በክርስቶስ ያለን ማንነትናሙና
መለኮት ከሰው ጋር
እግዚአብሔር ከሰው ጋር ለመገናኘት ቦታን አዘጋጀ፣ “የመገናኛው ድንኳን” ብሎ ጠራው! በዚህ በቆዳ ድንኳን ውስጥ የእግዚአብሔር ክብር ከሰው ጋር ኖሯል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ምን እንደ መጣ እናውቃለን! ክርስቶስ፣ አማኑኤል፣ እግዚአብሔር “ከእኛ ጋር” መጣ፡፡ በእርሱ ስቅለትና ትንሳኤ ምክንያት “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” አሁን “እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ” ሆኗል!
እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን? (1 ቆሮ 3፡16) ሰማይ ከምድር ጋር የሚገናኝበትና መለኮት ከሰው ልጆች ጋር የሚገናኝበት ቦታ አሁን እርስዎ እና እኔ ነን፡፡ ጥሪው ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ በእኛ ውስጥ እንዲኖር ነው፡፡ (ኤፌ. 3 17) የማደሪያው ድንኳን የአማኙ ጥላ ነበር። ይህ ማለት የፈውስ ሀይሉን በሙላት በውስጣችን ይዘናል ማለት ነው! በእኛ በኩል መንፈሱ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቃል! እግዚአብሔር እንዲህ እንድንሆን መፍቀዱ የሚያስደንቅ ነው! ይህ የእግዚአብሔርን የምሕረት መጠን የምናይበት ምስክር ነው!
ወዳጄ ሆይ፣ ይህንን ስታነብ እንደኔ ከሆንክ የብቃት እጥረቶችህ በፊትህ ድቅን ይላሉ፡፡ ይህም ከእርሱ የተሰወረ አይደለም፡፡ በዘፀአት 30፡16 እግዚአብሔር ለቤተመቅደስ ጥገናዎች አቅርቦት አደረገ፡፡ እግዚአብሔር የማይበላሹ እንደ ወርቅ ያሉትን ነገሮችን ብቻ ለድንኳኑ ስራ አልመረጠም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የመገናኛው ድንኳን ዋጋ በውስጡ ካለው ከእርሱ መገኘት እንዲሆን ፈለገ።
በ 2 ኛ ቆሮንቶስ 4፡7 ጳውሎስ “ነገር ግን ይህ እጅግ ታላቅ ኀይል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አለመሆኑን ለማሳየት፣ ይህ የከበረ ነገር በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን” ብሏል። ይህ ቤተመቅደስ (መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁ፣ አዕምሯችሁ) ከጊዜ ወደ ጊዜ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል፡፡ የኑሮ ውጣ ውረዶች፣ ሀዘኖችና ሌሎችም በዚህ የሥጋ ድንኳን ውስጥ ክፍተቶችንና ቀዳዳዎችን ሊፈጥሩ ይችላሉ። እግዚአብሔር ይህንን በእርግጥ ያውቃል። እንደ መቅደሱም ሁሉ፣ ከነዚህ ነገሮች አንዳቸውም አላገደውም፣ ይልቁንም እግዚአብሔር ሌዋውያን ቤተመቅደሱን እንዲያድሱ አዘዛቸው። እግዚአብሔር ከአመድ ላይ ውበትን ሊያወጣ እንደሚችል እወቁ! አሁንም የመለኮትና የ ፍጥረት መገናኛ እንድንሆን መርጦናል።
የሕይወት ተዛምዶ
በዚህ ቤተመቅደስ (በእርስዎ) ዙሪያ ያሉ ፍላጎቶች ምንድን ናቸው? በእምነት እጅዎን ዘርግተው ለጎረቤትዎ ፈውስ እግዚአብሔር እንዲጠቀምብዎት ይታመኑ፡፡ ተዓምር ያያሉ!
ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ ክብርህን የሚሸከም ይህ የሸክላ አፈር ይኸውልህ፡፡ ራዕይህን በውሰጤ አድስ! ራሴን በፊትህ አቀርባለሁ ተጠቀምብኝ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በእውነት በክርስቶስ ማን እንደሆንን ራሳችንን ለማስታወስ የ5 ቀን ጉዞ። ክርስቶስ ምን እንዳደረገልንና ይህ ከእርሱ ጋር በየቀኑ የምንጓዝበት መንገድ ላይ ምን ሚና እንደሚጫወት እናስታውስ።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org