የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?ናሙና

Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?

ቀን {{ቀን}} ከ5

እግዚአብሔር በቀጣይ ምን ይፈልጋል

በሐጌ መጽሐፍ የእግዚአብሔር ህዝብ ምን ሲፈልጉ እንደነበር በግልፅ እንማራለን፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ቆም ብለው መመልከት አልቻሉም ነበር፡፡ ሐጌ ግን የእስራኤል ህዝብ ማስቀደም የሚገባቸውንና የሚጠብቁት ነገር ከእግዚአብሔር ፍቃድ ጋር እንዲጣጣም ሲያሳያቸውና ሲያነቃቸው እናያለን፤ ምክንያቱም ከስጦታዎች ሁሉ የሆነውን ስጦታ እርሱም ህልውናውን ይሰጣቸዋልና፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ስናልፍ የፍላጎቶችን ዝርዝር ማጠናቀር ቀላል ነው። ህይወታችንን ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስ ከመጓጓታችን የተነሳ የትኛውንም የገጠመንን መከራ ለማቅለል የሚረዳንን ምቹ ነገር ሁሉ እንከተላለን፡፡ ይሁን እንጂ ልክ እንደ ህዝብ እስራኤል እግዚአብሔር ቀጣይ ምን እንደሚፈልግ ለመመልከት በእነዚያ ሁኔታዎች ቆም ልንል እንችላለን፡፡ ውጪውን ከማየት ወደ ውስጠታችን እናተኩራለን፡፡

በሐጌ ዘመን የነበሩት ህዝብ እስራኤል ከእውነተኛ ጭንቀት ጋር እየታገሉ የነበሩ ናቸው፤ ይኸውም አንዳንዱ ከእነሱ አቅም በላይ ሲሆን አንዳንዱ ግን በራሳቸው የፈጠሩት ጭንቀት ነበር፡፡ ካጋጠማቸው መከራዎች የተነሳ በራስ ድንበር መታጠር፣ ራስን መውደድና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ቸል ማለት ሆኖባቸዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ ሂደት እነርሱን ሊተዏቸው ብቻ ሲሉ ለቀጣይ 17 ዓመታት የቤተ መቅደሱን መሰረት ጣሉ፡፡ ትኩረታቸውን ወደ ራሳቸው አስቸኳይ፣ ሥጋዊ ፍላጎቶች እና ምቾቶች ይኸውም እንደ ቤት፣ ሰብል፣ ምግብ እና ልብስ ባሉት ነገሮች ላይ በማድረግ የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ እንደገና መገንባቱን ቸል አሉ። እስኪ እግዚአብሔር ከዛሬ ወር፣ ከዓመት ወይም ከ10 ዓመት በፊት በግልፅ የመጨረሻ ጊዜ የነገረህን አስብ፡፡ ከገጠመህ ታላቅ መከራ የተነሳ እግዚአብሔርን ባለማወቅ አለመታዘዝ ገጥሞ ይሆን? ገጥሞህ ከሆነ እግዚአብሔር እንድታደርገው የጠራህን ነገር ችላ በማለትህ ባለፉት ዘመናት በሕይወትህ ውስጥ ምን ያህል እንደተጫወተብህ አስብ።

ሐጌ የእግዚአብሔር ህዝብ ቤተ መቅደሱን በመስራት ሂደት ላሳየው ግድየለሽነት በድፍረት ሞግቷቸዋል፡፡ እርግጥ ነው እግዚአብሔር ህንፃ አልነበረም የፈለገው፡፡ አካላዊ ሕንጻው የእርሱን መገኘትና ከሚወዳቸው ህዝቡ ጋር ያለውን ህብረት የሚያመለክት ሲሆን በዙሪያው ላሉት ህዝቦች ደግሞ የአንድ እውነተኛ አምላክ ኃይል እና ዓላማዎች ማሳያ ነው።

እግዚአብሔር ህዝበ እስራኤል ከእርሱ ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖራቸውና ጤናማ ልማዶችን እንዲገነቡ ፈልጓል። በሐጌ በኩል ንስሃ እንዲገቡ፣ እንደገና እንዲያስቀድሙትና ትኩረት እንዲሰጡት ሲያሳስባቸው እናያለን፡፡ ምናልባት አንተም ከእግዚአብሔር ያለህን ህብረት ቸል እንድትል የሚጫኑህ፣ የሚያስጨንቁህና የሚጨቁኑህ ሁኔታዎች ሊኖር ይችላል፡፡ ከራስህ ድሎት እግዚአብሔርን ወደመከተል በንስሃ፣ እንደገና እርሱን ማስቀደምና በተግባር ለእርሱ ትኩረት መስጠት በህይወትህ ላይ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? እስቲ እግዚአብሔር ለአንተ ካለው ምርጥ የሚለይህን ነገሮች ለይተህ አውጣቸው፤ ከዚያም እግዚአብሔር ለህይወትህ ያቀደውን የመገኘቱን ሙላት ለማጣጣምም ንስሃ ግባ፣ እንደገና አስቀድመው፤ እንደገናም ትኩረት አድርግ፡፡ ዘላለማዊ የሆነ፤ የሁሉ ፈጣሪ የሆነ ፈጣሪ ከሰው ምንማ የማይሻና በሰው እጅ የማይገለገል ሆኖ ሳለ አሁንም ከእኛ ጋር ህብረት ማድረግ ይፈልጋል፡፡ ፍቅሩ መተኪያ የሌለው፤ በትህትና ለሚፈልጉት ሁሉ በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በነፃ የተሰጠ ነው፡፡ ስሙ አማኑኤል (ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር)፤ ህይወታችንን እንደገና በእርሱ ማዕከል ውስጥ እንድናደርግና ቀጣዩን ምዕራፋችን ሊያመለክተን ያለማቋረጥ ይጠራናል፡፡

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

Haggai: ቀጣዩ ምን ይሆን?

ነገህን እየፈራህ ከሆነ ይህ የአምስት ቀናት እቅድ ለአንተ ነው፡፡ ምናልባት ልትቋቋመው የማትችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞህ ይሆናል፤ ነገር ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ ሆነህ ኑር ይኸውም በአንተ ሕይወት የመጨረሻው ቃል ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡ አግዚአብሐርን ማስቀደም፣ ህወትህን ከዓላማው ጋር ማጣጣም፤ በሚያጠነክርህና ቀጣዩ ምን እንደሆነ በሚያስቀጥልህ እውነት ላይ ማረፍን ተማር፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Badi Badibanga ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.bbc.org.za/