Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?ናሙና
ታዲያ እግዚአብሔር በቀጣይ ምን ያደርጋል?
አንድ የስነ መለኮት አስተማሪ ስለ ክርስትና እምነቱ ሲናገር “የመጀመሪያዎቹ 50 ዓመታት እጅግ ከባድ ናቸው፡፡” ምናልባት ይህ አስደናቂ ነው፡፡ ምናልባትም እውነቱን ነው፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ ከብዙ አስርት ዓመታት በኋላ የራሳቸውን ነገር ወደ መጨረስና በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ መደገፍን፣ መጠንከርና መኖር ተማሩ፡፡
መፃፍ ስጀምር ለ20 ዓመታት ክርስቲያን ነበርኩኝ ግን ይህን ያህል እንዳስቆጠርኩኝ አላውቅም ነበር፡፡ በእነዚህ ዓመታት ከክርስቶስ ጋር የነበረኝ ግንኙነት የሻከረበትና እግዚአብሐርን በጣም እንደተውኩት የሚሰሙኝ ጊዜያቶች ነበሩ፡፡ በራሴ ከእግዚአብሔር ጋር ሊያራምደኝ የሚያስችል ነገር እንደሌለኝ ተረድቻለሁ። በርግጥ ጥረታችን ብቻውን እግዚአብሐር ቀጥሎ በሕይወታችን ውስጥ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ለማየት በቂ ባይሆንም፣ ብዙውን ጊዜ የምንጠቀመውን ‘እግዚአብሔር ግን!’ በሚለውን የአዲስ ኪዳን ማቆሚያ መደሰት እንችላለን። ይህ ሀረግ ለክርስትና ህይወታችን አስደማሚ ተስፋ ይሰጠናል፡፡
እግዚአብሔር ብቁ ላልሆንበት አንዳች ነገር ስለሚያደርግልን በእውነት ለእርሱ እንኖራለን፡፡ እርሱ በእምነት ጉዞዋችን ስለሚያጠነክረንና ስለሚያስቀጥለን የማይታለፉትን መሰናክሎች በእርሱ አቅም እናልፋቸዋለን፡፡ ሐጌ 2:1–9 ሁለተኛውን የመጨረሻውን የዳስ በዓል ያብራራል፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ የ40 ዓመቱን የምድረበዳ ትዝታቸውንና በምድረ በዳ ያዩትን ተአምራዊ የእግዚአብሔር አቅርቦት ለመዘከር ወደ ኢየሩሳሌም ተመሙ፡፡ ከወር በፊት ንስሃ ገብተው፤ እንደገና እግዚብሔርን አስቀድመውና፤ የእግዚአብሔርን ቤት ለመስራት ትኩረት አድርገው የነበረ ቢሆንም አሁንም በኢየሩሳሌም ያላቸው የህይወት ምልልስ ዝቅተኛ ነው፡፡ ህዝቡ በመንፈሳዊ የትላንት ናፋቂነት ምክንያት እግዚአብሔር ወደፊት ለእነርሱ ወዳዘጋጀው ነገር መዘርጋት ሲሳናቸው እንመለከታለን፡፡ የእነርሱ ምርጥ ጥረት እግዚአብሔር እንዲያደርጉ የጠራቸውን ለማድረግ በቂ አለመሆኑን ተገንዝበው ተስፋ ሲቆርጡ እናያለን። ይሁን እንጂ እኛ ለእርሱ ከተሸነፍን ወደፊት እግዚአብሔር በእኛ ህይወት ሊሰራ የሚፈልገው ነገር ሁልጊዜ ከዚህ በፊት ካወቅነው ነገር በላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሐጌ በኩል ለህዝቡ፤ ስለ ህልውናው፣ ስለ ኃይሉና ስለ ሰላሙ ተስፋ በመስጠት የነገ ተስፋቸው ደግሞ ካለፈው በጣም የተሻለ መሆኑን ያስረግጥላቸዋል፡፡
እግዚአብሔር ሕዝቡ አብሯቸው መሆኑን በማወቅ ወደፊት እንዲራመዱ በማሳሰብ በነፍሳቸውና በሚታይ ነገር ያፀናቸው ነበር፡፡ ልክ በፋርሱ ንጉስ በዳርዮስ ዘመን እንዳደረገው ቤተ መቅደሱን እንደገና ለማስገንባት አህዛብን ሁሉ ማናወጥ ይችላል፡፡ ማን ከአንተ ጋር እንዳለ ማስታወስ ይኸውም ሁሉን ቻይ ጌታ የሆነው ወደፊት በአንተ ህይወት የሚሆነውን ትሰራ ዘንድ ያጠነክርሃል፡፡ አንተ መቼም ብቻህን አይደለህም፤ እናም እግዚአብሔር አንተ እንድትቀጥል፤ ለአንተ የሚገባውን አቅርቦት ማቅረቡን፤ እንዲሁም ወደፊት ያለውን ቀጣዩን እርምጃ እንድትዘረጋ ማስቻሉን ይቀጥላል፡፡
በራሳችን፣ ማናችንም ብንሆን እግዚአብሔር የጠራንን ለመሆንና ለማድረግ የሚያስፈልገን ማንነት የለንም፤ እግዚአብሔር እንጂ! በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ያለህ ቀጣዩ ምዕራፍህ የማይናወጥ መሆኑን ማሰብ ይብዛልህ፤ ምንም እንኳን በዙሪያህ ያለው ዓለም ነውጥ የበዛበት ቢሆንም! የሰማዩ አባትህ እርሱ ወደ ጠራህ ነገር እንደሚያስቀጥልህ ቃል ይገባልሃል፡፡
ስለዚህ እቅድ
ነገህን እየፈራህ ከሆነ ይህ የአምስት ቀናት እቅድ ለአንተ ነው፡፡ ምናልባት ልትቋቋመው የማትችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞህ ይሆናል፤ ነገር ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ ሆነህ ኑር ይኸውም በአንተ ሕይወት የመጨረሻው ቃል ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡ አግዚአብሐርን ማስቀደም፣ ህወትህን ከዓላማው ጋር ማጣጣም፤ በሚያጠነክርህና ቀጣዩ ምን እንደሆነ በሚያስቀጥልህ እውነት ላይ ማረፍን ተማር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Badi Badibanga ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.bbc.org.za/