YouVersion Logo
Search Icon

መዝ​ሙረ ዳዊት 29

29
ለቤቱ መመ​ረቅ ምስ​ጋና የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና፥
የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አላ​ደ​ረ​ግ​ኸ​ኝ​ምና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከፍ ከፍ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” ይላል።
2አቤቱ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ይቅ​ርም አል​ኸኝ።
3አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ከሲ​ኦል አወ​ጣ​ሃት፥
ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ለይ​ተህ አዳ​ን​ኸኝ።
4ጻድ​ቃን ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥
ለቅ​ድ​ስ​ና​ውም መታ​ሰ​ቢያ አመ​ስ​ግኑ።
5መቅ​ሠ​ፍቱ ከቍ​ጣው ነውና፥#ዕብ. “ለጥ​ቂት ጊዜ” ይላል።
መዳ​ንም ከፈ​ቃዱ#ዕብ. “ሞገሱ ግን ለሕ​ይ​ወት ዘመን” ይላል። ነውና፤
ማታ ልቅሶ ይሰ​ማል፥
ጥዋት ግን ደስታ ይሆ​ናል።
6እኔም በደ​ስ​ታዬ፥ “ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ታ​ወ​ክም” አልሁ።
7አቤቱ፥ በፈ​ቃ​ድህ ለሕ​ይ​ወቴ ኀይ​ልን ስጣት፤
ፊት​ህን መለ​ስህ፥ እኔም ደነ​ገ​ጥሁ።
8አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥
ወደ አም​ላ​ኬም ለመ​ንሁ።
9ወደ ጥፋት ብወ​ርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ?
አፈር ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ልን? ጽድ​ቅ​ህ​ንም ይና​ገ​ራ​ልን?
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ፥ ይቅ​ርም አለኝ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ሆነኝ።
11ልቅ​ሶ​ዬን መል​ሰህ ደስ አሰ​ኘ​ኸኝ።
ማቄን ቀድ​ደህ ደስ​ታን አስ​ታ​ጠ​ቅ​ኸኝ።
12ክብሬ እን​ዲ​ዘ​ም​ር​ልህ እን​ዳ​ል​ደ​ነ​ግ​ጥም፥#ዕብ. “ዝም እን​ዳ​ል​ልም” ይላል።
አቤቱ፥ አም​ላኬ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝ​ሙረ ዳዊት 29