በክርስቶስ ያለን ማንነትናሙና
ክብሩን ማን ያገኛል?
“ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል።” 2 ቆሮንቶስ 4፡17
ሰይጣን የሚፈልገውን እንዲያገኝ አትፍቀዱለት። ፍላጎቱ ክብር ለማግኘት ነው። የናንተን ከሰረቀ የራሱን ያገኛል። እንዴት ነው የሚሰርቀው? ዘላለማዊ የሆነው ላይ ሳይሆን ጊዜያዊ የሆነው ላይ እንድናተኩር በማድረግ ነው።
ባልሽ ትቶሽ በመሄዱ ብቸኛ ወላጅ ሆንሽ።
አለቃችሁ ያጣጥላችኋል፣ እንዲሁም እድገትን ሊሰጣችሁ ፈቃደኛ አይደለም።
በእድሜያችሁ ሙሉ ያጠራቀማችሁትን ጥሪት ንግድ ብትከፍቱበት በወሮበሎች ጥቃትና ውድመት ደረሰበት።
ከባድ ነው? — አዎን! ነገር ግን “ወዮልኝ” አንድ ጊዜ የምናሰማው እሮሮ ሳይሆን የዘወትር ማሊያችን ስናደርገው ሰይጣን ክብሩን ያገኛል። ፈተናዎች እኛን ሊያበረቱን የተዘጋጁ ተራሮች እንደሆኑ ሳይሆን መሰናክል እንዲሆኑብን ስንፈቅድ፣ ቃላቶቻችን ለሰይጣን ሙገሳ ይሆናሉ።
ያለፈ ፈተና ነገአችን ሲይዝ፣ በቸልተኝነት ምክንያት የጥቃት ቁስላችን በምሬትና በይቅር ባይ አለመሆን ሲመረዝ፤ ለሰይጣንን ጀሌዎች ከባድ መሳሪያ እያስታጠቅናቸው ነው። ታዲያ እንደዚህ ሲሆን በምሬት የተሞሉ ሃሳቦቻችን የሰይጣንን ስራ የሚሰሩ ቅጥረኛ ሰራተኞቹ ስለሚሆኑ እርሱ ሽርሽር ሊሄድ ሁሉ ይችላል።
ፍጻሜያችን ይህ አይደለም። የሰይጣንንም ዕቅድ አንስተውም (2 ቆሮ 2፡11)። የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የፈሰሰው ለዚህ አይደለም። ለዘላለም የምንኖር ነን — በኢየሱስ ስም ሃሳቦቻችንም እንደዚሁ ይሁኑ!
ቀና በሉ! እጆቻችሁ በታች ሲሰሩ ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማይ ማማተርን አለማምዷቸው። ምክንያቱም ልባችን ዓይናችንን ይከተላል፣ እጆቻችን ደሞ ልባችንን። ይህን ብታደርጉ አትስቱም። የከበደባችሁ የአሁኑ መከራ ወደፊት በሚገለጠው እውነታ ጸጋ በአሁኑ ጊዜ ይጥለቀለቃል። ይህን ስታደርጉ እግዚአብሔር ክብሩን ያገኛል፣ ለናንተም ያካፍላችኋል፣ ሰይጣን ግን ምንም አያገኝም። ሰይጣን ስራው ይከስራል። እግዚአብሔር ደሞ መቶ እጥፍ ያገኛል።
የሕይወት ተዛምዶ
ከሕይወታችሁ ማን ነው ክብር የሚያገኘው? ከፈተኖቻችሁስ? በመከራ ወቅት ልባችሁ ለእግዚአብሔር የተከፈተ ይሁን፣ ትማራላችሁ፣ ታድጋላችሁ፣ ትሆናላችሁ።
ፀሎት
ራሴን ዘላለም በክብር ከአንተ ጋር በመሆን ሃሳብ እሞላለሁ! አመሰግንሃለሁ!
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በእውነት በክርስቶስ ማን እንደሆንን ራሳችንን ለማስታወስ የ5 ቀን ጉዞ። ክርስቶስ ምን እንዳደረገልንና ይህ ከእርሱ ጋር በየቀኑ የምንጓዝበት መንገድ ላይ ምን ሚና እንደሚጫወት እናስታውስ።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org