YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 30

30
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በማ​ድ​ነቅ ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አል​ፈር፤
በጽ​ድ​ቅ​ህም አስ​ጥ​ለኝ፥ አድ​ነ​ኝም።
2ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፥ ፈጥ​ነ​ህም አድ​ነኝ፤
ታድ​ነኝ ዘንድ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒ​ቴና የመ​ጠ​ጊ​ያዬ ቤት ሁነኝ።
3ኀይ​ሌና መጠ​ጊ​ያዬ አንተ ነህና
ስለ ስምህ ምራኝ፥ መግ​በ​ኝም፤
4አቤቱ፥ አንተ ረዳቴ#ዕብ. “መታ​መ​ኛዬ” ይላል። ነህና
ከሰ​ወ​ሩ​ብኝ ከዚች ወጥ​መድ አው​ጣኝ።
5በእ​ጅህ ነፍ​ሴን አደራ እሰ​ጣ​ለሁ፤
የጽ​ድቅ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ተቤ​ዠኝ።
6ከን​ቱን ነገር የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ ሊ. በብዙ ቍጥር ነው። ሁሉ ሁል​ጊዜ ጠላህ፤
እኔ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ንሁ።
7በት​ድ​ግ​ናህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በም​ሕ​ረ​ትህ” ይላል። ደስ ይለ​ኛል፤ ሐሴ​ትም አደ​ር​ጋ​ለሁ።
መከ​ራ​ዬን አይ​ተ​ሃ​ልና፥
ነፍ​ሴ​ንም ከጭ​ን​ቀት አድ​ነ​ሃ​ታ​ልና።
8በጠ​ላቴ እጅ አል​ዘ​ጋ​ኸኝም፥
በሰ​ፊም ስፍራ እግ​ሮ​ቼን አቆ​ምህ።
9ተቸ​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና አቤቱ ይቅር በለኝ፥
ዐይ​ኔም ከቍጣ የተ​ነሣ ታወ​ከች፥
ነፍ​ሴም፥ ሆዴም።
10ሕይ​ወቴ በመ​ከራ አል​ቋ​ልና፥
ዘመ​ኔም በጩ​ኸት፤ ኀይሌ በች​ግር ደከመ፥
አጥ​ን​ቶቼም ሁሉ ተነ​ዋ​ወጡ።
11በጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ ዘንድ ተሰ​ደ​ብሁ፥
ይል​ቁ​ንም በጎ​ረ​ቤ​ቶቼ ዘንድ፥
ለዘ​መ​ዶ​ቼም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለሚ​ያ​ው​ቀኝ” ይላል። አስ​ፈሪ ሆንሁ፤
በሜዳ ያዩ​ኝም ከእኔ ሸሹ።
12እንደ ሞተ ሰው ከልብ ረሱኝ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተረ​ሳሁ” ይላል።
እንደ ጠፋ ዕቃም ሆንሁ።
13በዙ​ሪ​ያዬ የከ​በ​ቡ​ኝን ድምፅ ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤
በላዬ በአ​ን​ድ​ነት በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ፥
ነፍ​ሴን ለመ​ን​ጠቅ በተ​ማ​ከሩ ጊዜ።
14አቤቱ፥ እኔ ግን በአ​ንተ ታመ​ንሁ፤
አንተ አም​ላኬ ነህ አልሁ።
15ርስቴ በእ​ጅህ ነው፤
ከጠ​ላ​ቶቼ እጅና ከከ​በ​ቡኝ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱኝ” ይላል። አድ​ነኝ።
16ፊት​ህን በባ​ሪ​ያህ ላይ አብራ፥
ስለ ምሕ​ረ​ት​ህም አድ​ነኝ።
17አቤቱ፥ አን​ተን ጠር​ቻ​ለ​ሁና አል​ፈር፤
ሸን​ጋ​ዮች ይፈሩ፥ ወደ ሲኦ​ልም ይው​ረዱ።
18በት​ዕ​ቢ​ትና በመ​ናቅ
በጻ​ድቅ ላይ ዐመ​ፃን የሚ​ና​ገሩ
የሽ​ን​ገላ ከን​ፈ​ሮች ወዮ​ላ​ቸው።#ዕብ. እና ግሪክ አባ. ሊ. “ድዳ ይሁኑ” ይላል።
19 # መዝ. 30 ቁ. 19 ከዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል። አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ ብዛት
የሚ​ፈ​ሩ​ህን ሰወ​ር​ኻ​ቸው፥
በሰው ልጆች ፊት የሚ​ታ​መ​ኑ​ብ​ህ​ንም አዳ​ን​ኻ​ቸው።
20በፊ​ትህ ጥላ ከሰው ክር​ክር ትጋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፥
በመ​ጋ​ረ​ጃ​ህም ከአ​ን​ደ​በት ሽን​ገላ ትሸ​ፍ​ና​ቸ​ዋ​ለህ።
21በመ​ከ​ራዬ ብዛት ጊዜ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በተ​መ​ሸገ ከተማ” ይላል። ምሕ​ረ​ቱን በእኔ ላይ የገ​ለጠ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።
22እኔስ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት ተጣ​ልሁ ብዬ ነበር።
ስለ​ዚህ ወደ እርሱ የጮ​ኽ​ሁ​ትን
የል​መ​ና​ዬን ቃል ሰማኝ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. በቅ​ርብ ነው።
23ጻድ​ቃን ሁላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ዱት፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን ይሻ​ልና፥
ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ሹ​ትን ፈጽሞ ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋል።
24በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ምኑ ሁላ​ችሁ፥
ታገሡ ልባ​ች​ሁ​ንም አጽኑ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in