BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተስፋ በኢየሱስ ላይ ይመረኮዛል፤ ምክንያቱም ለሚያምኑት ሁሉ በሞቱና በትንሳኤው "ህያው ተስፋ" ሊሰጥ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው። በሌላ አባባል፣ ኢየሱስ የሚሰጠው ተስፋ "ህያው" የሆነው እርሱ ራሱ ህያው ስለሆነና ዘላለማዊ ህይወትን ስለሚሰጥ ነው። ተስፋችንን በእርሱ ላይ ስናደርግ አናዝንም፣ ከእርሱ ጋርም ለዘላለም እንኖራለን።
ያንብቡ፦
1ኛ ጴጥሮስ 1÷3-5
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
ይህን ክፍል ሲያነቡ ምን ይመለከታሉ?
ይህ ክፍል ለእግዚአብሔር የቀረበ ባርኮት እንደሆነ ያስተውሉ። እግዚአብሔርን በራስዎ አባባል እየባረኩ ለመጸለይ ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ።
Scripture
About this Plan
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More