የዕዝራ መጽሐፍ የወንጌል ዕይታናሙና
መፈፀም
ምናልባት እግዚአብሔር መቼ ወይም እንዴት ተስፋ ቃሉን በህይወትህ ላይ ሊፈፅም እንደሚችል ትገረም ይሆናል፡፡ ምናልባትም ደግሞ አሁን ባለህበት ወቅትና ሁኔታዎች ፍሬያማ ሆነህ ለማየት እየታገልህ ይሆናል፡፡ የዕዝራ መጽሐፍ እግዚአብሔር እንደ አማኝ ሲጠራን ፍሬያማ እንድንሆንና እንድንሰራ ኃይልን የሚያስታጥቀን እግዚአብሔር የተስፋ ቃሉን በመፈፀም የታመነ መሆኑን እያሳየን ነው፡፡ በዚህ የ3 ቀን የንባብ ዕቅድ ስለ ተስፋ መፈፀም፣ ስለ ታማኝነት፣ እና ፍሬያማነት ዋና ጭብጥ እንመለከታለን፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዕዝራ የተጫወተው ታሪካዊ ሚና እንዴት ወደ ኢየሱስና ወደ ወንጌል እንደሚያመለክተን እንቃኛለን፡፡
በመጀመሪያ በዕዝራ ታሪክ የምናየው እግዚአብሔር እንዴት ህዝቡን ከስደት እንደታደገና ወደ ምድራቸው እንደመለሳቸው ነው፡፡ ግዞትና ምርኮ አዲስ ነገር ሊሆንባቸውም አይገባም ምክንያቱም እግዚአብሔር እርሱን ባለመታዘዝ ከቀጠሉ ውጤቱ ምርኮ መሆኑን በተደጋጋሚ አስጠንቅቋቸዋል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ የህዝቡ ኃጢያትና የእግዚአብሔር ተግሳፅ እንዳለ ሆኖ የተቀጠረው ጊዜ ሲፈፀም ከተማዋን፣ ቤተ መቅደሱን እና ህዝቡን ሊያድስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመልሳቸው እርሱ ራሱ የተስፋ ቃል ገብቶላቸው ነበር፡፡ ዕዝራ ምዕራፍ 1፡1 እግዚአብሔር በኤርሚያስ በኩል የሰጣቸውን ትንቢት መፈፀሙን ይነግረናል፡፡ ኤርሚያስ በባቢሎን ሰባው የምርኮ ዓመት ሲፈፀም እግዚአብሔር ለህዝቡ የገባውን መልካሙን የተስፋ ቃል እንደሚፈፅም ተናግሮ ነበር፡፡ ይህንን የመታደግ ተአምርና የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ፍፃሜ ለማድረግ እግዚአብሔር የቂሮስን ልብ ቀሰቀሰ፡፡
በዕዝራ ህይወት የነበሩ ክስተቶች አግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የሰራልን ማሳያ ጥላ ነው፡፡ ዘፍጥረት ምዕራፍ 3ን መለስ ብለን ስናይ የአዳምና ሔዋን የሚያፀፅት ምርጫ የሰው ዘር ሁሉ ምርኮኛ እንዲሆን አደረገ፡፡ እኛ ከእግዚእብሔር የተሰደድንና በኃጢአት የተወለድን ነን፡፡ እንደ እስራኤላዊ ዕዝራ ራሱ ስደተኛ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ጌታ ህዝቡን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተጠቀመበት፡፡ በተመሳሳይ ኢየሱስም እንደ እኛ ሆኖ መጥቶ፣ በመካከላችን ኖሮ ወደ ነፃነት መራን፡፡ ጳውሎስ ለፊሊጵስዩስ ሰዎች በፃፈው ደብዳቤ ኢየሱስ በምድር በኖረበት ቆይታው እንዴት ባለ የስደተኝነት ስሜት ሊሆን እንደሚችል ገልጿል፡፡
በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት በዕዝራ መጽሐፍ ላይ በምናደርገው ጉዞ ምናልባት ኢየሱስን በዚህ የጥንት ታሪክ ውስጥ ልትመለከቱት ትችላላችሁ፡፡ ወንጌሉ እርሱን ለማወቅና ለማሳወቅ ፍሬያማ እንድትሆኑ የሚያስችላችሁና የሚያበረታችሁ የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ እኛ የምናገለግለው ኪዳኑን የሚያከብር ሁልጊዜም የገባውን ቃል የሚያከብረውን እግዚአብሔርን ነው፡፡ ምንም ዓይነት እንቅፋት ይግጠምህ እንዲሁም በምንም ዓይነት የግንኙነት፣ የፋይናንስ ወይም አካላዊ ስደት ውስጥ ራስህን አግኘው በዕዝራ ታሪክ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እንደተንፀባረቀው የክርስቶስ ኢየሱስ የምስራች ሁሉ እግዚአብሔር ምንም ዓይነት የገባልህን የተስፋ ቃል ይፈፅማል፡፡
ስለዚህ እቅድ
እግዚአብሔር የገባልህን የተስፋ ቃል እንዴት እንደሚፈፅመው ትገረም ይሆን? ፍሬያማ ኑሮስ ለመኖር ተስፋ ታደርጋለህ? የዕዝራ መጽሐፍ የሚዳስሰው እግዚአብሔር ህዝቡን ለመታደግና ለማደስ የተስፋ ቃሉን መፈፀሙን ሲሆን ከዚህም የተነሳ የኖሩትን ፍሬያማ ኑሮ ያሳያል፡፡ በዕዝራ አስደማሚ ታሪክ ውስጥ የሚታየው አግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ የገባው ትልቁ የተስፋ ፍፃሜ የሆነውና ብቸኛው የፍሬያማነት መንገድ የሆነው ኢየሱስ ነው፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/