BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample
ነቢዩ ኢሳያስ ግዛቱ ወደ ዘላለማዊ ሻሎም የሚመራውን የሰላም አለቃን መምጣት ይጠባበቅ ነበር። የኢሳያስ ትንቢቶች ፍጻሜ ያገኙት ኢየሱስ ሲመጣ ነበር። ለዚህ ነው መላእክት የኢየሱስን ውልደት "ሰላም በምድር" ሲሉ የገለጹት።
ያንብቡ፦
ሉቃስ 2÷9-15
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
እግዚአብሔር የንጉሱን መምጣት ስመጥር ላልሆኑ እረኞች ያበሰረው ለምን ይመስልዎታል? ይህ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ መንግስቱ ምን ይነግርዎታል?
በዚያ ሌሊት ከእርኞቹ ጋር እንደሆኑ አድርገው ራስዎን ያስቡ። ምን ይሰማዎት ነበር? ምን ምላሽ ይሰጣሉ?
በመላእክቱ አምልኳዊ የምስራች ውስጥ ያሉትን "ታላቅ" እና "ምድር" የሚሉትን ቃላት ያስተውሉ። ኢየሱስ ሲወለድ ከሰማያት ወርዶ ወደ ምድር የመጣው ምንድን ነው? ይህ የምስራች የሆነው እንዴት ነው? የተሰማዎትን የመደነቅና የምስጋና ስሜት ለመግለጽ ምልከታዎ ወደ ጸሎት እንዲያመራ ያድርጉ።
Scripture
About this Plan
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More