ዘካርያስ 7:1-5
ዘካርያስ 7:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። የቤቴልም ሰዎች ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ሰዎቻቸውንም በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ዘንድ፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር። የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
ዘካርያስ 7:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ካሴሉ በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ የቤቴል ሰዎች እግዚአብሔርን ለመለመን ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች ጋር ላኩ፤ እነርሱም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ካህናትና ነቢያት፣ “ብዙ ዓመት እንዳደረግሁት፣ በአምስተኛው ወር ማዘንና መጾም ይገባኛልን?” ብለው ጠየቁ። ከዚያም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ “የምድሩን ሕዝብ ሁሉና ካህናቱን እንዲህ በላቸው፤ ‘ባለፉት ሰባ ዓመታት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት በርግጥ ለእኔ ነበርን?
ዘካርያስ 7:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። የቤቴልም ሰዎች ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ሰዎቻቸውንም በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ዘንድ፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር። የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
ዘካርያስ 7:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ኪስሌው የተባለ ዘጠነኛው ወር በገባ በአራተኛው ቀን እግዚአብሔር ለዘካርያስ የነገረው ቃል ይህ ነው፤ የቤትኤል ነዋሪዎች ሣርኤጼርንና ሬጌሜሌክን አብረዋቸው ከነበሩ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላኩአቸው፤ የላኩአቸውም የእግዚአብሔር በረከት ይወርድ ዘንድ እንዲጸልዩና፥ የቤተ መቅደሱን ካህናትና ነቢያትን “እስከ አሁን ለብዙ ዓመቶች እንዳደረግነው በየአምስተኛው ወር በመጾም ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ ማዘናችንን እንቀጥልን?” ብለው እንዲጠይቁ ነበር። ከዚህም በኋላ ወደ እኔ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ “ባለፉት ሰባ ዓመቶች በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት እኔን ለማክበር ነበርን?
ዘካርያስ 7:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት፥ ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን፥ የጌታ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። የቤቴልም ሰዎች በጌታ ፊት ልመና እንዲያቀርቡ ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ከሰዎቻቸው ጋር ላኩ፤ ለሠራዊት ጌታ ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መጾምና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው እንዲናገሩ ልኳቸው ነበር። የሠራዊትም ጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ ለምድሩ ሕዝብና ለካህናት ለሁሉም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ስታለቅሱ፥ በውኑ ለእኔ ነው የጾማችሁልኝ?