የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 5

5
አምስተኛ ራእይ፦ በራሪው ጥቅልል መጽሐፍ
1ተመልሼም ዐይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ። 2#ሕዝ. 2፥9-10፤ ራእ. 10፥9-11።እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አያለሁ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ወርዱም ዐሥር ክንድ ነው” አልኩት። 3እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ የሚሰርቅና በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእዚህ ላይ እንደተጻፈው ይጠፋል። 4#ዘፀ. 20፥7፤ 16።እኔ እልከዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ወደሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፤ በቤታቸውም ውስጥ ይኖራል፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።”
ስድስተኛ ራእይ፦ የክፋት መስፈሪያ
5ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ “ዐይኖችህን አንሣ፥ ይህችም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ” አለኝ። 6እኔም፦ “ምንድን ናት?” አልኩት። እርሱም፦ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ#5፥6 የእህል መስፈሪያ ወይም ቁና ማለት ነው። ናት” አለኝ። ደግሞም፦ “ይህ ነው በምድር ሁሉ ያለ የእነርሱ በደል” አለ። 7ከዚያም የእርሳሱን መክሊት አነሡት፥ እነሆም፥ በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። 8እርሱም፦ “ይህች ክፋት ናት” አለኝ፤ ከዚያም በኢፍ መስፈሪያው ውስጥ ጣላት፥ የእርሳሱንም ጠገራ በመስፈሪያ አፍ ላይ ጣለ።
9ከዚያም ዐይኖቼን አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበረ፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት። 10ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ “እነዚህ የኢፍ መስፈሪያውን ወዴት ይወስዱታል?” አልኩት። 11እርሱም፦ “በሰናዖር ምድር ቤት ሊሠሩለት ይወስዱታል፤ መቅደሱም በተዘጋጀ ጊዜ፥ እዚያ በስፍራው ይኖራል” አለኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ