BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample
ሐዋሪያው ጳውሎስ እስር ቤት እያለ ነበር ለፊሊጵስዩስ ሰዎች ደብዳቤ የጻፈው። መከራን ያውቃል ግን ደግሞ የእግዚአብሔርን ሰላምም ያውቅ ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሰላም፣ ልክ እንደ ተስፋ፣ በክርስቶስ ላይ እንጂ በሁኔታዎች ላይ ስላልተመሰረተ ነው። ጳውሎስ ተደራሲያኑን በእግዚአብሔር ሁልጊዜ ደስ እንዲላቸው፣ እንዲጸልዩ፣ እንዲያመሰግኑ፣ እንዲሁም በጎና እውነት የሆነውን እንዲያስቡ ጥሪ ያደርጋል።
ያንብቡ፦
ፊልጵስዩስ 4÷1-9
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 4÷1-9 የሚያስቀምጣቸውን ትዕዛዛት (ለምሳሌ እንደ "በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ"፣ "በአንድ ሃሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ" የመሳሰሉትን) ሁሉ ዘርዝራችሁ ጻፉ።
የጻፉትን ዝርዝር ይመልከቱና እያንዳንዱን ነገር ሁልጊዜ የሚለማመዱት ልማድ እንዴት ሊያደርጉት እንደሚችሉ ያስቡ። እነዚህ ልማዶች በዕለት ተዕለት ህይወትዎ በተግባር ምን ሊመስሉ ይችላሉ? እነዚህ ልማዶች በሂደት የእግዚአብሔርን ሰላም ወደ መለማመድ እንዴት የሚያመሩ ይመስልዎታል?
ቁጥር 7 እና 9ን ይከልሱ። ምን ያስተውላሉ? እነዚህ ጥቅሶች ስለእግዚአብሔር ሰላም ጠባቂነት ምን ይነግሩናል? ለጥበቃው ምስጋናዎን አሁን ይግለጹ።
Scripture
About this Plan
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More