መዝሙረ ዳዊት 31
31
የዳዊት ትምህርት መዝሙር።
1ኀጢአታቸው የተተወላቸው፥
በደላቸውንም ሁሉ ያልቈጠረባቸው ብፁዓን ናቸው።
2እግዚአብሔር በደሉን የማይቈጥርበት
በልቡም ሽንገላ የሌለበት ሰው ብፁዕ ነው።
3ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ
ዝም ብያለሁና አጥንቶቼ አረጁ፤
4በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥
እሾህ በወጋኝ ጊዜ ወደ ጕስቍልና#ከዕብ. ይለያል። ተመለስሁ።
5ኀጢአቴን ነገርሁ፤
በደሌንም አልሸሸግሁም፤
ስለ ኀጢአቴ ወደ እግዚአብሔር ራሴን እከስሳለሁ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እነግራለሁ” ይላል። አልሁ፤
አንተም የልቤን ሽንገላ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኀጢአት” ይላል። ተውልኝ።
6ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ በምቹ ጊዜ
ወደ አንተ ይጸልያል፤
ነገር ግን ብዙ የጥፋት ውኃ ወደ አንተ አይቀርብም።#ግእዝ “ወደ እርሱ” ይላል።
7አንተ ካገኘችኝ ከዚች መከራዬ መሸሸጊያዬ ነህ፥
ከከበቡኝም ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።
8አስተምርሃለሁ፥ በምትሄድባትም በዚች መንገድ አጸናሃለሁ።
ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጸናለሁ።
9ወደ አንተ እንዳይቀርቡ
በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥
ልብ እንደሌላቸው
እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
10የኃጥኣን መቅሠፍታቸው ብዙ ነው፤
በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን ይቅርታ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ምሕረት” ይላል። ይከባቸዋል።
11ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ሐሤትም አድርጉ፤
ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ በእርሱ ተመኩ።#ዕብ. “እልል በሉ” ይላል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 31: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in