YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 29

29
በበ​ዓለ መጥ​ቅዕ የሚ​ቀ​ርብ መሥ​ዋ​ዕት
(ዘሌ. 23፥23-25)
1“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወሩ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ለእ​ና​ንተ ይህች ዕለት የተ​ቀ​ደ​ሰች ናት፤#ዕብ. “በመ​ጀ​መ​ሪያ ቀን የተ​ቀ​ደሰ ጉባኤ ይሁ​ን​ላ​ችሁ” ይላል። የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ምል​ክት ያለ​ባት ቀን ትሁ​ን​ላ​ችሁ።#ዕብ. “መለ​ከ​ቶች የሚ​ነ​ፉ​በት ቀን ነው” ይላል። 2ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት፥ የበግ ጠቦ​ቶች፥ 3ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸው በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለበ​ሬው ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራው በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 4ለሰ​ባቱ ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 5ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 6በወሩ መባቻ ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን እንደ ሕጋ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።
በኀ​ጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረያ ቀን የሚ​ቀ​ርብ መሥ​ዋ​ዕት
(ዘሌ. 23፥26-32)
7“የዚ​ህም ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤#ዕብ. “በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የተ​ቀ​ደሰ ጉባኤ ይሁ​ን​ላ​ችሁ” ይላል። ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቁ​አት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታ​ድ​ርጉ። 8ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ። 9ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለበ​ሬው ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራው በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 10ለሰ​ባቱ ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ፥ 11ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል አቅ​ርቡ። ከሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ በዘ​ወ​ት​ርም ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ሌላ አቅ​ር​ቡት።
በዳስ በዓል ቀን የሚ​ቀ​ርብ መሥ​ዋ​ዕት
(ዘሌ. 23፥33-44)
12“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ዐሥራ አም​ስ​ተ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤#ዕብ. “በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን የተ​ቀ​ደሰ ጉባኤ ይሁ​ን​ላ​ችሁ” ይላል። የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ሰባት ቀንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል አድ​ርጉ። 13ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ዐሥራ ሦስት በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች አቅ​ርቡ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁኑ። 14ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለዐ​ሥራ ሦስት በሬ​ዎች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለሁ​ለቱ አውራ በጎች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 15ለዐ​ሥራ አራቱ ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ፥ 16ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።
17“በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥራ ሁለት በሬ​ዎ​ችን፥ ሁለት አውራ በጎ​ችን፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶ​ችን፥ 18ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ችው መጠን እንደ ሕጉ፥ 19ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየ​ልን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባ​ና​ቸው ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።
20“በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥራ አንድ በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ 21ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥ 22ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።
23“በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ዐሥር በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ 24ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ችው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥ 25ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።
26“በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን ዘጠኝ በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ 27ለበ​ሬ​ዎ​ቹና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥ 28ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።
29“በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ስም​ንት በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ 30ለበ​ሬ​ዎ​ችና ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥ 31ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።
32“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሰባት በሬ​ዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ዐሥራ አራት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ 33ለበ​ሬ​ዎቹ፥ ለአ​ውራ በጎቹ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው፥ 34ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።
35“ስም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን የተ​ቀ​ደሰ በዓል ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት። 36ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 37የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ውና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸው ለበ​ሬው፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን እንደ ሕጋ​ቸው ይሆ​ናሉ። 38ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።
39“እነ​ዚ​ህ​ንም፥ ከስ​እ​ለ​ታ​ች​ሁና በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ ከም​ታ​መ​ጡት ሌላ፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ህ​ልም፥ ለመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ በበ​ዓ​ላ​ችሁ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።” 40ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ኦሪት ዘኍ​ልቍ 29