መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 8

8
1ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ #ዕብ. “የእ​ና​ቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወን​ድሜ ምነው በሆ​ንህ” ይላል።የእ​ና​ቴን ጡት ትጠባ ዘንድ ማን በሰ​ጠህ?
በሜዳ ባገ​ኘ​ሁህ ጊዜ በሳ​ም​ሁህ፥ ማንም ባል​ና​ቀ​ኝም ነበር።
2ይዤ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ ባገ​ባ​ሁህ፥
እኔ ከመ​ል​ካሙ የወ​ይን ጠጄ ከሮ​ማ​ኔም ውኃ ባጠ​ጣ​ሁህ ነበር።
3ቀኙ ባቀ​ፈ​ችኝ ግራ​ውም ከራሴ በታች በሆ​ነች ነበር።
4እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥
ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት
በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።
5በልጅ ወን​ድ​ምዋ ላይ ተደ​ግፋ እንደ ማለዳ ደም​ቃና አብ​ርታ የም​ት​ወጣ ይህች ማን ናት?
ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ከእ​ን​ኮይ በታች አስ​ነ​ሣ​ሁህ፤
በዚያ እና​ትህ አማ​ጠ​ችህ፥
በዚ​ያም ወላጅ እና​ትህ ወለ​ደ​ችህ።
6እንደ ቀለ​በት በል​ብህ፥
እንደ ቀለ​በ​ትም ማኅ​ተም በክ​ን​ድህ አኑ​ረኝ፤
ፍቅር እንደ ሞት የበ​ረ​ታች ናትና፥
ቅን​ዐ​ትም እንደ ሲኦል የጨ​ከ​ነች ናትና።
ላን​ቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበ​ል​ባል ነው።
7ብዙ ውኃ ፍቅ​ርን ያጠ​ፋት ዘንድ አይ​ች​ልም፥
ፈሳ​ሾ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​አ​ትም፤
ሰው የቤ​ቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ አይ​ን​ቁ​ትም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይን​ቁ​ታል” ይላል።
8እኅ​ታ​ችን ትንሽ ናት፥ ጡትም የላ​ትም፤
ስለ እር​ስዋ በሚ​ና​ገ​ሩ​ባት ቀን
ለእ​ኅ​ታ​ችን ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት?
9እር​ስዋ ቅጥር ብት​ሆን የብር ግንብ በላ​ይዋ እን​ሥራ፤
ደጅ​አ​ፍም ብት​ሆን የዝ​ግባ ሳንቃ እን​ሥ​ራ​ላት።
10እኔ ቅጥር ነኝ፥ ጡቶ​ችም እንደ ግንብ ናቸው፤
በዚያ ጊዜ በፊቱ ሰላ​ምን እን​ደ​ም​ታ​ገኝ ሆንሁ።
11ለሰ​ሎ​ሞን በብ​ኤ​ላ​ሞን የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው፤
የወ​ይ​ኑን ቦታ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ አከ​ራ​የው፤
ሰው ሁሉ በየ​ጊ​ዜው ለፍ​ሬው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አንድ ሺህ ብር” ይላል። ያመ​ጣል።
12ለእኔ ያለኝ የወ​ይን ቦታ በፊቴ ነው፤
አንዱ ሺህ ለሰ​ሎ​ሞን፥
ሁለቱ መቶ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ ነው።
13በአ​ት​ክ​ልቱ ቦታ ሲኖር ሌሎች አዩት፥
ቃል​ህን አሰ​ማኝ።
14ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ፍጠን፤
በቅ​መም ተራራ ላይ ሚዳ​ቋን
ወይም የዋ​ሊ​ያን እን​ቦሳ ምሰል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ