YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 4

4
የኀ​ጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረያ መሥ​ዋ​ዕት
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦ 2“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ሳያ​ውቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ 3የተ​ቀ​ባ​ውም ሊቀ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ላይ በደል እን​ዲ​ቈ​ጠ​ር​ባ​ቸው ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢ​አቱ ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​በ​ዋል። 4ወይ​ፈ​ኑ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያመ​ጣ​ዋል፤ እጁ​ንም በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ ይጭ​ነ​ዋል፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል። 5ተቀ​ብቶ የተ​ሾ​መው ካህን ከወ​ይ​ፈኑ ደም በእጁ ወስዶ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ያመ​ጣ​ዋል፤ 6ካህ​ኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ፊት ደሙን ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል። 7ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው ጣፋጭ ዕጣን በሚ​ታ​ጠ​ን​በት መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ የወ​ይ​ፈ​ኑ​ንም ደም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል። 8ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ታ​ረ​ደው ወይ​ፈን ስብን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ 9ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶች ጋር፥ 10ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ ተወ​ሰ​ደው ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል። 11የወ​ይ​ፈ​ኑን ቍር​በት፥ ሥጋ​ው​ንም ሁሉ፥ ራሱ​ንም፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፥ ሆድ ዕቃ​ው​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም፤ 12ወይ​ፈ​ኑን ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደ​ሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ አመድ በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።
13“የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገ​ሩም ከማ​ኅ​በሩ ዐይን ቢሸ​ሸግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፉ፤ 14ከዚ​ህም በኋላ፥ የሠ​ሩት ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቃ​ቸ​ውና ንስሓ ቢገቡ ማኅ​በሩ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንን ያቀ​ር​ባሉ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ፊት ያመ​ጡ​ታል። 15የማ​ኅ​በ​ሩም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይጭ​ናሉ፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል። 16የተ​ቀ​ባ​ውም ካህን ከወ​ይ​ፈኑ ደም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ያመ​ጣል፤ 17ካህ​ኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል። 18በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባለው በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል። 19ስቡ​ንም ሁሉ ከእ​ርሱ ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል። 20እን​ዲ​ህም በወ​ይ​ፈኑ ያደ​ር​ጋል፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት በታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ አደ​ረገ እን​ዲሁ በዚህ ያደ​ር​ጋል፤ ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል። 21ወይ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም ወይ​ፈን እን​ዳ​ቃ​ጠሉ ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ የማ​ኅ​በሩ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።
22“መኰ​ን​ንም ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ሳያ​ው​ቅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ እን​ዲ​ህም ቢበ​ድል፥ 23የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ከፍ​የ​ሎች ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያቀ​ር​ባል፤ 24በፍ​የ​ሉም ራስ ላይ እጁን ይጭ​ናል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ እርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና። 25ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል። 26ስቡ​ንም ሁሉ እንደ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ስብ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።
27“ከሀ​ገ​ሩም ሕዝብ አንድ ሰው ኀጢ​አ​ትን ሳያ​ውቅ ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢበ​ድ​ልም፥ 28ለእ​ር​ሱም የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥#“ንስሓ ቢገባ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ስለ ሠራው ኀጢ​አት ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያመ​ጣል። 29እጁ​ንም በኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት እን​ስ​ሳ​ትን በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ፍየ​ል​ዋን ያር​ዳ​ታል። 30ካህ​ኑም ከደ​ምዋ በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል። 31ስቡም ሁሉ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ፥ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ እርሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።
32“ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት የበግ ጠቦት ቢያ​ቀ​ርብ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ትን እን​ስት ያመ​ጣል። 33እጁ​ንም በኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዳ​ታል። 34ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል። 35ስቡ ሁሉ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው የበግ ጠቦት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in