YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 3

3
የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት
1“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ቢሆን፥ ከላ​ሞች መንጋ ተባት ወይም እን​ስት ቢያ​ቀ​ርብ፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቅ​ርብ። 2እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል። 3ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ባሉ፤ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ 4ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ያመ​ጣሉ። 5የአ​ሮ​ንም ልጆች ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያቀ​ር​ቡ​ታል፤ የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ነው።
6“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባኑ ከበ​ጎች ተባት ወይም እን​ስት ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ያቀ​ር​ባል። 7ለቍ​ር​ባኑ የበግ ጠቦ​ትን ቢያ​ቀ​ርብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤ 8እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያር​ደ​ዋል፤ ካህ​ና​ቱም የአ​ሮን ልጆች ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል። 9ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ያቀ​ር​ባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀር​ባ​ውም ድረስ የተ​ቈ​ረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ 10ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድ​ኑም አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ይወ​ስ​ዳል። 11ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ በጎ መዓዛ ያለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።
12“ቍር​ባ​ኑም ፍየል ቢሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤ 13እጁ​ንም በራሱ ላይ ይጭ​ን​በ​ታል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃ​ፍም ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል። 14ከእ​ር​ሱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን አድ​ርጎ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ሆድ ዕቃ​ውን የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ 15ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ይወ​ስ​ዳል። 16ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። 17ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in