ዘፍጥረት 4

4
ቃየንና አቤል
1አዳም ሚስቱን ሔዋንን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ቃየንን#4፥1 ቃየን የሚለው ስም ማምጣት ወይም ማግኘት የሚል ትርጕም ካላቸው የዕብራይስጥ ቃላት ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው ወለደች፤ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” አለች። 2ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።
አቤል የበግ እረኛ፣ ቃየንም ዐራሽ ነበር። 3በአንድ ወቅት፣ ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት አቀረበ። 4አቤልም መጀመሪያ ከተወለዱት በጎች መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤ 5በቃየንና በመሥዋዕቱ ግን አልተደሰተም፤ ስለዚህ ቃየን ክፉኛ ተናደደ፤ ፊቱም ጠቈረ።
6 እግዚአብሔር አምላክም (ያህዌ ኤሎሂም) ቃየንን እንዲህ አለው፤ “ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቈረ? 7መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።”
8ቃየንም ወንድሙን አቤልን፣ “እስቲ ና፤ ወደ መስኩ እንውጣ”#4፥8 እስቲ ና፣ ወደ መስኩ እንውጣ የሚለው ሐረግ በኦሪተ ሳምራውያን፣ በሰብዓ ሊቃናት፣ በቩልጌትና፣ በሱርስት የሚገኝ ሲሆን በማሶሬቲክ ጽሑፍ ውስጥ ግን የለም አለው፤ በመስኩም ሳሉ፣ ቃየን ወንድሙን አቤልን አጠቃው፤ ገደለውም።
9ከዚያም፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ቃየንን፣ “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው።
ቃየንም፣ “አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ሲል መለሰ።
10 እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “ምንድን ነው ያደረግኸው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። 11እንግዲህ የተረገምህ ነህ፤ የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፏን ከከፈተችው መሬት ትሰደዳለህ። 12ብታርሳትም ፍሬዋን አትለግስህም፤ በምድር ላይ ኰብላይና ተንከራታች ትሆናለህ።” 13ቃየንም እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “ቅጣቴ ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው። 14እነሆ፤ ዛሬ ከምድሪቱ አባረርኸኝ፤ ከፊትህም እሸሸጋለሁ፤ በምድር ላይ ኰብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል።”
15 እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን፣ “የለም! እንደርሱ አይሆንም፤#4፥15 ዕብራይሰጡ ከሰብዓ ሊቃናት፣ ከቩልጌትና ከሱርስቱ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን መልካም ይለዋል። ማንም ቃየንን ቢገድል፣ ሰባት ዕጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው፤ ስለዚህ፣ ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው እግዚአብሔር (ያህዌ) በቃየን ላይ ምልክት አደረገለት። 16ቃየንም ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወጥቶ ሄዶ፣ ከዔድን በስተ ምሥራቅ በምትገኝ ኖድ#4፥16 ኖድ ማለት መቅበዝበዝ ማለት ነው (12 እና 14 ይመ)። በተባለች ምድር ተቀመጠ።
17ቃየን ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ሄኖክን ወለደች። ቃየን የቈረቈረውን ከተማ በልጁ ስም ሄኖክ ብሎ ጠራው። 18ሄኖክ ኢራድን ወለደ፤ ኢራድም መሑያኤልን፣ መሑያኤልም ማቱሣኤልን፣ ማቱሣኤልም ላሜሕን ወለደ።
19ላሜሕ ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የአንደኛዋ ስም ዓዳ፣ የሁለተኛዋም ጺላ ነበር። 20ዓዳ ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ከብት አርቢዎች አባት ነበረ። 21ወንድሙም ዩባል ይባላል፤ እርሱም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበረ። 22ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።
23ላሜሕ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤
“ዓዳና ጺላ ሆይ ስሙኝ፤
የላሜሕ ሚስቶች ሆይ አድምጡኝ፤
አንድ ሰው ቢያቈስለኝ፣
ጕልማሳው ቢጐዳኝ፣ ገደልሁት፤#4፥23 ወይም እገድላለሁ
24ቃየንን የሚገድል ሰባት ጊዜ ቅጣት ካገኘው፣
የላሜሕ ገዳይማ ሰባ ሰባት ጊዜ ቅጣት ያገኘዋል።”
25አዳም እንደ ገና ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ምትክ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ሴት#4፥25 ሴት ማለት ሰጠ ሳይሆን አይቀርም። ብላ ጠራችው። 26ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው።
በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም መጥራት#4፥26 ወይም ማወጅ ጀመሩ።

നിലവിൽ തിരഞ്ഞെടുത്തിരിക്കുന്നു:

ዘፍጥረት 4: NASV

ഹൈലൈറ്റ് ചെയ്യുക

പങ്ക് വെക്കു

പകർത്തുക

None

നിങ്ങളുടെ എല്ലാ ഉപകരണങ്ങളിലും ഹൈലൈറ്റുകൾ സംരക്ഷിക്കാൻ ആഗ്രഹിക്കുന്നുണ്ടോ? സൈൻ അപ്പ് ചെയ്യുക അല്ലെങ്കിൽ സൈൻ ഇൻ ചെയ്യുക

ዘፍጥረት 4 - നുള്ള വീഡിയോ