YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 43

43
መዝሙር 43#43 በብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች መዝሙር 42 እና 43 አንድ መዝሙር ነው።
በስደት ላይ ያለ ሌዋዊ ልቅሶ
1አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤
ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፤
ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።
2አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣
ለምን ተውኸኝ?
ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣
ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?
3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤
እነርሱ ይምሩኝ፤
ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣
ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።
4እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤
ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣
በበገና አመሰግንሃለሁ።
5ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?
ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?
ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤
አዳኜና አምላኬን፣
ገና አመሰግነዋለሁና።

Currently Selected:

መዝሙር 43: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in