ማሕልየ መሓልይ 7:11-13
ማሕልየ መሓልይ 7:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እኔ የልጅ ወንድሜ ነኝ፥ የእርሱም መመለሻው ወደ እኔ ነው። ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ፥ በመንደሮችም እንደር። ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤ ወይኑ አብቦ፥ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያ ጡቶቼን እሰጥሃለሁ።
ማሕልየ መሓልይ 7:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ውዴ ሆይ፤ ና ወደ ገጠር እንሂድ፤ ወደ መንደርም ገብተን እንደር፤ ማልደን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፣ ወይኑ እንቡጥ አውጥቶ፣ አበባው ፈክቶ፣ ሮማኑ አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያም ራሴን በፍቅር እሰጥሃለሁ። ትርንጐዎች መዐዛቸውን ሰጡ፤ አዲስ የተቀጠፈውም ሆነ የበሰለው፣ ጣፋጩ ፍሬ ሁሉ በደጃፋችን አለ፤ ውዴ ሆይ፤ ለአንተ አስቀምጬልሃለሁ።
ማሕልየ መሓልይ 7:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው። ውዴ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ በመንደሮችም እንደር። ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፥ ወይኑ አብቦ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፥ በዚያ ውዴን እሰጥሃለሁ።
ማሕልየ መሓልይ 7:11-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ውዴ ሆይ! ና፤ ከከተማ ወጥተን ወደ ገጠር እንሂድ፤ ሌሊቱን በዚያ እናሳልፍ። ማልደንም ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፤ የወይኑ አበባ ፈክቶ እንደ ሆነ፥ ሮማኑም አብቦ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያም ፍቅሬን እገልጥልሃለሁ። የእንኰይ ፍሬ መዓዛና እንዲሁም ደስ የሚያሰኙ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎች ደጃችንን ሞልተውታል። ውዴ ሆይ! ከነዚህም ፍሬዎች የበሰሉትንና አዲስ የተቀጠፉትን ለአንተ አኑሬልሃለሁ።