YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 30

30
ስለ ብፅ​ዐት የተ​ሰጠ ሥር​ዐት
1ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ዶች አለ​ቆች እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው። 2ሰው ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ቢሳል፥ ወይም መሐ​ላን ቢምል፤ ራሱ​ንም ቢለይ፥#“ራሱን ቢለይ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ቃሉን አያ​ር​ክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድ​ርግ። 3ሴትም ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ብት​ሳል፥ እር​ስ​ዋም በአ​ባቷ ቤት ሳለች በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ ጊዜ ራስ​ዋን ብት​ለይ፥ 4አባ​ቷም ስእ​ለ​ቷ​ንና ራስ​ዋን የለ​የ​ች​በ​ትን ቢሰማ፥ አባ​ቷም ዝም ቢላት፥ ስእ​ለቷ ሁሉ ይጸ​ናል፤ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ሁሉ ይጸ​ናል። 5አባቷ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለቷ፥ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐ​ላዋ አይ​ጸ​ኑም፤ አባቷ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይላ​ታል።
6“ባል ያገ​ባች ብት​ሆን፥ በአ​ን​ደ​በ​ቷም እንደ ተና​ገ​ረች ስለ ራስዋ የተ​ሳ​ለ​ችው ስእ​ለት በራ​ስዋ ላይ ቢሆን፥ 7ባል​ዋም ቢሰማ፥ በሰ​ማ​በ​ትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእ​ለቷ፥ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ይጸ​ናሉ። 8ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ አይ​ጸ​ኑም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይቅር ይላ​ታል።
9“ባልዋ የሞ​ተ​ባት ወይም የተ​ፋ​ታች ግን ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ይጸ​ኑ​ባ​ታል። 10ሴትም በባ​ልዋ ቤት ሳለች ብት​ሳል፥ ወይም ራስ​ዋን በመ​ሐላ ብታ​ስር፥ 11ባል​ዋም ሰምቶ ዝም ቢላት፥ ባይ​ከ​ለ​ክ​ላ​ትም፥ ስእ​ለቷ ሁሉ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ሁሉ ይጸ​ናል። 12ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ስእ​ለ​ቷን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስለ ስእ​ለቷ ወይም ራስ​ዋን ስላ​ሰ​ረ​ች​በት መሐላ ከአ​ፍዋ የወ​ጣው ነገር አይ​ጸ​ናም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሏ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያነ​ጻ​ታል።
13“ስእ​ለ​ቷን ሁሉ፥ ነፍ​ስ​ዋ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን የመ​ሐላ ማሰ​ሪያ ሁሉ ባልዋ ያጸ​ና​ዋል፤ ወይም ባልዋ ይከ​ለ​ክ​ለ​ዋል። 14ነገር ግን በየ​ዕ​ለቱ ዝም ቢላት፥ ስእ​ለ​ቷን ሁሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ያለ​ውን መሐላ ሁሉ ያጸ​ና​ዋል፤ በሰ​ማ​በት ቀን ዝም ብሎ​አ​ታ​ልና አጽ​ን​ቶ​ታል። 15ከሰ​ማው በኋላ ግን ቢከ​ለ​ክ​ላት ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።” 16እር​ስዋ በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ ጊዜ በአ​ባቷ ቤት ሳለች በአ​ባ​ትና በል​ጂቱ መካ​ከል፥ ወይም በባ​ልና በሚ​ስት መካ​ከል ይሆን ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ያዘ​ዘው ሥር​ዐት ይህ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ኦሪት ዘኍ​ልቍ 30