መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነውናሙና
![La Biblia está viva](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans%2F27965%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
መጽሐፍ ቅዱስ ያስታጥቀናል እስቲ
ራስህን ከሌላ ሃገር ለመጣ ሰው "በፍጥነት ተናጋሪ" የሚል ትርጉም ያለው ቡድን አባል እንደሆንክ አድርገህ ራስህን ስታስተዋውቅ አስብ። "ፖፖሉካ" የሚለው ስም ትርጉም ይህ ነው፣ ይህም በቬራክሩዝ፣ ሜክሲኮ ያሉ ሰዎች እና ቋንቋ ጋር የተገናኘ ነው። እስከ ዛሬ ድረስ "ፖፖሉካ" በዚያ አካባቢ ያሉ 35,500 ሰዎችን ለመግለጽ ጥ
ቅም ላይ ይውላል። ቋንቋውን የሚናገሩት ሰዎች "ኑንታጂዪ"— “ቀጥተኛ ንግግር” ብለው ይጠሩታል። ምንም እንኳን ኑንታጂዪ ለአንዳንዶች ብዙ ፋይዳ ያለው ባይመስልም፣ የአዲስ ኪዳንን በራሳቸው ቋንቋ ለሚያነቡ ወይም ለሚያዳምጡ ሰዎች ለፈጠረው አካል ፋይዳ እንዳለው ይረዳሉ። ካሮሊና ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዷ ነች። የፖፖሉካ አዲስ ኪዳን ተርጓሚ የልጅ ልጅ ካሮሊና ከኮሌጅ የተመረቀች የመጀመሪያዋ የፖፖሉካ ሴት ነች። የእግዚአብሔርን ቃል በቋንቋዋ ለማካፈል ህይወቷን የሰጠች ስትሆን፣ አሁን ደግሞ 50 የሚሆኑ ሰዎችን በመምራት መዝሙረ ዳዊትን እየተረጎመች ነው። "መጽሐፍ ቅዱስን በስፓኒሽ ስናነብ፣ የባከነ ሙከራ ነው የሚመስለው። ነገር ግን በራሳችን ቋንቋ ስናነብ፣ ቀጥታ ወደልባችን ውስጥ ይገባል። ልባችንን ይነካል—ስሜታችንን ይነካል—ምክንያቱም በደንብ እንረዳዋለን።" ካሮሊና የ YouVersion ማህበረሰብ ንቁ ተሳታፊ ስትሆን በኑንታጂዪ የእግዚአብሔርን ቃል የምታስተምረው በ YouVersion ነው። "የእኛን ቃላት መተግበሪያችሁ ውስጥ ስላስገባችሁ በጣም ደስተኞች ነን፣ ምክንያቱም አሁን በአለም ውስጥ ያለ ማንም ሰው ማየት ይችላል—ቋንቋችን ከሌሎች ከሚታወቁ ቋንቋዎች ጋር አብሮ አለ! ብዙ ጊዜ ቋንቋችን ክብር አያገኝም ነበር፣ ነገር ግን በዚህ መተግበሪያ ውስጥ ቋንቋችን ክብር እንዳለው ማየት ችለናል።" ዛሬ፣ በቋንቋችሁ መጽሐፍ ቅዱስ ስላገኟችሁ አግዚአብሔርን ለማመስገን ጊዜ ውሰዱ። ስለ ካሮሊና እና በአለም ውስጥ ያሉ በሺዎች ሰለሚቆጠሩ መጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች እግዚአብሔር ይመስገን። ስለ ታማኝነታቸው እና ትጋታቸው፣ የእግዚአብሔር ቃል በሁሉም የአለም አካባቢዎች ይሰራጫል ይም የሚሰሙትን እና የሚረዱትን ይለውጣል።ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
![La Biblia está viva](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans%2F27965%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል በትጋት የብዙዎችን ልብ እና አእምሮን አድሷል—እናም እግዚአብሔር አሁንም አላበቃም። በዚህ የ 7 ቀን እቅድ፣ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ታሪክ እየሰራ እና በአለም ዙሪያ ህይወቶችን እንዴት እየቀየረ እንዳለ በቅርበት በመመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን የህይወት ለዋጭነት ሀይል አብረን እናከብር።
More
ይህ ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ እቅድ የተዘጋጀው እና የቀረበው በ YouVersion ነው።