በክርስቶስ ያለን ማንነትናሙና

በክርስቶስ ያለን ማንነት

ቀን {{ቀን}} ከ5

“እባኮዎን ፓስፖርት!”

በአንድ ወቅት በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ሳለሁ ፓስፖርቴን አጣሁት። የተስፋ መቁረጥ ስሜቱ አስገራሚ ነበር። ቆዳዬ ራሱ ወደ ፈረንጅነት ተለውጦ ነበር ብዬ አስባለሁ! በዚያን ጊዜ የትምህርት መረጃዎቼ፣ የሥራ ልምድ ወረቀቴና የባንክ ደብተሬ በጭራሽ ትርጉም አልነበራቸውም። የሚያስፈልገኝ ፓስፖርቴ ብቻ ነበር።

በብዙ መንገድ ኢየሱስ እንደ ፓስፖርታችን ነው። በጉምሩክና በኢሚግሬሽን ዓለም ውስጥ አንድ ብቻ ወሳኝ ነገር አለ - ፓስፖርታችሁ። እናም በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ አስፈላጊ የሆነው አንድ ስም ብቻ ነው -ኢየሱስ! እርሱም “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” እኛ መግባት የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው።

መልካም ሥነ-ምግባር አስፈላጊ አይደለም የሚል ሀሳብ እያቀረብኩ ነውን? እኔ እያልኩ ያለሁት ነገር ቢኖር መልካም ሥነ-ምግባር - ሌላው ቀርቶ ምርጥ ባህሪም ቢሆን በቂ አይደለም። የምንኖረው በጣም ብዙ ባልተጠናቀቁ ሥራዎች ግፊት ባለባት ዓለም ውስጥ ነው - ትምህርት ቤት፣ ሥራ፣ ክፍያዎች፣ ወዘተ። እኛም ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ የሥራ ዝርዝሮችን ወደ መንፈሳዊ ሕይወታችን እናስተላልፋለን። ግን በዚህ መንግሥት ውስጥ እነዚህ ዋጋ የላቸውም። ቆላስያስ 2፡23 እነዚህ “… የሥጋን ልቅነት ለመቆጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም” ሲል ያሳስበናል። እኛ የሚያስፈልገን ኢየሱስ ነው!

እኛ ባልተሳካልን በኩል ኢየሱስ ተሳክቶለታል። በዮሐንስ 8 ላይ በዝሙት የተያዘችው ሴት ኢየሱስ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ከእንግዲህ ግን ኃጢአት አትሥሪ” አላት። ከኃጢአት ነፃ ሆኖ የመኖር ኃይል የሚገኘው “ኩነኔ የለባቸውም” የሚለው ውስጥ ሲሆን፣ “ኩነኔ የለባቸውም” የመስቀሉ መልእክት ነው። (ሮሜ 8:1) ቆላስያስ 2፡14 “ሲቃወመንና ሲጻረረን የነበረውን የዕዳ ጽሕፈት ከነሕግጋቱ በመደምሰስ፣ በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው” ይለናል።

በመጨረሻ ዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ፓስፖርቴን አገኘሁት። በፍተሻ ስፍራው ትቼው ነበር። የጠፋ ፓስፖርትን በማግኘት ውስጥ የሚገኝ የተወሰነ ደስታና መተማመን አለ። ለእናንተ ወይ ኢየሱስን ለማታውቁት ወይም ከሥነ-ምግባራችሁ ጋር ለምታገሉ፣ የተጠናቀቀው የኢየሱስ ሥራ ደስታ ዛሬ የእናንተ ይሁን። እርሱ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ያለን መመኪያችን ነው።

የሕይወት ተዛምዶ

በሕይወታችሁ ውስጥ ሥራችሁን በእርሱ ሥራ የተካችሁበትን ቦታዎች መለየት ከቻላቹ እዩ። አሁን ሁለቱን አለዋውጧቸው።

ፀሎት

አብ ሆይ፣ ስለ ኢየሱስ አመሰግንሃለሁ!

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

በክርስቶስ ያለን ማንነት

በእውነት በክርስቶስ ማን እንደሆንን ራሳችንን ለማስታወስ የ5 ቀን ጉዞ። ክርስቶስ ምን እንዳደረገልንና ይህ ከእርሱ ጋር በየቀኑ የምንጓዝበት መንገድ ላይ ምን ሚና እንደሚጫወት እናስታውስ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org