መጽሐፈ መዝሙር 54
54
እነሆ፥ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ የዳዊት መዝሙር
ከጠላት እጅ ለመዳን የቀረበ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! በስምህ አድነኝ፤
በኀይልህም ፍረድልኝ።
2አምላክ ሆይ! ጸሎቴን ስማ!
ቃሌንም አድምጥ።
3ሞገደኞች አደጋ ሊጥሉብኝ ተነሡ፤
ጨካኞች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤
ስለ እግዚአብሔርም አያስቡም።
4ነገር ግን አምላክ ረዳቴ ነው፤
ጌታም የሕይወቴ ደጋፊ ነው።
5ተንኰላቸውን በሚያስጨንቁኝ ጠላቶቼ ላይ መልስባቸው፤
እነርሱን በማጥፋት ታማኝነትህን አሳይ።
6መሥዋዕትህን በፍላጎቴ አቀርብልሃለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ፥ ተገቢ ስለ ሆነ
ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ
7ከችግሬ ሁሉ አድነኸኛል፤
የጠላቶቼንም ውድቀት አየሁ። #1ሳሙ. 23፥19፤ 26፥1።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 54: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997