YouVersion Logo
Search Icon

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

DAY 16 OF 28

በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ገጽ እግዚአብሔር ይህች አለም መልካም እንደሆነች ተናግሯል፤ በመሆኑም ሰዎች እግዚአብሔር በሰራቸው መልካም ነገሮች ደስ ይሰኛሉ። ይሁን እንጂ፣ ይህች አለም እንዴት በእኛ ራስወዳድነት እንደተበላሸች እና አሁን በሞትና ዕጦት እንደተሞላች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በተጨማሪ ያሳያል። እንዴት ነው አንድ ሰው እጅግ በበዛ ቀውስና ሀዘን መካከል ደስታን ሊለማመድ የሚችለው? በዚህ ውጥረት መካከል ስለደስታ የተለየ አመለካከት ከመጽሐፍ ቅዱስ እናገኛለን። የእግዚአብሔር ህዝብ ደስታ የሚረጋገጠው እግዚአብሔር ስለወደፊቱ ዕጣ ፈንታቸው በሰጣቸው የተስፋ ቃል እንጂ አሁን ባሉበት ሁኔታ አይደለም። ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከባርነት በታደጋቸው ጊዜ፣ ሊሰጣቸው ቃል ከገባላቸው ምድር ርቀው በምድረ በዳ ቢሆኑም እንኳን በደስታ ጮኽዋል።

ያንብቡ፦

መዝሙር 105÷42-43፣ ዘጸአት 15÷1-3

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

የትኞቹ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች ናቸው ሃሴት እንዲያደርጉ የሚያግዝዎ?

ለዚህ ምላሽ፣ እግዚአብሔር ስለገባልዎ የተስፋ ቃል ምስጋናዎን ይጻፉ ወይም ይዘምሩ።

Day 15Day 17

About this Plan

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More