መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 8
8
1ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ #ዕብ. “የእናቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወንድሜ ምነው በሆንህ” ይላል።የእናቴን ጡት ትጠባ ዘንድ ማን በሰጠህ?
በሜዳ ባገኘሁህ ጊዜ በሳምሁህ፥ ማንም ባልናቀኝም ነበር።
2ይዤ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ወላጅ እናቴም እልፍኝ ባገባሁህ፥
እኔ ከመልካሙ የወይን ጠጄ ከሮማኔም ውኃ ባጠጣሁህ ነበር።
3ቀኙ ባቀፈችኝ ግራውም ከራሴ በታች በሆነች ነበር።
4እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥
ወድዶ እስኪነሣ ድረስ ፍቅሬን እንዳትቀሰቅሱትና እንዳታስነሡት
በምድረ በዳው ኀይልና ጽንዐት አምላችኋለሁ።
5በልጅ ወንድምዋ ላይ ተደግፋ እንደ ማለዳ ደምቃና አብርታ የምትወጣ ይህች ማን ናት?
ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፤
በዚያ እናትህ አማጠችህ፥
በዚያም ወላጅ እናትህ ወለደችህ።
6እንደ ቀለበት በልብህ፥
እንደ ቀለበትም ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፤
ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥
ቅንዐትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና።
ላንቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበልባል ነው።
7ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም፥
ፈሳሾችም አያሰጥሙአትም፤
ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ አይንቁትም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይንቁታል” ይላል።
8እኅታችን ትንሽ ናት፥ ጡትም የላትም፤
ስለ እርስዋ በሚናገሩባት ቀን
ለእኅታችን ምን እናድርግላት?
9እርስዋ ቅጥር ብትሆን የብር ግንብ በላይዋ እንሥራ፤
ደጅአፍም ብትሆን የዝግባ ሳንቃ እንሥራላት።
10እኔ ቅጥር ነኝ፥ ጡቶችም እንደ ግንብ ናቸው፤
በዚያ ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ።
11ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፤
የወይኑን ቦታ ፍሬውን ለሚጠብቁ አከራየው፤
ሰው ሁሉ በየጊዜው ለፍሬው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አንድ ሺህ ብር” ይላል። ያመጣል።
12ለእኔ ያለኝ የወይን ቦታ በፊቴ ነው፤
አንዱ ሺህ ለሰሎሞን፥
ሁለቱ መቶ ፍሬውን ለሚጠብቁ ነው።
13በአትክልቱ ቦታ ሲኖር ሌሎች አዩት፥
ቃልህን አሰማኝ።
14ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ፍጠን፤
በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋን
ወይም የዋሊያን እንቦሳ ምሰል።
Currently Selected:
መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 8: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ