መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 7
7
1አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤
እናይሽም ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ።
በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ?
እርስዋ በሩቁ እንደምትታይ እንደ ማኅበር ማሕሌት ናት።
2አንቺ የአሚናዳብ ልጅ ሆይ፥
በጫማ አካሄድሽ እጅግ ያማረ ነው።
የዳሌዎችሽ አቀማመጥ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ
እንደ ዕንቍዎች ይመስላል።
3እንብርትሽ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት እንደ ተነጠጠ ጽዋ ነው፤
ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአበባም እንደ ታጠረ ነው።
4ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለት መንታ
እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።
5አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፤
ዐይኖችሽ በሐሴቦን ውስጥ በብዙዎች ልጅ በሮች አጠገብ እንዳሉ
እንደ ውኃ ኵሬዎች ናቸው፤
አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አፋዛዥ እንደሚመለከት
እንደ ሊባኖስ ግንብ ነው።
6በራስሽ ላይ ያለው ጠጕርሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ ነው፤
የጠጕርሽም ሹርባ እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፥
ንጉሡም በሹርባው ታስሯል።#ግእዝ “አሠረ ንጉሥ ለረዊጽ” ይላል።
7ወዳጄ ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ!
እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!
ደስታሽንም እወድደዋለሁ።
8ይህ ቁመትሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥
ጡቶችሽም የወይን ዘለላ ይመስላሉ።
9ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ
ጫፉንም እይዛለሁ አልሁ፤
ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ናቸው፥
የአፍንጫሽም ሽታ እንደ እንኮይ ነው።
10ጕሮሮሽም ለልጅ ወንድሜ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥
ለከንፈሮችና ለምላሴ እንደሚስማማ
እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው።
11እኔ የልጅ ወንድሜ ነኝ፥ የእርሱም መመለሻው#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ምኞቱ” ይላል። ወደ እኔ ነው።
12ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ፥
በመንደሮችም እንደር።
13ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤
ወይኑ አብቦ፥ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ
ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤
በዚያ ጡቶቼን እሰጥሃለሁ።
14ትርንጎዎች መዓዛን ስጡ፤
መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥
አሮጌው ከአዲሱ ጋር፥ በደጃችን አሉ፤
ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።
Currently Selected:
መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 7: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ