BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample

የምስራቹ የሚያሳየው የኢየሱስ መንፈስ በእርግጥም በሰው ልጆች ውስጥ እንደሚኖር፣ እንዲሁም ደግሞ መንፈሱ የእግዚአብሔርን የመገኘት ታላቅነት የሰው ልጆች እንዲለማመዱ ማድረግ እንደሚያስችል ነው። ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህን ሚስጥር፣ "የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ" በማለት ገልፆታል።
ያንብቡ፦
ቈላስይስ 1÷25-29
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
ይህን ክፍል ሲያጤኑ፣ የትኛዎቹ ቃላት ወይም ሀረጎች ጎልተው ይታይዎታል?
የኢየሱስ መንፈስ እርሱን በሚታመኑ ሰዎች ውስጥ መኖር የመቻሉን ሚስጥር ያሰላስሉ። ይህን እያሰላሰሉ ሳለ፣ ጥያቄዎችዎን፣ መደነቅዎን እና አግራምዎቶን ለእግዚአብሔር ወደሚቀርብ ጸሎት ይቀይሩት።
Scripture
About this Plan

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More
Related Plans

Unboxed: Built on Purpose

Cherished & Chosen: A 7-Day Challenge for Single Women

Love at Work

Dear Black Woman, You Are Not Alone in Your Grief

Relentless Love: Reflections on the Book of Jonah

Holy Spirit - Breath of God

Boundaries: A Biblical Perspective

Journey Through Revelation

Journey Through 1 & 2 Peter and Jude
