የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 6

6
ሰባተኛ ራእይ፦ አራቱ ሰረገሎች
1 # ራእ. 6፥2-8። ተመልሼም ዐይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ። 2በፊተኛው ሠረገላ ቀይ ፈረሶች፥ በሁለተኛውም ሠረገላ ጥቁር ፈረሶች ነበሩ፥ 3በሦስተኛውም ሠረገላ ነጭ ፈረሶች፥ በአራተኛውም ሠረገላ ዥጉርጉር ፈረሶች ነበሯቸው፤ ሁሉም ጠንካሮች ነበሩ። 4ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልኩት። 5#ራእ. 7፥1።መልአኩም መልሶ፦ “በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ እነዚህ አራቱ የሰማይ ነፋሳት ናቸው። 6ጥቁር ፈረሶች ያሉበት ወደ ሰሜን ይወጣል፤ ነጭ ፈረሶች ወደ ምዕራብ ይወጣሉ፥ ዥጉርጉር ፈረሶች ወደ ደቡብ ይወጣሉ” አለኝ። 7ጠንካሮቹ ፈረሶች ሲወጡ፥ በምድር ሁሉ ለመመላለስ አቈብቁበው ነበር፤ እርሱም፥ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ። 8ከዚያም ጮኾ፦ “እነሆ፥ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት እነርሱ መንፈሴን በሰሜን ምድር ላይ አሳርፈዋል” በማለት ተናገረኝ።
አክሊሎቹ
9የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 10ከባቢሎን ከመጡት ምርኮኞች ከሔልዳይ፥ ከጦብያና ከዮዳኤም ውሰድ፤ በዚያም ቀን መጥተህ ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ግባ። 11ብርንና ወርቅን ከእነርሱ ውሰድ፥ አክሊሎችንም ሥራ፤ በሊቀ ካህኑ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋቸው፤ እንዲህም በለው፦ 12#ኤር. 23፥5፤ ዘካ. 3፥8።የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ቁጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የጌታንም መቅደስ ይሠራል። 13#ዘካ. 4፥14።እርሱ የጌታን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይጐናጸፋል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ መግባባት ይኖራል። 14ሌሎቹም አክሊሎች ለሔሌም፥ ለጦብያ፥ ለዮዳኤምና ለሶፎንያስም ልጅ ለሔን፥ በጌታ መቅደስ ውስጥ ለመታሰቢያ ይሆናሉ። 15#ዘዳ. 28፥1።በሩቅ ያሉትም መጥተው የጌታን መቅደስ ይሠራሉ፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የጌታን ቃል በእውነት ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ