜ ንስሓ ገብ​ተ​ዋ​ልና፤ እነሆ፥ ከዮ​ናስ የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።
33“በስ​ውር ቦታ ወይም ከዕ​ን​ቅብ በታች ሊያ​ኖ​ራት መብ​ራ​ትን የሚ​ያ​በራ የለም፤ የሚ​መ​ላ​ለሱ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ያዩ ዘንድ በመ​ቅ​ረ​ዝዋ ላይ ያኖ​ራ​ታል እንጂ። 34የሰ​ው​ነ​ትህ መብ​ራት ዐይ​ንህ ነው፤ ዐይ​ንህ ብሩህ ከሆነ ሰው​ነ​ትህ ሁሉ ብሩህ ነው፤ ዐይ​ንህ ታማሚ ቢሆን ግን፤ ሰው​ነ​ትህ ሁሉ ጨለማ ነው። 35እን​ግ​ዲህ ብር​ሃ​ንህ ጨለማ እን​ዳ​ይ​ሆን ተጠ​ን​ቀቅ። 36ሰው​ነ​ትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነ በአ​ን​ተም ላይ ምንም ጨለማ ባይ​ኖ​ር​ብህ የመ​ብ​ረቅ ብር​ሃን እን​ደ​ሚ​ያ​በ​ራ​ልህ ሁለ​ን​ተ​ናህ ብሩህ ይሆ​ናል።”
ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ምሳ ስለ ጠራው ፈሪ​ሳዊ
37ይህ​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው አንድ ፈሪ​ሳዊ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ገብ​ቶም ለምሳ ተቀ​መጠ። 38ፈሪ​ሳ​ዊ​ዉም አይቶ አደ​ነቀ፤ ምሳ ለመ​ብ​ላት እጁን አል​ታ​ጠ​በም ነበ​ርና። 39ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “እና​ንተ ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ዛሬ የጽ​ዋ​ው​ንና የወ​ጭ​ቱን ውጭ​ውን ታጥ​ቡ​ታ​ላ​ችሁ፤ ታጠ​ሩ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ ውስጡ ግን ቅሚ​ያ​ንና ክፋ​ትን የተ​መላ ነው። 40እና​ንተ ሰነ​ፎች፥ የው​ጭ​ውን የፈ​ጠረ የው​ስ​ጡ​ንስ የፈ​ጠረ አይ​ደ​ለ​ምን? 41ነገር ግን የሚ​ወ​ደ​ደ​ውን ምጽ​ዋት አድ​ር​ጋ​ችሁ ስጡ፤ ሁሉም ንጹሕ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል። 42#ዘሌ. 27፥30። የእ​ን​ስ​ላ​ልና የጤና አዳም፥ ከአ​ት​ክ​ል​ትም ሁሉ ዐስ​ራት የም​ታ​ገቡ ፍር​ድ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍቅር ቸል የም​ትሉ እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! ይህ​ንም ልታ​ደ​ርጉ ይገ​ባ​ች​ኋል፥ ያንም አት​ተዉ። 43እና​ንተ ግብ​ዞች ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! በም​ኵ​ራብ ፊት ለፊት መቀ​መ​ጥን፥ በገ​በ​ያም እጅ መነ​ሣ​ትን ትወ​ዳ​ላ​ች​ሁና። 44እና​ንተ ግብ​ዞች ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! ሰዎች ሳያ​ውቁ በላዩ እን​ደ​ሚ​መ​ላ​ለ​ሱ​በት እንደ ተሰ​ወረ መቃ​ብር ናች​ሁና።”
45ከሕግ ዐዋ​ቂ​ዎ​ችም አንዱ መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስ​ደ​ብህ ነው” አለው። 46እር​ሱም እን​ዲህ አለው፤ “ለእ​ና​ንተ ለሕግ ዐዋ​ቂ​ዎች ወዮ​ላ​ችሁ! ሰውን ከባድ ሸክም ታሸ​ክ​ሙ​ታ​ላ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን ያን ሸክም በአ​ን​ዲት ጣታ​ችሁ እን​ኳን አት​ነ​ኩ​ትም። 47እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥#“ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም። ወዮ​ላ​ችሁ! አባ​ቶ​ቻ​ችሁ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን የነ​ቢ​ያ​ትን መቃ​ብር ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና። 48የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሥራ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ሩ​ባ​ቸ​ውም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ናችሁ፤ እነ​ርሱ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውን እና​ንተ ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና። 49ስለ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበቡ እን​ዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢ​ያ​ት​ንና ሐዋ​ር​ያ​ትን ወደ እነ​ርሱ እል​ካ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ይገ​ድ​ላሉ፤ ያሳ​ድ​ዳ​ሉም። 50ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ እስ​ከ​ዚ​ህች ትው​ልድ ድረስ ስለ ፈሰ​ሰው ስለ ነቢ​ያት ሁሉ ደም ይበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ፥ 51ከአ​ቤል ደም ጀምሮ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በቤተ መቅ​ደሱ መካ​ከል እስከ ገደ​ሉት እስከ ዘካ​ር​ያስ ደም ድረስ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ ከዚች ትው​ልድ ይፈ​ለ​ጋል። 52እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! የጽ​ድ​ቅ​ንና የዕ​ው​ቀ​ትን መክ​ፈቻ ወስ​ዳ​ችሁ ትሰ​ው​ራ​ላ​ች​ሁና፤ እና​ን​ተም አት​ገ​ቡ​ምና፤ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም መግ​ባ​ትን ትከ​ለ​ክ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” 53በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ይህን ሲነ​ግ​ራ​ቸው ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን አጽ​ን​ተው ይጣ​ሉት፥ ይቀ​የ​ሙ​ትም ጀመር። 54በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ሊያ​ስ​ቱ​ትና ሊያ​ጣ​ሉት ያደ​ቡ​በት ነበር።

Kleurmerk

Deel

Kopieer

None

Wil jy jou kleurmerke oor al jou toestelle gestoor hê? Teken in of teken aan