መጽሐፍ ቅዱስ ህያው ነውናሙና
መፅሐፍ ቅዱስን ማንም ሊያስቆመው አይችልም
በ16ኛው ክፍለዘመን መፅሃፍ ቅዱስ በብዙ ቋንቋዎች አይገኝም ነበር። በጣም የተማሩ እና ባለጠጋ የሆኑ ሰዎች ብቻ በ እብራይስጥ : በግሪክ እና በላቲን ቋንቋዎች የሚያጠኑት መፅሀፍ ነበር ።
ነገርግን አንድ ዊሊያም ቲንዳል የተባለ ሊቅ ሁሉም ሰው የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ዕድል ማግኘት እንደሚገባው በማመን ወደ ገዛ ቋንቋው ወደሆነው ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ መፅሐፍ ቅዱስን መተርጎም ጀመረ።
ብዙ ባለስልጣናት በዚህ ሃሳቡ እና አመለካከቱ ምክንያት ተቃወሙት ስለሆነም ከሀገሩ ከእንግሊዝ ተሰዶ ወጣ ሆኖም በኋላ ላይ የራሱን የአዲስ ኪዳን ትርጉምን በድብቅ ወደሀገሩ ይዞ መመለስ ቻለ። ለ ዘጠኝ አመታትም የመጀመሪያውን የእንግሊዝኛ መፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም በድብቅ እየሰራ ከመታሰር ድኖ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ተያዘ እና በስህተት አስተምሮ ተከሶ ተቃጥሎ እንዲሞት ተፈረደበት።
ሆኖም እግዚአብሔር አንድን ነገር ሊያደርግ ሲነሳ ማንም ሊያቆመው አይችልም ።
የቲንዳል ሰማዕትነትም ለውጥ እንዲደረግ የሚጠይቅ የውስጥ ለውስጥ ንቅናቄን አቀጣጠለ።ከመቶ ዓመታት በኋላም ይህ ለውጥ ሊመጣ ቻለ። የኪንግ ጀምስ መፅሐፍ ቅዱስ በ እንግሊዘኛ ቋንቋ ሊዘጋጅም ቻለ ።በቀዳሚው እትሙም የቲንዳልን የትርጉም ስራዎች በአብዛኛው ያካተተ ነበር።
በጊዜ ሂደት እንግሊዝ በመፅሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ስርነቀል ለውጥ ውስጥ አለፈች። መንፈሳዊ መነሳሳት እና መነቃቃቶች ተካሄዱ: የሚሲዮናዊ እንቅስቃሴዎችም ተወለዱ: መፅሀፍ ቅዱስን የመተርጎም ስራ የሚሰሩ ተቋማትም ተቋቋሙ። ቅዱስ መፅሀፍ መላ ሀገሪቱን አነቃቃ! መነቃቃቱ የተጀመረው ግን ቀዳሚዎቹ ተርጓሚዎች ሁሉም ሰው የእግዚአብሔርን ቃል የማንበበ ዕድል ማግኘት አለበት ብለው በማመናቸው እና ለዚህም የሚጠቅም ስራ በመስራታቸው ነበር።
የቀዳሚዎቹ የመፅሀፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ፅናት እንዴት አይነት መነሳሳትን እየፈጠረባችሁ ነው ?
አሁን ቲንዳል ያለፈበትን መንገድ አስቡና እግዚአብሔርን ቃሉን በዙሪያችሁ ላሉ ሰዎች ለማድረስ ልትወስዷቸው ስለሚገቡ እርምጃዎች አቅጣጫ እንዲሰጣችሁ ጠይቁት። ምንአልባት አንድ ጥቅስ ለአንድ ሰው መላክ ሊሆን ይችላል ወይም ለመፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ሊሆንም ይችላል።
ምንም ቢሆን ምን የእግዚአብሔርን ቃል የማግኘት እድል ባይኖራችሁ ህይወታችሁ ከዛሬው እንዴት የተለየ ሊሆን እንደሚችል አስቡና የሌላ አንድ ሰው ህይወት ይቀየር ዘንድ ምክንያት ለመሆን ወስኑ።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል በትጋት የብዙዎችን ልብ እና አእምሮን አድሷል—እናም እግዚአብሔር አሁንም አላበቃም። በዚህ የ 7 ቀን እቅድ፣ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ታሪክ እየሰራ እና በአለም ዙሪያ ህይወቶችን እንዴት እየቀየረ እንዳለ በቅርበት በመመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን የህይወት ለዋጭነት ሀይል አብረን እናከብር።
More