ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 5

5
የአ​ዳም ትው​ልድ
(1ዜ.መ. 1፥1-4)
1የሰ​ዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዳ​ምን በፈ​ጠረ ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ አደ​ረ​ገው፤ 2ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም። እነ​ር​ሱ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው። 3አዳ​ምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም እንደ ምሳ​ሌው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙ​ንም ሴት ብሎ ጠራው። 4አዳ​ምም ሴትን ከወ​ለደ በኋላ የኖ​ረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 5አዳ​ምም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
6ሴትም ሁለት መቶ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ሄኖ​ስ​ንም ወለደ፤ 7ሴትም ሄኖ​ስን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 8ሴትም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
9ሄኖ​ስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፤ ቃይ​ና​ን​ንም ወለደ፤ 10ሄኖ​ስም ቃይ​ና​ንን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ። ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 11ሄኖ​ስም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
12ቃይ​ና​ንም መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፤ መላ​ል​ኤ​ል​ንም ወለደ፤ 13ቃይ​ና​ንም መላ​ል​ኤ​ልን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 14ቃይ​ና​ንም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ዐሥር ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
15መላ​ል​ኤ​ልም መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ያሬ​ድ​ንም ወለደ፤ 16መላ​ል​ኤ​ልም ያሬ​ድን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 17መላ​ል​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ስም​ንት መቶ ዘጠና አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
18ያሬ​ድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሄኖ​ክ​ንም ወለደ፤ 19ያሬ​ድም ሄኖ​ክን ከወ​ለደ በኋላ ስም​ንት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 20ያሬ​ድም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
21ሄኖ​ክም መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ኖረ፤ ማቱ​ሳ​ላ​ንም ወለደ፤ 22ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው፤ ሄኖ​ክም ማቱ​ሳ​ላን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 23ሄኖ​ክም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ሆነ። 24ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ስላ​ሰ​ኘው አል​ተ​ገ​ኘም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው​ሮ​ታ​ልና።
25ማቱ​ሳ​ላም መቶ ሰማ​ንያ ሰባት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ስድሳ ሰባት” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ላሜ​ሕ​ንም ወለደ፤ 26ማቱ​ሳ​ላም ላሜ​ሕን ከወ​ለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰማ​ንያ ሁለት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስም​ንት መቶ ሁለት” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 27ማቱ​ሳ​ላም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
28ላሜ​ሕም መቶ ሰማ​ንያ ሁለት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ሰማ​ንያ ስም​ንት” ይላል። ዓመት ኖረ፤ ልጅ​ንም ወለደ። 29ስሙ​ንም ከሥ​ራዬ፥ ከእጄ ድካ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከረ​ገ​ማት ምድር ይህ ያሳ​ር​ፈኝ ዘንድ አለው ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው። 30ላሜ​ሕም ኖኅን ከወ​ለደ በኋላ አም​ስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት#ዕብ. “አም​ስት መቶ ዘጠና አም​ስት” ይላል። ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም ወለደ። 31ላሜ​ሕም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰባት መቶ ሃምሳ ሦስት” ዕብ. “ሰባት መቶ ሰባ ሰባት” ይላል። ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
32ለኖ​ኅም አም​ስት መቶ ዓመት ሆነው፤ ኖህም ሦስት ልጆ​ችን ወለደ፤ እነ​ር​ሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው።

Qaqambisa

Share

Copy

None

Ufuna ukuba iimbalasane zakho zigcinwe kuzo zonke izixhobo zakho? Bhalisela okanye ngena