Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?ናሙና
እግዚአብሔርን ማስቀደም
ምናልባት ሕይወት እንቆቅልሽ በሆነ ወይም በጥፋት መንገድ አጨልሞብህ ይሆናል፣ በዚህም የቀረህ ቀጣዩስ ምንድነው ብለህ መጠየቅ ይሆን ይሆናል። ሁሉም ሰው እንደወትሮው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ያለ ይመስለዋል፤ ምናልባትም ለአንተ ህይወት ቀደም ሲል እንደነበረው ላይሆንህ ይችላል፡፡ ምን ሊሆን እንዳለም እርግጠኛ አይደለህም፡፡ የት እንደገና መገንባት መጀመር እንዳለበትም እርግጠኛ ልትሆን አትችልም፡፡ ምናልባት ብቻህን ቀርተህ ሊሆን ይችላል፣ በሀዘን ተመተህ ወይም የገንዘብ ክስረት ገጥሞህ ሊሆን ይችላል፤ እናም ቀጣዩ ምን ይሆን ወደሚለው ለመሄድ እምነት ያስፈልጋል፡፡

በሐጌ ምዕራፍ 1 ላይ ብቻ ህዝቡ ልባቸውን በምን ላይ እንደጣሉ ለማንፀባረቅ አግዚአብሔር ሁለት ጊዜ ያህል “መንገዳችሁን ተመልከቱ!” እያለ ሲጠይቃቸው እናያለን፡፡ እኛም ልክ እንደ እስራኤላውያኑ በእጅጉ ልናስቀድም ከሚገባን ነገር ፈቀቅ ብለን የግል ፍላጎታችን ላይ እያተኮርን እንገኛለን፡፡ እስራኤላውያን የገዛ ፈቃዳቸውን ኑሮ በመኖር ወጥመድ ተይዘው ወደቁ፤ በዚህም እግዚአብሔርን ተዉ! እግዚአብሔርን የህይወትህ ማዕከል ለማድረግ የምታደርገው ጦርነት በህይወት ዘመንህ ከምታደርጋቸው የትኛውም ጦርነት ዋናና ወሳኙ ነው፤ ይህ ምንም እንኳን ወደ ዘላለም ጉዞ እያቀናህ ስትሄድ የሚገጥምህ ተግዳሮት ቢሆንም ልትጋደልለት የሚገባህ ጦርነት ነው።
ሐጌ ጀምሮ የሚያበቃው የእግዚአብሔር ኃይልና ታማኝነት ስላለው ውጤት በማሳየት ነው። እግዚአብሔር በህዝቡ መካከል በመኖር ጦርነቱን ተቀላቀለ ስለዚህም የእውነት ሊኖሩ ቻሉ፡፡ ሁኔታዎችህን አልፎ እርሱ በአንተ ትግል ውስጥም ይገባል፡፡ እግዚአብሔር እንድትሆን ወይም እንድትሠራ ለሚጠራህ ለማንኛውም ነገር የሰጠኸው ታማኝ ምላሽ አንተ ያለ እርሱ ፈፅሞ ልትጀምረው፣ ልታስቀጥለው ወይም ልትፈፅመው የምትችለው ነገር አይደለም። ደግነቱ አንተ የእርሱ ልጅ እንደሆንህ ለማስታወስና አንተን ወደ እርሱ ህብረት ለመጥራት አሁናዊ ሁኔታዎችህን ይጠቀማል።
ስለ ህዝቡ ታማኝነትና መታዘዝ እግዚአብሔር ቂሮስን አስነስቶ፤ ከምርኮ ነፃ አውጥቶ ወደ ምድራቸው እንዲገቡ መንገድን ጠርጓል፡፡ የፈረሰውን እንደገና የሚነገቡበትንም ግብዓት አቅርቧል፡፡ እግዚአብሔር አንተ እንዴት እርሱን ስታስቀድም የሚያዘጋጀውን ተመልከት፡፡ ስላጣኸው ነገር እያዘንህ ካለህ፣ ስላልተረጋገጠው ነገህ እየፈራህ ካለህ፣ ዛሬ ላይ ባለው ጫናዎች እንደተዋጥክ እየተሰማህ ካለህ፣ አንድ መጠየቅ ያለብህ ጥያቄ እንዳለህ እወቅ እርሱም “ቀጣዩ ምንድነው?” መልሱም እግዚአብሔርን ማስቀደም ነው፡፡ በእያንዳንዷ ቅፅበት ኢየሱስ መሄጃህ እና መደላደልህ መሆኑን እወቅ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ነው፤ እርሱ ለአንተ ነው፤ እንዲሁም ታማኝነቱ መቼም አያልቅም፡፡
ስለዚህ እቅድ
ነገህን እየፈራህ ከሆነ ይህ የአምስት ቀናት እቅድ ለአንተ ነው፡፡ ምናልባት ልትቋቋመው የማትችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞህ ይሆናል፤ ነገር ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ ሆነህ ኑር ይኸውም በአንተ ሕይወት የመጨረሻው ቃል ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡ አግዚአብሐርን ማስቀደም፣ ህወትህን ከዓላማው ጋር ማጣጣም፤ በሚያጠነክርህና ቀጣዩ ምን እንደሆነ በሚያስቀጥልህ እውነት ላይ ማረፍን ተማር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Badi Badibanga ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.bbc.org.za/