የሉ​ቃስ ወን​ጌል 10

10
ሌሎች ሰባ ሰዎ​ችን ስለ መም​ረጡ
1ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ሌሎች ሰባ ሰዎ​ችን መረጠ፤#በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “አር​አየ” ይላል። ሁለት ሁለት አድ​ር​ጎም ሊሄ​ድ​በት ወደ አለው ከተ​ማና መን​ደር በፊቱ ላካ​ቸው። 2#ማቴ. 9፥37-38። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አላ​ቸው፥ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራ​ተ​ኛው ግን ጥቂት ነው፤ እን​ግ​ዲህ ለመ​ከሩ ሠራ​ተኛ ጨምሮ ይልክ ዘንድ ባለ መከ​ሩን ለም​ኑት። 3#ማቴ. 10፥16። ሂዱ፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተ​ኵ​ላ​ዎች መካ​ከል እል​ካ​ች​ኋ​ለሁ። 4#ማቴ. 10፥7-14፤ ማር. 6፥8-11፤ ሉቃ. 9፥3-5። ከረ​ጢ​ትም፥ ስል​ቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አት​ያዙ፤ በመ​ን​ገ​ድም ማን​ንም ሰላም አት​በሉ። 5ወደ ገባ​ች​ሁ​በት ቤትም አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ‘ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላም ይሁን’ በሉ። 6በዚ​ያም የሰ​ላም ልጅ ቢኖር ሰላ​ማ​ችሁ ያድ​ር​በ​ታል፤ ያለ​ዚያ ግን ሰላ​ማ​ችሁ ይመ​ለ​ስ​ላ​ች​ኋል። 7#1ቆሮ. 9፥14፤ 1ጢሞ. 5፥18። በዚ​ያም ቤት ተቀ​መጡ፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ገ​ኘ​ው​ንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠ​ራ​ተኛ ዋጋው ይገ​ባ​ዋ​ልና፤ ከቤ​ትም ወደ ቤት አት​ሂዱ። 8ወደ ማና​ቸ​ውም ከተማ ብት​ገቡ፥ የዚያ ከተማ ሰዎ​ችም ቢቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ያቀ​ረ​ቡ​ላ​ች​ሁን ብሉ። 9በው​ስ​ጥዋ የሚ​ገ​ኙ​ትን ድው​ያ​ን​ንም ፈውሱ፤ ‘የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ ቀር​ባ​ለች’ በሉ​አ​ቸው። 10ነገር ግን ወደ ማና​ቸ​ውም ከተማ ብት​ገቡ፥ የዚ​ያች ከተማ ሰዎ​ችም ባይ​ቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ወጥ​ታ​ችሁ የእ​ግ​ራ​ች​ሁን ትቢያ አራ​ግፉ።#“የእ​ግ​ራ​ች​ሁን ትቢያ አራ​ግፉ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። እን​ዲ​ህም በሉ፦ 11#የሐዋ. 13፥51። ከከ​ተ​ማ​ችሁ የተ​ጣ​በ​ቀ​ብ​ንን ትቢያ እን​ኳን እና​ራ​ግ​ፍ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ እንደ ቀረ​በች ይህን ዕወቁ። 12#ዘፍ. 19፥24-28፤ ማቴ. 11፥24፤ 10፥15። በፍ​ርድ ቀን ሰዶም ከዚ​ያች ከተማ ይልቅ እን​ደ​ም​ት​ሻል ይቅ​ር​ታ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ገኝ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።
13 # ኢሳ. 23፥1-8፤ ሕዝ. 26፥1—28፥26፤ ኢዩ. 3፥4-8፤ አሞ. 1፥9-10፤ ዘካ. 9፥2-4። “ኮራዚ ወዮ​ልሽ! ቤተ ሳይዳ ወዮ​ልሽ! በእ​ና​ንተ የተ​ደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ተደ​ርጎ ቢሆን ቀድሞ ማቅ ለብ​ሰው አመ​ድም ነስ​ን​ሰው በተ​ቀ​መጡ ንስ​ሓም በገቡ ነበር። 14ነገር ግን ጢሮ​ስና ሲዶና ከእ​ና​ንተ ይልቅ በፍ​ርድ ቀን ይቅ​ር​ታን ያገ​ኛሉ። 15#ኢሳ. 14፥13-15። አን​ቺም ቅፍ​ር​ና​ሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወ​ር​ጃ​ለሽ።
16 # ማቴ. 10፥40፤ ማር. 9፥37፤ ሉቃ. 9፥48፤ ዮሐ. 13፥20። “እና​ን​ተን የሚ​ሰማ እኔን ይሰ​ማል፤ እና​ን​ተ​ንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም እንቢ የሚል የላ​ከ​ኝን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም የሚ​ሰማ የላ​ከ​ኝን ይሰ​ማል።”#“እኔን የሚ​ሰ​ማኝ የላ​ከ​ኝን ይሰ​ማል” የሚ​ለው በግ​ሪኩ እና በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም።
ስለ ሰባው መል​እ​ክ​ተ​ኞች መመ​ለስ
17እነ​ዚ​ያም ሰባው ደስ ብሎ​አ​ቸው ተመ​ለ​ሱና፥ “አቤቱ፥ አጋ​ን​ንት ስንኳ በስ​ምህ ተገ​ዙ​ልን” አሉት። 18እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰይ​ጣ​ንን ከሰ​ማይ እንደ መብ​ረቅ ሲወ​ድቅ አየ​ሁት። 19#መዝ. 90፥13። እነሆ፥ ጊን​ጦ​ች​ንና እባ​ቦ​ችን፥ የጠ​ላ​ት​ንም ኀይል ሁሉ ትረ​ግጡ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ የሚ​ጐ​ዳ​ች​ሁም ነገር የለም። 20ነገር ግን አጋ​ን​ንት ስለ ተገ​ዙ​ላ​ችሁ በዚህ ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ፤ ግን ስማ​ችሁ በሰ​ማ​ያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።”
21በዚ​ያች ሰዓ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ደስ አለው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የሰ​ማ​ይና የም​ድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከዐ​ዋ​ቂ​ዎ​ችና ከአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች ሰው​ረህ ለሕ​ፃ​ናት ስለ​ገ​ለ​ጥ​ኸው አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃ​ድህ በፊ​ትህ እን​ዲሁ ሆኖ​አ​ልና። 22#ዮሐ. 3፥35፤ 10፥15። ሁሉ ከአ​ባቴ ዘንድ ተሰ​ጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወ​ልድ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም። ወልድ ግን ለወ​ደ​ደው ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል።”
23ተመ​ል​ሶም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ለብ​ቻ​ቸው አድ​ርጎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የም​ታ​ዩ​ትን የሚ​ያዩ ዐይ​ኖች ብፁ​ዓን ናቸው። 24ብዙ ነቢ​ያ​ትና ነገ​ሥ​ታት እና​ንተ የም​ታ​ዩ​ትን ሊያዩ ተመኙ፤ አላ​ዩ​ምም፤ እና​ንተ የም​ት​ሰ​ሙ​ት​ንም ሊሰሙ ተመኙ፥ አል​ሰ​ሙም።”
ጌታን ስለ ፈተ​ነው ሕግ ዐዋቂ
25 # ማቴ. 22፥35-40፤ ማር. 12፥28-34። ከዚህ በኋላ አንድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈ​ት​ነው ተነ​ሣና፥ “መም​ህር ሆይ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እወ​ርስ ዘንድ ምን ላድ​ርግ?” አለው። 26እር​ሱም፥ “በኦ​ሪት ምን ተጽ​ፎ​አል? እን​ዴ​ትስ ታነ​ብ​ባ​ለህ?” አለው። 27#ዘሌ. 19፥18፤ ዘዳ. 6፥5። እር​ሱም መልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ትህ፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልህ፥ በፍ​ጹም ዐሳ​ብህ ውደ​ደው፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው። 28#ዘሌ. 18፥5። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “መል​ካም መል​ሰ​ሃል፤ እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ትድ​ና​ለ​ህም” አለው።
29ራሱን ሊያ​ከ​ብር ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሊንቅ#ግሪኩ እና አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሊንቅ” የሚ​ለ​ውን አይ​ጽ​ፉም። ወድዶ፥ “ባል​ን​ጀ​ራዬ ማነው?” አለው።
ስለ ደጉ ሳም​ራዊ
30ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ኢያ​ሪኮ ይወ​ርድ ነበር፤ ሽፍ​ቶ​ችም አገ​ኙት፤ ደበ​ደ​ቡት፥ አቈ​ሰ​ሉት፥ ልብ​ሱ​ንም ገፍ​ፈው፤ በሕ​ይ​ወ​ትና በሞት መካ​ከል ጥለ​ውት ሄዱ። 31አንድ ካህ​ንም በዚ​ያች መን​ገድ ሲወ​ርድ ድን​ገት አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አል​ፎት ሄደ። 32እን​ዲ​ሁም አንድ ሌዋዊ በዚያ ቦታ አገ​ኘ​ውና፥ አይቶ እንደ ፊተ​ኛው አል​ፎት ሄደ። 33አንድ ሳም​ራዊ ግን በዚ​ያች መን​ገድ ሲሄድ አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አዘ​ነ​ለት። 34#2ዜ.መ. 28፥15። ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ቍስ​ሉ​ንም አጋ​ጥሞ አሰ​ረ​ለት፤ በቍ​ስሉ ላይም ወይ​ንና ዘይት ጨመ​ረ​ለት፤ በአ​ህ​ያ​ውም ላይ አስ​ቀ​ምጦ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰው የእ​ን​ግ​ዶ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ጠ​ብ​ቀው ወሰ​ደው፤ የሚ​ድ​ን​በ​ት​ንም ዐሰበ። 35በማ​ግ​ሥ​ቱም ሁለት ዲናር አው​ጥቶ ለእ​ን​ግዳ ቤት ጠባ​ቂው ሰጠ​ውና፦ ‘በዚህ አስ​ታ​ም​ልኝ፤ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ለእ​ርሱ የም​ታ​ወ​ጣው ቢኖር እኔ በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ እከ​ፍ​ል​ሃ​ለሁ’ አለው። 36እን​ግ​ዲህ ሽፍ​ቶች ለደ​በ​ደ​ቡት ሰው ከእ​ነ​ዚህ ከሦ​ስቱ ባል​ን​ጀራ የሚ​ሆ​ነው ማን​ኛው ይመ​ስ​ል​ሃል?” 37እር​ሱም“ምሕ​ረት ያደ​ረ​ገ​ለት ነዋ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ኪ​ያስ አን​ተም ሂድና እን​ዲሁ አድ​ርግ” አለው።
ስለ ማር​ያ​ምና ስለ ማርታ
38ከዚ​ህም በኋላ ሄደው ወደ አን​ዲት መን​ደር ገቡ፤ ማርታ የም​ት​ባል አን​ዲት ሴትም በቤቷ ተቀ​በ​ለ​ችው። 39#ዮሐ. 11፥1። ማር​ያም የም​ት​ባል እኅ​ትም ነበ​ረ​ቻት፤ እር​ስ​ዋም ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጣ ትም​ህ​ር​ቱን ትሰማ ነበር። 40ማርታ ግን ብዙ በማ​ዘ​ጋ​ጀት ትደ​ክም ነበር፤ ቆማም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኅቴ ትታኝ ብቻ​ዬን ስሠራ አያ​ሳ​ዝ​ን​ህ​ምን? ርጃት በላት” አለ​ችው። 41ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፥ ትቸ​ገ​ሪ​ያ​ለ​ሽም፤ ታዘ​ጋ​ጂ​ያ​ለ​ሽም። 42ጥቂት ይበ​ቃል፤ ያም ባይ​ሆን አንድ ይበ​ቃል፤ ማር​ያ​ምስ የማ​ይ​ቀ​ሙ​አ​ትን መል​ካም ዕድል መረ​ጠች።”

Kleurmerk

Deel

Kopieer

None

Wil jy jou kleurmerke oor al jou toestelle gestoor hê? Teken in of teken aan