YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 31

31
የዳ​ዊት ትም​ህ​ርት መዝ​ሙር።
1ኀጢ​አ​ታ​ቸው የተ​ተ​ወ​ላ​ቸው፥
በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያል​ቈ​ጠ​ረ​ባ​ቸው ብፁ​ዓን ናቸው።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ሉን የማ​ይ​ቈ​ጥ​ር​በት
በል​ቡም ሽን​ገላ የሌ​ለ​በት ሰው ብፁዕ ነው።
3ሁል​ጊዜ ከመ​ጮኼ የተ​ነሣ
ዝም ብያ​ለ​ሁና አጥ​ን​ቶቼ አረጁ፤
4በቀ​ንና በሌ​ሊት እጅህ ከብ​ዳ​ብ​ኛ​ለ​ችና፥
እሾህ በወ​ጋኝ ጊዜ ወደ ጕስ​ቍ​ልና#ከዕብ. ይለ​ያል። ተመ​ለ​ስሁ።
5ኀጢ​አ​ቴን ነገ​ርሁ፤
በደ​ሌ​ንም አል​ሸ​ሸ​ግ​ሁም፤
ስለ ኀጢ​አቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሴን እከ​ስ​ሳ​ለሁ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መተ​ላ​ለ​ፌን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ግ​ራ​ለሁ” ይላል። አልሁ፤
አን​ተም የል​ቤን ሽን​ገላ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኀጢ​አት” ይላል። ተው​ልኝ።
6ስለ​ዚህ ጻድቅ ሁሉ በምቹ ጊዜ
ወደ አንተ ይጸ​ል​ያል፤
ነገር ግን ብዙ የጥ​ፋት ውኃ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም።#ግእዝ “ወደ እርሱ” ይላል።
7አንተ ካገ​ኘ​ችኝ ከዚች መከ​ራዬ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ ነህ፥
ከከ​በ​ቡ​ኝም ታድ​ነኝ ዘንድ ደስ​ታዬ ነህ።
8አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ፥ በም​ት​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ አጸ​ና​ሃ​ለሁ።
ዐይ​ኖ​ቼን በአ​ንተ ላይ አጸ​ና​ለሁ።
9ወደ አንተ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ
በል​ባ​ብና በል​ጓም ጉን​ጫ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ለ​ጕ​ሙ​አ​ቸው፥
ልብ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው
እንደ ፈረ​ስና እንደ በቅሎ አት​ሁኑ።
10የኃ​ጥ​ኣን መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው ብዙ ነው፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መ​ኑ​ትን ግን ይቅ​ርታ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ምሕ​ረት” ይላል። ይከ​ባ​ቸ​ዋል።
11ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤
ልባ​ች​ሁም የቀና ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ተመኩ።#ዕብ. “እልል በሉ” ይላል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 31