የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 7

7
ስለ ጾም ጥያቄ
1በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት፥ ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን፥ የጌታ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። 2የቤቴልም ሰዎች በጌታ ፊት ልመና እንዲያቀርቡ ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን ከሰዎቻቸው ጋር ላኩ፤ 3ለሠራዊት ጌታ ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መጾምና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው እንዲናገሩ ልኳቸው ነበር። 4የሠራዊትም ጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 5#አሞጽ 5፥21።ለምድሩ ሕዝብና ለካህናት ለሁሉም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ስታለቅሱ፥ በውኑ ለእኔ ነው የጾማችሁልኝ? 6ስትበሉና ስትጠጡስ፥ የምትበሉትና የምትጠጡት ለራሳችሁ አይደለምን?
7ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች እየኖሩባቸው፥ በሰላም ተቀምጠው እያሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች እየኖሩባቸው በነበረ ጊዜ አይደለም እንዴ፥ ይህንን ቃል ጌታ በቀደሙት ነቢያት አማካኝነት የተናገረው? 8የጌታም ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ 9#ኢሳ. 1፥17፤ 58፥6።የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ እርስ በርሳችሁ ደግነትና ርኅራኄ ይኑራችሁ፤ 10#ዘፀ. 22፥20-24፤ ዘዳ. 24፥17፤ ኤር. 5፥28፤ ሚክ. 2፥1። መበለቲቱንና ድኻ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉ ነገር በልቡ አያስብ። 11#ዘፀ. 32፥9፤ ኢሳ. 48፥4።እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ በእልኸኝነት ጀርባቸውን አዞሩ፤ ጆሮአቸውንም ደፈኑ። 12#ሕዝ. 11፥19።የሠራዊት ጌታም በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ታላቅ ቁጣ መጣ። 13እኔ ስጠራቸው እነርሱ አልሰሙኝም፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩኝ ጊዜ እኔ አልሰማቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። 14#ዘዳ. 4፥27።በማያውቋቸው በባዕዳን አሕዛብ መካከል በዐውሎ ነፋስ በተንኳቸው። ስለዚህ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚዘዋወርባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፤ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ