በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት፥ ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን፥ የጌታ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። የቤቴልም ሰዎች በጌታ ፊት ልመና እንዲያቀርቡ ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ከሰዎቻቸው ጋር ላኩ፤ ለሠራዊት ጌታ ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መጾምና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው እንዲናገሩ ልኳቸው ነበር። የሠራዊትም ጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ ለምድሩ ሕዝብና ለካህናት ለሁሉም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ስታለቅሱ፥ በውኑ ለእኔ ነው የጾማችሁልኝ?
ትንቢተ ዘካርያስ 7 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ዘካርያስ 7:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos