የዕዝራ መጽሐፍ የወንጌል ዕይታናሙና

ፍሬያማነት
በዕዝራ መጽሐፍ ዳሰሳ ላይ እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ሊዋጀንና ሊያድሰን የገባውን የተስፋ ቃል ለመፈፀም የታመነ መሆኑን ተመልክተናል፤ ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ እግዚአብሔር ለሾመን ስራ ታማኞቸች እንድንሆን ኃይል የሚሰጠን እርሱ ኢየሱስ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ዕዝራ እግዚአብሔር በሾመው ነገር ላይ የነበረው ታማኝነት ብዙ ፍሬያማነትን እንዳስገኘለት እንይ፡፡ በፀሎት በእርሱ ላይ በተደገፍን ቁጥር በህይወታችን የእግዘአብሔርን ዓላማ እንድንፈፅም ፍሬያማ የሚያደርገን በውስጣችን የሚኖረው የክርሰቶስ ህይወት ነው፡፡
የዕዝራ መጽሐፍ ከምዕራፍ 1 – 6 ያለው ታሪክ የሚነግረን የመጀመሪያው የአይሁድ ተመላሽ ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌም ስለመመለሳቸውና ስለ ቤተ-መቅደሱ ዳግም መገንባት ነው፡፡ የዕዝራ መጽሐፍ ከምዕራፍ 1 – 6 ያለው ታሪክ የሚዘግበው ስለ ሁለተኛ ዙር ተመላሽ ምርኮኞች እና ቀጥሎ ስለነበረው መንፈሳዊ ተሃድሶ ነው፡፡ በመመለስ ሂደት ውስጥ ዕዝራ ትኩረት ያደረገው የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ኋላ ባፈገፈገው ህዝብ ላይ እንደገና መመለስ ነበር፡፡ የይሁዳ ወንዶች እግዚአብሐርን ከማምለክ የሚያርቋቸውን ጣኦት አምላኪ ሴቶችን ያገቡ ነበር፡፡ ዕዝራ በውሳኔና በቆራጥነት ለህዝቡ አለመታዘዝ ምላሽ ሲሰጥና ከህዝባቸውም መካከል የኃጢአት ልምምዶችን እንዲያስወግዱ ሲረዳቸው እናያለን፡፡ ይህ ደግሞ ለብሔራዊ መነቃቃት ምክንያት ሆነ፡፡ የዕዝራ የታማኝነት ስራ ፍሬያማነትን አመጣ፤ የእግዚአብሔርም ህዝብ ከእርሱ ጋር ወዳላቸው ትክክለኛ ህብረት ተመለሱ፡፡
ይህ ሁሉ የሚያንፀባርቀው በእኛ ህይወት ውስጥ የክርስቶስን ስራ ነው፡፡ ከክርሰቶስ ጋር ያለን አንድነት በውስጣችን ለቅድስና፣ ለእግዚአብሔርና ለመንግስተ ሰማይ አዲስ ፍላጎትን ይፈጥራል፡፡ ኃጢአት አንሰራም ማለት አይደልም፤ ኃጢአት መስራት ግን አንፈልግም፡፡ እንዲህ አስበህ አታውቅ ይሆናል እንጂ ኃጢአትን ላለማድረግ ያለህ ፈላጎት ፍሬያማ ህይወትን እየኖርክ እንዳለህ ማሳያ ነው፡፡ መንፈሳዊ ፍሬያማነታችን ወደ ተግባራዊ ፍሬያማነት ይለወጣል፤ ይህ ደግሞ አግዚአብሔር የሰጠን ስጦታዎችን በዙሪያችን ላሉ ለሌሎች ጥቅም የምናውልበት ነው፡፡ እግዚአብሔር አሁን ላይ ቤተሰብን፣ ጎረቤቶቻችንን ወይም የቤተ-ክርስቲያን ማህበረሰብን የምታገለግልበት ምን ዕድል እንዳለህ ዓይኖችህን እንዲከፍትልህ ጠይቀው፡፡ የስራ ቦታህን ለእግዚአብሔር መንግስት ፍሬ የምታፈራበት ቦታ መሆኑን ተመልከት፡፡ ቀጣዩ እርምጃህ ምንድን ነው? በዕዝራ ታሪክ ላይ እንደምናየው በክርስቶስ የተቀበልነው አዲሱ ሕይወት ሥራችንን ተስፋ አስቆራጭ በሆነ በራስ ጥገኝነት ድካም ሳይሆን እረፍት በተሞላበት በእግዚአብሔር ላይ በተመሰረተ እምነት ይኸውም በወንጌል የተቃኘ ፍሬያማነት መሆኑን ነው፡፡
በፀሎት በእርሱ ላይ በተደገፍን ቁጥር ህይወትህን ዳግም በህይወትህ የእግዘአብሔርን ዓላማ እንድትፈፅም ፍሬያማ የሚያደርግህ በውስጥህ የሚኖረው የክርሰቶስ ህይወት በመሆኑ ደስ ለመሰኘት ጊዜ ውሰድ፤ ይህም ዓላማውን ለቤተ ክርስቲያኑ እና ለዓለሙ የሚፈፅምበት ነው፡፡ የገባውን የተስፋ ቃል ለመፈፀም የታመነውን በዚህም ታማኝ የሆነውንና ፍሬያማ፤ የእግዚአብሔርም ስራ በእጁ የታየውን የዕዝራን ምሳሌነት መከተል ይሁንልን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እግዚአብሔር ለስራው ባስቀመጠህ ቦታ ስትሰማራ ይህ በአንተም እውነት ይሁን፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር የገባልህን የተስፋ ቃል እንዴት እንደሚፈፅመው ትገረም ይሆን? ፍሬያማ ኑሮስ ለመኖር ተስፋ ታደርጋለህ? የዕዝራ መጽሐፍ የሚዳስሰው እግዚአብሔር ህዝቡን ለመታደግና ለማደስ የተስፋ ቃሉን መፈፀሙን ሲሆን ከዚህም የተነሳ የኖሩትን ፍሬያማ ኑሮ ያሳያል፡፡ በዕዝራ አስደማሚ ታሪክ ውስጥ የሚታየው አግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ የገባው ትልቁ የተስፋ ፍፃሜ የሆነውና ብቸኛው የፍሬያማነት መንገድ የሆነው ኢየሱስ ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/