የዕዝራ መጽሐፍ የወንጌል ዕይታናሙና
ታማኝነት
ትናንትና እግዚአብሔር እኛን ሊዋጀንና ሊያድሰን የገባልንን የተስፋ ቃል እንደሚፈፅም ተምረናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ለህዝቡ ያለውን የእግዚአብሔርን ታማኝነት እንመልከት፡፡ የዕዝራ ታሪክ የሚያሳየን እግዚአብሔር በሾመን ስራ ላይ ታማኞች እንድንሆን ኃይል የሚሰጠን በመንፈስ ቅዱስ በኩል እርሱ ክርስቶስ መሆኑን እና የዕዝራ እግዚአብሔር በሾመው ኃላፊነት ላይ የመታመኑ ምስጢር የሚያመለክተው ክርስቶስ ለተቀበለው ኃላፊነት ያለውን ታማኝነት ይኸውም የወደቁትንና ኃጢያተኞችን ወደ እግዚአብሔር ኅብረት መመለስ ነው፡፡
ይህ የመሲሃዊ ጥላ በብዙ የብሉይ ኪዳን ምስሎች ውስጥ ይታያል። የዕብራውያን ፀሐፊ የሙሴን ታማኝነት ከኢየሱስ ታማኝነት ጋር ያነፃፅረዋል፡፡ ኢየሱስ እውነተኛውና ምቹውንና የለመደውን አከባቢ ትቶ የእግዚአብሔርን ድምፅ በመስማት አዲስን የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመፍጠር ወዴት እንደሚሄድ እንኳን ሳያውቅ እንደታመነው አብርሃም ነው፡፡ ከዳዊት ታሪክ ኢየሱስ ለመፈፀም አንድም ድንጋይ ባላበረከቱ ነገረ ግን የእርሱ ድል የህዝቡ ድል የሆነ እውነተኛና እጅግ የታመነ ዳዊት መሆኑን እናያለን፡፡ ከዮሴፍ ታሪክ ደግሞ በንጉሱ ቀኝ የተቀመጠው፤ የካዱትን ሁሉ ይቅር ያለው እና እነርሱን ለማዳን ኃይሉን የተጠቀመው ኢየሱስ እውነተኛና እጅግ የታመነ ዮሴፍ መሆኑን እንማራለን፡፡
ዕዝራ የሚያጠና፣ የሚተረጉም፣ የሚያስተምርና የእግዚአብሔርን ቃል የሚኖር የታመነ ካህንና ፀሐፊ ነበር፡፡ አሁንም የእርሱ እውነትን ለመኖር እና ሌሎችም ፈለጉን እንዲከተሉ የሚያበረታበት መንገድ ኢየሱስን ያሳየነናል፤ ይኸውም አንዴ ራሱን በመስቀል ላይ መስወዋዕት አድርጎ የኃጢአታችንን ስርየት በማረጋገጥ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀን ከሁሉ የሚበልጠውና እጅግ የታመነ ሊቀ-ካህናችን ነው፡፡ ኢየሱስ ደግሞ ህያው የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚፅፍልን ፍፁም ፀሐፊ ሆኗል፡፡
በቀደመው ኪዳን ዕዝራ የእግዚአብሔርን ድንጋጌና ህጎችን ለህዝቡ አስተምሯል፡፡ በአዲስ ኪዳን ደግሞ እግዚአብሔር ህጉን በአእምሮአችንና በልባችን በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ህያው የእግዚአብሔር ቃል በሆነው በኢየሱስ በእኛ ውስጥ አስቀምጧል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ባነበብን ቁጥር መንፈስ ቅዱስ ከውስጥ ወደ ውጪ በሆነ ለውጥ ይለውጠናል፡፡ የእግዚአብሔር እውነት ሀሳባችንንና ተግባራችንን ይለውጣል፤ ስለዚህም በእርሱ ጥንካሬ ልክ ዕዝራ የእግዚአብሔርን ህዝብ በማደስ ረገድ የተጫወተውን የታማኝነት ሚና ዓይነት ታማኞች መሆን አንችላለን፡፡ እስቲ እግዚአብሔር አንተ እንድታከናውነው የሰጠህን ሚና በተሰጠህ ዘመን ተመልከት እና አንተ ተፅዕኖ በምታሳድርበት ዙሪያህ ላይ ምን ተሃድሶ ያስፈልግ ይሆን፡፡
ዕዝራ በትህትና ለእግዚአብሔር መታዘዝ የኢየሱስን ታማኝነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን ለእኛም ምሳሌ ነው፡፡ የእኛ የራሳችን ጥንካሬ ሲጥለን ወደ ኢየሱስ ብርታትበየቀኑ መቅረብ ስለምንችል ደስ ይበለን፡፡ እግዚአብሔር በታማኝነቱ ፍፁም ነው፤ እኛም ታማኞች እንድንሆን ይጠራናል፤ ይኸውም ለእርሱ በምንሰጠው ጊዜና በዓለም ዙሪያ እርሱን ለማገልገል ታማኞች በመሆን ነው፡፡
ስለዚህ እቅድ
እግዚአብሔር የገባልህን የተስፋ ቃል እንዴት እንደሚፈፅመው ትገረም ይሆን? ፍሬያማ ኑሮስ ለመኖር ተስፋ ታደርጋለህ? የዕዝራ መጽሐፍ የሚዳስሰው እግዚአብሔር ህዝቡን ለመታደግና ለማደስ የተስፋ ቃሉን መፈፀሙን ሲሆን ከዚህም የተነሳ የኖሩትን ፍሬያማ ኑሮ ያሳያል፡፡ በዕዝራ አስደማሚ ታሪክ ውስጥ የሚታየው አግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ የገባው ትልቁ የተስፋ ፍፃሜ የሆነውና ብቸኛው የፍሬያማነት መንገድ የሆነው ኢየሱስ ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/